Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 17:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ይፈሩ ነበር፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ በሚ​ኖ​ሩ​በት ከተማ በሰ​ማ​ርያ በሠ​ሩት በከ​ፍ​ታው ቦታ ጣዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን አኖሩ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ይፈሩ ነበር፤ ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ለኮ​ረ​ብ​ታው መስ​ገ​ጃ​ዎች ካህ​ና​ትን አደ​ረጉ፤ በኮ​ረ​ብ​ታ​ውም መስ​ገ​ጃ​ዎች ይሠዉ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 እግዚአብሔርን አመለኩ፤ ይሁን እንጂ እያንዳንዱ ወገን የመጣበትን ሕዝብ ልማድ ተከትሎ፣ በየኰረብታው ባሉት ቤተ ጣዖታት የሚያገለግሉትን ካህናት ሾመ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 እነዚሁ ሰዎች በተጨማሪ ለእውነተኛው አምላክ ለእግዚአብሔር ይሰግዱ ነበር። ከእያንዳንዳቸውም ቡድን በአረማውያን የማምለኪያ ስፍራዎች የሚያገለግሉና መሥዋዕት የሚያቀርቡላቸውን ካህናት መረጡ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 እነዚሁ ሰዎች በተጨማሪ ለእውነተኛው አምላክ ለእግዚአብሔር ይሰግዱ ነበር። ከእያንዳንዳቸውም ቡድን በአረማውያን የማምለኪያ ስፍራዎች የሚያገለግሉና መሥዋዕት የሚያቀርቡላቸውን ካህናት መረጡ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 እግዚአብሔርንም ይፈሩ ነበር፤ ከመካከላቸውም ለኮረብታው መስገጃዎች ካህናት አደረጉ፤ በኮረብታውም መስገጃዎች ይሠዉ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 17:32
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በኮ​ረ​ብ​ቶ​ቹም ላይ መስ​ገ​ጃ​ዎ​ችን ሠራ፤ ከሌዊ ልጆች ካይ​ደሉ ከማ​ን​ኛ​ውም ሕዝብ ሁሉ የጣ​ዖት ካህ​ና​ትን ሾመ።


በየ​ሕ​ዝ​ባ​ቸ​ውም አም​ላ​ኮ​ቻ​ቸ​ውን አደ​ረጉ፤ ሳም​ራ​ው​ያ​ንም በሠ​ሯቸው በኮ​ረ​ብ​ታው መስ​ገ​ጃ​ዎች ሕዝቡ ሁሉ በሚ​ኖ​ሩ​ባቸው ከተ​ሞ​ቻ​ቸው አኖ​ሩ​አ​ቸው።


በሰገነትም ላይ ለሰማይ ሠራዊት የሚሰግዱትን፥ በእግዚአብሔርና በንጉሣቸው በሚልኮም ምለው የሚሰግዱትን፥


በሰ​ማ​ር​ያም ከተ​ሞች የነ​በ​ሩ​ትን፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያስ​ቈ​ጡት ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የሠ​ሩ​ትን የኮ​ረ​ብ​ታ​ውን መስ​ገ​ጃ​ዎች ኢዮ​ስ​ያስ አስ​ወ​ገ​ዳ​ቸው፤ በቤ​ቴ​ልም እን​ዳ​ደ​ረ​ገው ነገር ሁሉ እን​ዲሁ አደ​ረ​ገ​ባ​ቸው።


ከዚ​ህም በኋላ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ከክ​ፋቱ አል​ተ​መ​ለ​ሰም፤ ነገር ግን ለኮ​ረ​ብ​ታ​ዎቹ መስ​ገ​ጃ​ዎች አብ​ልጦ ከሕ​ዝብ ሁሉ የጣ​ዖት ካህ​ና​ትን ሾመ፤ የሚ​ወ​ድ​ደ​ው​ንም ሁሉ ይቀ​ድስ ነበር፤ እር​ሱም ለኮ​ረ​ብ​ቶቹ መስ​ገ​ጃ​ዎች ካህን ይሆን ነበር።


ከቀ​በ​ሩ​ትም በኋላ ልጆ​ቹን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፥ “በሞ​ትሁ ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው በተ​ቀ​በ​ረ​በት መቃ​ብር ቅበ​ሩኝ፤ አጥ​ን​ቶቼ ከአ​ጥ​ን​ቶቹ ጋር ይድኑ ዘንድ አጥ​ን​ቶቼን በአ​ጥ​ን​ቶቹ አጠ​ገብ አኑሩ፤


በዚ​ያም መቀ​መጥ በጀ​መሩ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አይ​ፈ​ሩ​ትም ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አን​በ​ሶ​ችን ሰደ​ደ​ባ​ቸው፤ ይገ​ድ​ሉ​አ​ቸ​ውም ነበር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሲፈሩ ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው እንደ ፈለ​ሱት እንደ አሕ​ዛብ ልማድ አም​ላ​ካ​ቸ​ውን ያመ​ልኩ ነበር።


ወደ ዘሩ​ባ​ቤ​ልና ወደ አባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆ​ችም ቀር​በው፥ “የአ​ሦር ንጉሥ አስ​ራ​ዶን ወደ​ዚህ ካመ​ጣን ቀን ጀምሮ ለአ​ም​ላ​ካ​ችሁ እን​ሠ​ዋ​ለ​ንና፥ እንደ እና​ን​ተም እን​ፈ​ል​ገ​ዋ​ለ​ንና ከእ​ና​ንተ ጋር እን​ሥራ” አሉ​አ​ቸው።


በስ​ም​ን​ተ​ኛ​ውም ወር በዐ​ሥራ አም​ስ​ተ​ኛው ቀን በልቡ ባሰ​በው ቀን ወደ ሠራው መሠ​ዊያ ወጣ፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በዓል አደ​ረ​ገ​ላ​ቸው፤ ወደ መሠ​ዊ​ያ​ውም ሊሠዋ ወጣ።


እነ​ዚ​ህም አሕ​ዛብ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይፈሩ ነበር፤ ደግ​ሞም የተ​ቀ​ረጹ ምስ​ሎ​ቻ​ቸ​ውን ያመ​ልኩ ነበር፤ ልጆ​ቻ​ቸ​ውም፥ የልጅ ልጆ​ቻ​ቸ​ውም አባ​ቶ​ቻ​ቸው እን​ዳ​ደ​ረጉ እስከ ዛሬ ድረስ እን​ዲሁ ያደ​ር​ጋሉ።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች