Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 15:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 በዚያ ጊዜም ምና​ሔም ቴር​ሳን፥ በእ​ር​ስ​ዋም ያሉ​ትን ሁሉ፥ ዳር​ቻ​ዋ​ንም መታ፤ ይከ​ፍ​ቱ​ለ​ትም ዘንድ አል​ወ​ደ​ዱ​ምና መታት፤ በእ​ር​ስ​ዋም የነ​በ​ሩ​ትን እር​ጉ​ዞች ሁሉ ሰነ​ጠ​ቃ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 በዚያ ጊዜም ምናሔም ከቴርሳ ወጥቶ በቲፍሳና በከተማዪቱ ነዋሪዎች ላይ ሁሉ፣ በአካባቢዋም ጭምር አደጋ ጣለ፤ ይህን ያደረገውም የከተማዪቱን በሮች ለመክፈት ፈቃደኞች ባለመሆናቸው ነበር፤ ቲፍሳን መታት፤ የነፍሰጡሮችንም ሆድ ሁሉ ቀደደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ምናሔም ከቲርጻ ተነሥቶ በሚያልፍበት ጊዜ እግረ መንገዱን የቲፍሳሕን ከተማ፥ ነዋሪዎችዋንና በዙሪያዋ የነበረውን ግዛት ሁሉ ደመሰሰ፤ ይህንንም ያደረገበት ምክንያት የከተማይቱ ነዋሪዎች ለእርሱ እጃቸውን ለመስጠት ባለመፍቀዳቸው ነበር፤ ከዚህም የተነሣ ነፍሰ ጡሮችን እንኳ ሳይምር ሆዳቸውን ቀደደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ምናሔም ከቲርጻ ተነሥቶ በሚያልፍበት ጊዜ እግረ መንገዱን የቲፍሳሕን ከተማ፥ ነዋሪዎችዋንና በዙሪያዋ የነበረውን ግዛት ሁሉ ደመሰሰ፤ ይህንንም ያደረገበት ምክንያት የከተማይቱ ነዋሪዎች ለእርሱ እጃቸውን ለመስጠት ባለመፍቀዳቸው ነበር፤ ከዚህም የተነሣ ነፍሰ ጡሮችን እንኳ ሳይምር ሆዳቸውን ቀደደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 በዚያን ጊዜም ምናሔም ከቴርሳ ወጥቶ ቲፍሳን በእርስዋም ያሉትን ሁሉ ዳርቻዋንም መታ፤ ይከፍቱለትም ዘንድ አልወደዱምና መታት፤ በእርስዋም የነበሩትን እርጉዞች ሁሉ ቀደዳቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 15:16
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አዛ​ሄ​ልም፥ “ጌታ​ዬን ምን ያስ​ለ​ቅ​ሰ​ዋል?” አለ። ኤል​ሳ​ዕም፥ “በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ላይ የም​ታ​ደ​ር​ገ​ውን ክፋት ስለ​ማ​ውቅ ነው፤ ምሽ​ጎ​ቻ​ቸ​ውን በእ​ሳት ታቃ​ጥ​ላ​ለህ፤ ጐል​ማ​ሶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በሰ​ይፍ ትገ​ድ​ላ​ለህ፤ ሕፃ​ና​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ትፈ​ጠ​ፍ​ጣ​ለህ፤ እር​ጉ​ዞ​ቻ​ቸ​ው​ንም ትሰ​ነ​ጥ​ቃ​ለህ፤” አለው።


ከወ​ንዙ ወዲህ ባሉት ነገ​ሥ​ታት ሁሉ፥ ከወ​ን​ዙም ወዲህ ባለው ሀገር ሁሉ ላይ ከቲ​ላሳ ጀምሮ እስከ ጋዛ ድረስ ነግሦ ነበር፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ባለው በሁሉ ወገን ሰላም ሆኖ​ለት ነበር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ዳር​ቻ​ቸ​ውን ያሰፉ ዘንድ የገ​ለ​ዓ​ድን ነፍሰ ጡሮች ቀድ​ደ​ዋ​ልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የአ​ሞን ልጆች ኀጢ​አት መቅ​ሠ​ፍ​ቴን ከማ​ድ​ረግ አል​መ​ለ​ስም።


የቀ​ረ​ውም የሴ​ሎም ነገር፥ የተ​ማ​ማ​ለ​ውም ዐመፅ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሓፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?


አቤ​ሜ​ሌ​ክም ወደ ግንቡ ሄደ። እነ​ር​ሱም ተዋ​ጉት። አቤ​ሜ​ሌ​ክም በእ​ሳት ሊያ​ቃ​ጥ​ለው ወደ ግንቡ ደጅ ቀረበ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች