Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 14:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 የቀ​ረ​ውም የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ነገር፥ ያደ​ረ​ገ​ውም ሁሉ፥ ኀይ​ሉም፥ የይ​ሁዳ የነ​በ​ረ​ውን ደማ​ስ​ቆ​ንና ሔማ​ትን ለእ​ስ​ራ​ኤል እንደ መለሰ፥ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 በኢዮርብዓም ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ነገር፣ የፈጸመው ሁሉና ያደረጋቸው ጦርነቶች እንዲሁም የይሁዳ ግዛት የነበሩትን ደማስቆንና ሐማትን እንዴት ለእስራኤል እንዳስመለሰ በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ ተጽፎ የሚገኝ አይደለምን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ዳግማዊ ኢዮርብዓም ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ፥ በጦርነት ላይ ያሳየው ጀግንነት፥ እንዲሁም የይሁዳ ግዛት የነበሩት ደማስቆና ሐማት ለእስራኤል እንዲመለሱ ያደረገበት ታሪካዊ ዝክረ ነገር ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ዳግማዊ ኢዮርብዓም ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ፥ በጦርነት ላይ ያሳየው ጀግንነት፥ እንዲሁም የይሁዳ ግዛት የነበሩት ደማስቆና ሐማት ለእስራኤል እንዲመለሱ ያደረገበት ታሪካዊ ዝክረ ነገር ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 የቀረውም የኢዮርብዓም ነገር፥ ያደረገውም ሁሉ፥ ጭከናውም፥ እንደ ተዋጋም፥ የይሁዳ የነበረውን ደማስቆንና ሐማትን ለእስራኤል እንደ መለሰ፥ በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 14:28
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዳዊ​ትም በደ​ማ​ስቆ ሶርያ ጭፍ​ሮች አኖረ፤ ሶር​ያ​ው​ያ​ንም ለዳ​ዊት ገባ​ሮች ሆኑ፤ ግብ​ርም አመ​ጡ​ለት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዳዊ​ትን በሄ​ደ​በት ሁሉ ጠበ​ቀው።


ዳዊ​ትም የሲ​ባን ሰዎች በገ​ደለ ጊዜ ሬዞን ሰዎ​ችን ሰብ​ስቦ የጭ​ፍራ አለቃ ሆነ፤ ወደ ደማ​ስ​ቆም ሄዱ፥ በዚ​ያም ተቀ​መጡ፤ በደ​ማ​ስ​ቆም ላይ አነ​ገ​ሡት።


የቀ​ረ​ውም የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ነገር፥ እን​ዴት እንደ ተዋጋ፥ እን​ዴ​ትም እንደ ነገሠ፥ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ ተጽ​ፎ​አል።


አካ​ዝ​ያስ ያደ​ረ​ገው የቀ​ረ​ውም ነገር እነሆ፦ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ ተጽ​ፎ​አል። በእ​ር​ሱም ፋንታ የአ​ክ​ዓብ ልጅ ወን​ድሙ ኢዮ​ራም ነገሠ።


ዮአ​ስም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በሰ​ማ​ር​ያም ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት ጋር ተቀ​በረ፤ ልጁም ኢዮ​ር​ብ​ዓም በፋ​ን​ታው ነገሠ።


ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም እንደ አባ​ቶቹ እንደ እስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት አን​ቀ​ላፋ፤ ልጁም ዘካ​ር​ያስ በፋ​ን​ታው ነገሠ።


እነ​ዚህ ሁሉ በት​ው​ል​ዶ​ቻ​ቸው በይ​ሁዳ ንጉሥ በኢ​ዮ​አ​ታም ዘመ​ንና በእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ዘመን ተቈ​ጠሩ።


የደ​ማ​ስ​ቆ​ንም ቍል​ፎች እሰ​ብ​ራ​ለሁ፤ በአ​ዎን ሸለቆ የሚ​ኖ​ሩ​ት​ንም ሰዎች አጠ​ፋ​ለሁ፤ የካ​ራን ሰዎች ወገ​ኖ​ች​ንም እቈ​ራ​ር​ጣ​ለሁ፤ የሶ​ርያ ሕዝ​ብም ወደ ቂር ይማ​ረ​ካሉ፤” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች