Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 13:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 “የም​ሥ​ራ​ቁ​ንም መስ​ኮት ክፈት” አለ፤ ከፈ​ተ​ውም። ኤል​ሳ​ዕም፥ “ወር​ውር” አለው፤ ወረ​ወ​ረ​ውም እር​ሱም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መድ​ኀ​ኒት ፍላጻ ነው፤ ከሶ​ርያ የመ​ዳን ፍላጻ ነው፤ እስ​ክ​ታ​ጠ​ፋ​ቸ​ውም ድረስ ሶር​ያ​ው​ያ​ንን በአ​ፌቅ ትመ​ታ​ለህ” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ቀጥሎም፣ “የምሥራቁን መስኮት ክፈት” አለው፤ ከፈተውም፤ ኤልሳዕም፣ “በል አስፈንጥረው” አለው፤ አስፈነጠረውም፤ ከዚያም፣ “የእግዚአብሔር የድል ቀስት! ሶርያ ድል የምትሆንበት ቀስት!” አለ። ኤልሳዕም እንደ ገና “ሶርያውያንንም አፌቅ ላይ ፈጽመህ ድል ታደርጋቸዋለህ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ኤልሳዕ “የምሥራቁን መስኮት ክፈት” አለ፤ ንጉሡም ከፈተው፤ ኤልሳዕም “ፍላጻውን አስፈንጥር!” አለው፤ ንጉሡም ፍላጻውን እንዳስፈነጠረ ወዲያውኑ ኤልሳዕ፥ “ፍላጻ ነህ፤ በአንተም አማካይነት እግዚአብሔር ሶርያውያንን ድል ያደርጋል፤ ሶርያውያንን ድል እስክትነሣቸው ድረስ በአፌቅ ከተማ ትወጋቸዋለህ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ኤልሳዕ “የምሥራቁን መስኮት ክፈት” አለ፤ ንጉሡም ከፈተው፤ ኤልሳዕም “ፍላጻውን አስፈንጥር!” አለው፤ ንጉሡም ፍላጻውን እንዳስፈነጠረ ወዲያውኑ ኤልሳዕ፥ “ፍላጻ ነህ፤ በአንተም አማካይነት እግዚአብሔር ሶርያውያንን ድል ያደርጋል፤ ሶርያውያንን ድል እስክትነሣቸው ድረስ በአፌቅ ከተማ ትወጋቸዋለህ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 “የምሥራቁን መስኮት ክፈት፤” አለ፤ ከፈተውም። ኤልሳዕም “ወርውር!” አለ፤ ወረወረውም። እርሱም “የእግዚአብሔር መድኃኒት ፍላጻ ነው፤ በሶርያ ላይ የመድኃኒት ፍላጻ ነው፤ እስክታጠፋቸው ድረስ ሶርያውያንን በአፌቅ ትመታለህ፤” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 13:17
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት ያጠ​ፋ​ቸው አሞ​ራ​ው​ያን እንደ ሠሩት ሁሉ፥ ጣዖ​ትን በመ​ከ​ተል እጅግ ርኩስ ነገ​ርን ሠራ።


የመ​ስ​ቀሉ ነገር በሚ​ጠፉ ሰዎች ዘንድ ስን​ፍና ነውና፥ ለም​ን​ድ​ነው ለእኛ ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይል ነው።


በሾ​ላ​ውም ዛፍ ራስ ውስጥ የሽ​ው​ሽ​ውታ ድምፅ ስት​ሰማ፥ በዚያ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ጭፍራ ለመ​ም​ታት በፊ​ትህ ወጥቶ ይሆ​ና​ልና በዚያ ጊዜ ፍጠን” አለው።


በእ​ነ​ዚ​ያም ወራት እን​ዲህ ሆነ። ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ለጦ​ር​ነት በእ​ስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያን ላይ ተሰ​በ​ሰቡ። እስ​ራ​ኤ​ልም ሊዋ​ጉ​አ​ቸው ወጡ፤ በአ​ቤ​ኔ​ዜር አጠ​ገ​ብም ሰፈሩ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም በአ​ፌቅ ሰፈሩ።


ይህ​ች​ንም ተአ​ም​ራት የም​ታ​ደ​ር​ግ​ባ​ትን በትር በእ​ጅህ ያዝ።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ይህ በእ​ጅህ ያለው ምን​ድን ነው?” አለው። እር​ሱም፥ “በትር ነው” አለ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ንጉሥ አለው፥ “እጅ​ህን በቀ​ስቱ ላይ ጫን።” ዮአ​ስም እጁን በቀ​ስቱ ላይ ጫነ፤ ኤል​ሳ​ዕም እጁን በን​ጉሡ እጅ ላይ ጫነ፦


ኤል​ሳ​ዕም ደግሞ፥ “ፍላ​ጻ​ዎ​ች​ህን ውሰድ” አለው ወሰ​ዳ​ቸ​ውም። የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ንጉሥ፥ “ምድ​ሩን ምታው” አለው። ንጉ​ሡም ሦስት ጊዜ መትቶ ቆመ።


“አክ​ዓብ በፊቴ እንደ ደነ​ገጠ አየ​ህን? በፊቴ በልጁ ዘመን በቤቱ ላይ ክፉ ነገር አመ​ጣ​ለሁ እንጂ በእ​ርሱ ዘመን ክፉ ነገር አላ​መ​ጣም።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች