Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 12:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 የተ​ና​ደ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ለመ​ጠ​ገን መክ​ፈል ለሚ​ያ​ሻው ሁሉ ድን​ጋ​ይ​ንና እን​ጨ​ትን ይገዙ ዘንድ፥ ለግ​ን​በ​ኞ​ችና ለድ​ን​ጋይ ወቃ​ሪ​ዎች ይሰ​ጡት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ለድንጋይ ጠራቢዎችና ለድንጋይ ቅርጽ አውጭዎች የሚከፈል፣ እንዲሁም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ለሚታደስበት ዕንጨትና ጥርብ ድንጋይ መግዣ የሚውል ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ለድንጋይ ጠራቢዎች፥ ለማደሻ አገልግሎት የሚውል እንጨትና ድንጋይ ለሚገዙና እንዲሁም ለልዩ ልዩ አስፈላጊ ነገሮች ለሚውል ተግባር ሁሉ ይከፍሉ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ለድንጋይ ጠራቢዎች፥ ለማደሻ አገልግሎት የሚውል እንጨትና ድንጋይ ለሚገዙና እንዲሁም ለልዩ ልዩ አስፈላጊ ነገሮች ለሚውል ተግባር ሁሉ ይከፍሉ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 የተመዘነውንም ገንዘብ የእግዚአብሔርን ቤት ለመሥራት በተሾሙት እጅ ይሰጡ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 12:12
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስለ ቤተ መቅ​ደ​ስም ድን​ጋዩ ያማረ ነው፥ አሠ​ራ​ሩም ያጌጠ ነው የሚ​ሉት ነበሩ።


ወደ ይሁዳ ሀገር ወደ ታላ​ቁም አም​ላክ ቤት እንደ ሄድን ንጉሡ ይወቅ፤ እር​ሱም በጥሩ ድን​ጋይ ይሠ​ራል፤ በቅ​ጥ​ሩም ውስጥ ልዩ እን​ጨት ይደ​ረ​ጋል፤ ያም ሥራ በት​ጋት ይሠ​ራል፤ በእ​ጃ​ቸ​ውም ይከ​ና​ወ​ናል።


ለጠ​ራ​ቢ​ዎ​ችና ለአ​ና​ጢ​ዎ​ችም ብር ሰጡ፤ የፋ​ር​ስም ንጉሥ ቂሮስ እንደ ፈቀ​ደ​ላ​ቸው የዝ​ግባ ዛፍ ከሊ​ባ​ኖስ በባ​ሕር ወደ ኢዮጴ ያመጡ ዘንድ ለሲ​ዶ​ናና ለጢ​ሮስ ሰዎች መብ​ልና መጠጥ፥ ዘይ​ትም ሰጡ።


ለሰ​ሎ​ሞ​ንም ሰባ ሺህ ተሸ​ካ​ሚ​ዎች፥ ሰማ​ንያ ሺህም በተ​ራ​ራው ላይ ድን​ጋይ የሚ​ጠ​ርቡ ጠራ​ቢ​ዎች ነበ​ሩት።


የተ​ሰ​በ​ሰ​በ​ው​ንም ገን​ዘብ ሥራ​ውን በሚ​ሠ​ሩና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት በሚ​ጠ​ብ​ቁት እጅ ይሰጡ ነበር። እነ​ር​ሱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ለሚ​ሠሩ ግን​በ​ኞ​ችና አና​ጢ​ዎች ይሰጡ ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች