Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 10:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 የአ​ክ​አ​ብም የቤቱ አለ​ቆች፥ የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም አለ​ቆች፥ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቹና ልጆ​ቹ​ንም የሚ​ያ​ሳ​ድጉ፥ “እኛ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ነን፤ ያዘ​ዝ​ኸ​ን​ንም ሁሉ እና​ደ​ር​ጋ​ለን፤ የም​ና​ነ​ግ​ሠው ሰው የለም፤ የም​ት​ወ​ድ​ደ​ውን አድ​ርግ” ብለው ወደ ኢዩ ላኩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ስለዚህ የቤተ መንግሥቱ አዛዥ፣ የከተማዪቱ ገዥ፣ ሽማግሌዎችና የልጆቹ ሞግዚቶች፣ “እኛ የአንተው አገልጋዮች ነን፤ ትእዛዝህን ሁሉ እንፈጽማለን፤ እኛ ማንንም አናነግሥም፤ ደስ የሚያሰኝህን ሁሉ አንተው አድርግ” በማለት ይህን መልእክት ለኢዩ ላኩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ስለዚህም የቤተ መንግሥቱ ኃላፊና የከተማይቱ ገዢ ከታወቁ የአገር ሽማግሌዎችና ከአሳዳጊ ሞግዚቶች ጋር በመተባበር ለኢዩ “እኛ አገልጋዮችህ ነን፤ አንተ የምታዘንን ሁሉ ለመፈጸም ዝግጁዎች ነን፤ እኛ ማንንም አናነግሥም፤ አንተ መልካም መስሎ የታየህን አድርግ” ሲሉ መልእክት ላኩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ስለዚህም የቤተ መንግሥቱ ኀላፊና የከተማይቱ ገዢ ከታወቁ የአገር ሽማግሌዎችና ከአሳዳጊ ሞግዚቶች ጋር በመተባበር ለኢዩ “እኛ አገልጋዮችህ ነን፤ አንተ የምታዘንን ሁሉ ለመፈጸም ዝግጁዎች ነን፤ እኛ ማንንም አናነግሥም፤ አንተ መልካም መስሎ የታየህን አድርግ” ሲሉ መልእክት ላኩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 የቤቱ አለቃ፥ የከተማይቱም አለቃ፥ ሽማግሌዎችና ልጆቹን የሚያሳድጉ “እኛ ባሪያዎችህ ነን፤ ያዘዝኸንንም ሁሉ እናደርጋለን፤ ንጉሥም በላያችን አናነግሥም፤ የምትወድደውን አድርግ፤” ብለው ወደ ኢዩ ላኩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 10:5
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አክ​ዓ​ብም አዝኖ ሄደ፤ በአ​ል​ጋ​ውም ላይ ተኝቶ ፊቱን ተሸ​ፋ​ፈነ፤ እን​ጀ​ራ​ንም አል​በ​ላም።


ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ች​ንና የሀ​ገ​ራ​ችን ሰዎች ሁሉ፦ ለመ​ን​ገድ ስንቅ ያዙ፤ ልት​ገ​ና​ኙ​አ​ቸ​ውም ሂዱ፦ እኛ ባሪ​ያ​ዎ​ቻ​ችሁ ነን፤ አሁ​ንም ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን አድ​ርጉ በሉ​አ​ቸው አሉን።


የይ​ሁ​ዳም ንጉሥ ሕዝ​ቅ​ያስ፥ “በድ​ያ​ለሁ፥ ከእኔ ተመ​ለስ፤ የም​ት​ጭ​ን​ብ​ኝ​ንም ሁሉ እሸ​ከ​ማ​ለሁ” ብሎ ወደ አሦር ንጉሥ ወደ ለኪሶ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ። የአ​ሦ​ርም ንጉሥ በይ​ሁዳ ንጉሥ በሕ​ዝ​ቅ​ያስ ላይ ሦስት መቶ መክ​ሊት ብርና ሠላሳ መክ​ሊት ወርቅ ጫነ​በት።


ኢያ​ሱ​ንም፥ “እኛ ባሪ​ያ​ዎ​ችህ ነን፤ ከሩቅ ሀገ​ርም ነን” አሉት። ኢያ​ሱም፥ “እና​ንተ እነ​ማን ናችሁ? ከወ​ዴ​ትስ መጣ​ችሁ?” አላ​ቸው።


እኔን የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ለኝ ካለ ይከ​ተ​ለኝ፤ የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ለኝ እኔ ባለ​ሁ​በት በዚያ ይኖ​ራ​ልና፤ እኔን የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ለ​ኝ​ንም አብ ያከ​ብ​ረ​ዋል።


እነ​ር​ሱን አት​ስሙ፤ ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ተገዙ፤ በሕ​ይ​ወ​ትም ኑሩ፤ ይህ​ችስ ከተማ ስለ ምን ባድማ ትሆ​ና​ለች?


አንተ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ወደ ማል​ህ​ላ​ቸው ምድር አደ​ር​ሳ​ቸው ዘንድ፦ ሞግ​ዚት የሚ​ጠ​ባ​ውን ልጅ እን​ድ​ታ​ቅፍ በብ​ትህ እቀ​ፋ​ቸው የም​ት​ለኝ፥ በውኑ ይህን ሕዝብ ሁሉ እኔ ፀነ​ስ​ሁ​ትን? ወይስ ወለ​ድ​ሁ​ትን?


ከዚ​ህም በኋላ ኢዩ፥ “ወገ​ኖ​ቼስ ከሆ​ና​ችሁ፥ ነገ​ሬ​ንም ከሰ​ማ​ችሁ የጌ​ታ​ች​ሁን ልጆች ራስ ቍረጡ፤ ነገም በዚህ ሰዓት ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ወደ እኔ ይዛ​ችሁ ኑ” ብሎ ሁለ​ተኛ ደብ​ዳቤ ጻፈ​ላ​ቸው። የን​ጉ​ሡም ልጆች ሰባው ሰዎች በሚ​ያ​ሳ​ድ​ጓ​ቸው በከ​ተ​ማ​ዪቱ ታላ​ላ​ቆች ዘንድ ነበሩ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች