Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 10:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት አቅ​ር​በው በፈ​ጸሙ ጊዜ ኢዩ ዘበ​ኞ​ቹ​ንና አለ​ቆ​ቹን፥ “ግቡና ግደ​ሉ​አ​ቸው፤ አን​ድም አያ​ም​ልጥ” አላ​ቸው። በሰ​ይ​ፍም ስለት ገደ​ሉ​አ​ቸው፤ ዘበ​ኞ​ችና አለ​ቆ​ችም ወደ ውጭ ጣሉ​አ​ቸው፤ ወደ በዓ​ልም ቤት ከተማ ሄዱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ኢዩ የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቅርቦ እንዳበቃ ጠባቂዎቹንና የጦር አለቆቹን፣ “ግቡና ግደሏቸው፤ ማንም እንዳያመልጥ” ሲል አዘዘ። እነርሱም በሰይፍ ፈጇቸው፤ ጠባቂዎቹና የጦር ሹማምቱም ሬሳውን በሙሉ ወደ ውጭ አውጥተው ጣሉ። ከዚያም ወደ ውስጠኛው የበኣል ቤተ ጣዖት ገቡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ኢዩ መሥዋዕቱን አቅርቦ እንዳበቃ ወዲያውኑ ለዘብ ጠባቂዎችና ለጦር መኰንኖች “ገብታችሁ እነዚህን ሁሉ ግደሉ፤ አንድም ሰው እንዳያመልጥ!” ሲል አዘዛቸው፤ እነርሱም ሰይፍ ሰይፋቸውን በመምዘዝ ገብተው ሁሉንም ገደሉ፤ ሬሳቸውንም ሁሉ እየጐተቱ ወደ ውጪ አወጡት፤ ከዚህም በኋላ ወደ ቤተ መቅደሱ ውስጠኛ ክፍል ገብተው፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ኢዩ መሥዋዕቱን አቅርቦ እንዳበቃ ወዲያውኑ ለዘብ ጠባቂዎችና ለጦር መኰንኖች “ገብታችሁ እነዚህን ሁሉ ግደሉ፤ አንድም ሰው እንዳያመልጥ!” ሲል አዘዛቸው፤ እነርሱም ሰይፍ ሰይፋቸውን በመምዘዝ ገብተው ሁሉንም ገደሉ፤ ሬሳቸውንም ሁሉ እየጐተቱ ወደ ውጪ አወጡት፤ ከዚህም በኋላ ወደ ቤተ መቅደሱ ውስጠኛ ክፍል ገብተው፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 የሚቃጠለውንም መሥዋዕት አቅርበው በፈጸሙ ጊዜ ኢዩ ዘበኞቹንና አለቆቹን “ግቡና ግደሉአቸው፤ አንድም አይውጣ፤” አላቸው። በሰይፍም ስለት ገደሉአቸው፤ ዘበኞችና አለቆችም ወደ ውጭ ጣሉአቸው፤ ወደ በኣልም ቤት ከተማ ሄዱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 10:25
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኤል​ያ​ስም ሕዝ​ቡን፥ “የበ​ዓ​ልን ነቢ​ያት ያዙ፤ ከእ​ነ​ርሱ አንድ ሰው እን​ኳን የሚ​ያ​መ​ልጥ አይ​ኑር፤” አላ​ቸው። ያዙ​አ​ቸ​ውም፤ ኤል​ያ​ስም ወደ ቂሶን ወንዝ ወስዶ፥ በዚያ እየ​ወጋ ጣላ​ቸው።


እር​ሱም፦ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰይ​ፉን በወ​ገቡ ላይ ይታ​ጠቅ፤ ሂዱና በሰ​ፈሩ ውስጥ ከበር እስከ በር ተመ​ላ​ለሱ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ወን​ድ​ሙን፥ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ጎረ​ቤ​ቱን፥ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም የቅ​ር​ቡን ይግ​ደል” አላ​ቸው።


“ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብቻ በቀር ለአ​ማ​ል​ክት የሚ​ሠዋ ፈጽሞ ይጥፋ።


ንጉ​ሡም በዙ​ሪ​ያው የቆ​ሙ​ትን እግ​ረ​ኞች፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ካህ​ናት እጅ ከዳ​ዊት ጋር ነውና፥ ኵብ​ለ​ላ​ው​ንም ሲያ​ውቁ አል​ነ​ገ​ሩ​ኝ​ምና፥ ዞራ​ችሁ ግደ​ሉ​አ​ቸው” አላ​ቸው። የን​ጉሡ አገ​ል​ጋ​ዮች ግን እጃ​ቸ​ውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ካህ​ናት ላይ ይዘ​ረጉ ዘንድ እንቢ አሉ።


በዚ​ያም የነ​በ​ሩ​ትን የኮ​ረ​ብ​ታ​ውን መስ​ገ​ጃ​ዎች ካህ​ናት ሁሉ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ዎቹ ላይ ገደ​ላ​ቸው፥ የሰ​ዎ​ቹ​ንም አጥ​ንት በመ​ሠ​ዊ​ያ​ዎቹ ላይ አቃ​ጠለ። ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ተመ​ለሰ።


የሀ​ገ​ሩም ሕዝብ ሁሉ ወደ በዓል ቤት ሄደው ሰበ​ሩት፤ መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም አፈ​ረሱ፤ ምስ​ሎ​ቹ​ንም አደ​ቀቁ፥ የበ​ዓ​ል​ንም ካህን ማታ​ንን በመ​ሠ​ዊ​ያው ፊት ገደ​ሉት። ካህኑ ዮዳ​ሄም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ጠባ​ቂ​ዎ​ችን ሾመ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች