Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 10:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትና ሌላ መሥ​ዋ​ዕ​ትም ያቀ​ርቡ ዘንድ ገቡ፤ ኢዩም፥ “በእ​ጃ​ችሁ አሳ​ልፌ ከም​ሰ​ጣ​ችሁ ሰዎች አንድ ሰው ያመ​ለጠ እንደ ሆነ ነፍሱ በዚያ እን​ዲ​ያ​መ​ልጥ ባደ​ረ​ገው ሰው ነፍስ ፋንታ ትሆ​ና​ለች” ብሎ በውጭ ሰማ​ንያ ሰዎ​ችን አዘ​ጋ​ጅቶ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ከዚያም የሚቃጠል መሥዋዕትና ሌላም መሥዋዕት ለማቅረብ ገቡ። በዚህ ጊዜም ኢዩ፣ “በእጃችሁ አሳልፌ ከሰጠኋችሁ ሰዎች አንድ እንኳ እንዲያመልጥ ያደረገ በገመዱ ይገባበታል” ብሎ በማስጠንቀቅ ውጭ ሰማንያ ሰዎች አዘጋጅቶ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ወዲያውም እርሱና ኢዮናዳብ ለበዓል የሚቃጠል መሥዋዕትና ሌላም ልዩ ልዩ መሥዋዕት ለማቅረብ ገቡ፤ ከዚህም ቀደም ብሎ ኢዩ በቤተ መቅደሱ ዙሪያ ሰማኒያ ወታደሮች በማሰለፍ “እነዚህን ሁሉ ሰዎች እንድትገድሉ ከእነርሱ አንድ ሰው እንኳ እንዲያመልጥ የሚያደርግ ማንም ሰው ቢኖር በዚያ ሰው ምትክ እርሱ ራሱ ይገደላል!” ሲል መመሪያ ሰጥቶአቸው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ወዲያውም እርሱና ኢዮናዳብ ለባዓል የሚቃጠል መሥዋዕትና ሌላም ልዩ ልዩ መሥዋዕት ለማቅረብ ገቡ፤ ከዚህም ቀደም ብሎ ኢዩ በቤተ መቅደሱ ዙሪያ ሰማኒያ ወታደሮች በማሰለፍ “እነዚህን ሁሉ ሰዎች እንድትገድሉ ከእነርሱ አንድ ሰው እንኳ እንዲያመልጥ የሚያደርግ ማንም ሰው ቢኖር በዚያ ሰው ምትክ እርሱ ራሱ ይገደላል!” ሲል መመሪያ ሰጥቶአቸው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 የሚቃጠል መሥዋዕትና ሌላ መሥዋዕትም ያቀርቡ ዘንድ ገቡ፤ ኢዩም “በእጃችሁ አሳልፌ ከምሰጣችሁ ሰዎች አንድ ሰው ያመለጠ እንደ ሆነ ነፍሱ በዚያ ነፍስ ፋንታ ትሆናለች፤” ብሎ በውጪ ሰማንያ ሰዎችን አዘጋጅቶ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 10:24
3 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኤል​ያ​ስም ሕዝ​ቡን፥ “የበ​ዓ​ልን ነቢ​ያት ያዙ፤ ከእ​ነ​ርሱ አንድ ሰው እን​ኳን የሚ​ያ​መ​ልጥ አይ​ኑር፤” አላ​ቸው። ያዙ​አ​ቸ​ውም፤ ኤል​ያ​ስም ወደ ቂሶን ወንዝ ወስዶ፥ በዚያ እየ​ወጋ ጣላ​ቸው።


ኢዩና የሬ​ካብ ልጅ ኢዮ​ና​ዳ​ብም ወደ በዓል ቤት ገቡ። የበ​ዓ​ል​ንም አገ​ል​ጋ​ዮች፥ “መር​ምሩ፥ ከበ​ዓል አገ​ል​ጋ​ዮች ብቻ በቀር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከሚ​ያ​መ​ልኩ ወገን በእ​ና​ንተ ዘንድ አንድ እንኳ እን​ዳ​ይ​ኖር ተመ​ል​ከቱ” አላ​ቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች