Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 10:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ኢዩም ወደ እስ​ራ​ኤል ሀገ​ሮች ሁሉ ላከ፤ የበ​ዓ​ልም አገ​ል​ጋ​ዮች ሁሉ፥ ካህ​ና​ቱም ሁሉ፥ ነቢ​ያ​ቶ​ቹም ሁሉ መጡ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ሳይ​መጣ የቀረ አንድ ሰው እንኳ አል​ነ​በ​ረም። ሁሉም ወደ በዓል ቤት ገቡ፤ የበ​ዓ​ል​ንም ቤት ከዳር እስከ ዳር ድረስ ሞሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ከዚያም ኢዩ በመላው እስራኤል መልእክት ላከ፤ የበኣል አገልጋዮች በሙሉ መጡ፤ ማንም አልቀረም፤ ሁሉም ወደ በኣል ቤተ ጣዖት ገቡ፤ የበኣል ቤተ ጣዖት ዳር እስከ ዳር ሞላ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ኢዩም በእስራኤል ምድር ሁሉ መልእክት አስተላለፈ፤ በዓልን የሚያመልኩ ሁሉ ተሰበሰቡ፤ አንድም እንኳ የቀረ ሰው አልነበረም፤ ሁሉም ወደ በዓል ቤተ መቅደስ ገብተው ዳር እስከ ዳር ሞሉት፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ኢዩም በእስራኤል ምድር ሁሉ መልእክት አስተላለፈ፤ ባዓልን የሚያመልኩ ሁሉ ተሰበሰቡ፤ አንድም እንኳ የቀረ ሰው አልነበረም፤ ሁሉም ወደ ባዓል ቤተ መቅደስ ገብተው ዳር እስከ ዳር ሞሉት፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ኢዩም ወደ እስራኤል ሁሉ ላከ፤ የበኣልም አገልጋዮች ሁሉ መጡ፤ ሳይመጣ የቀረ አንድ ስንኳ አልነበረም። ወደ በኣልም ቤት ገቡ፤ የበኣልም ቤት ከዳር እስከ ዳር ድረስ ሞልቶ ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 10:21
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በሰ​ማ​ር​ያም በሠ​ራው በበ​ዓል ቤት ውስጥ ለበ​ዓል መሠ​ዊ​ያን ሠራ።


በዕብራይስጥም አርማጌዶን ወደሚባል ስፍራ እስከተቱአቸው።


አሕ​ዛ​ብን ሁሉ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ወደ ኢዮ​ሳ​ፍ​ጥም ሸለቆ አወ​ር​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል በተ​በ​ተ​ኑ​በ​ትና ምድ​ሬን በተ​ካ​ፈ​ሉ​በት በዚያ ስለ ወገ​ኖች ስለ ርስቴ ስለ እስ​ራ​ኤል እወ​ቅ​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ።


የሀ​ገ​ሩም ሕዝብ ሁሉ ወደ በዓል ቤት ሄደው ሰበ​ሩት፤ መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም አፈ​ረሱ፤ ምስ​ሎ​ቹ​ንም አደ​ቀቁ፥ የበ​ዓ​ል​ንም ካህን ማታ​ንን በመ​ሠ​ዊ​ያው ፊት ገደ​ሉት። ካህኑ ዮዳ​ሄም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ጠባ​ቂ​ዎ​ችን ሾመ።


በቤ​ትም ውስጥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ሞል​ተ​ው​በት ነበር፤ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም መሳ​ፍ​ን​ትም ሁሉ በዚያ ነበሩ፤ በቤ​ቱም ሰገ​ነት ላይ ሶም​ሶን ሲጫ​ወት የሚ​ያዩ ሦስት ሺህ የሚ​ያ​ህሉ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ነበሩ።


የዕቃ ቤቱ​ንም ሹም፥ “ለበ​ዓል አገ​ል​ጋ​ዮች ሁሉ ልብ​ስን አውጣ” አለው። የሚ​ያ​ለ​ብ​ሳ​ቸ​ው​ንም ልብ​ሱን አወ​ጣ​ላ​ቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች