Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ቆሮንቶስ 4:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 በሕ​ይ​ወት የም​ን​ኖር እኛም በሟች ሰው​ነ​ታ​ችን ላይ የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ሕይ​ወቱ ይገ​ለጥ ዘንድ፥ ዘወ​ትር ስለ ኢየ​ሱስ ክስ​ር​ቶስ ብለን ተላ​ል​ፈን ለሞት እን​ሰ​ጣ​ለን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 የኢየሱስ ሕይወት ሟች በሆነው ሥጋችን እንዲገለጥ፣ እኛ ሕያዋን የሆንን ሁልጊዜ ስለ ኢየሱስ ለሞት ዐልፈን እንሰጣለንና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 የኢየሱስ ሕይወት ደግሞ በሚሞት ሥጋችን እንዲገለጥ፥ እኛ ሕያዋን የሆንን ስለ ኢየሱስ ስንል ዘወትር ለሞት አልፈን እንሰጣለን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 የኢየሱስ ሕይወት በሟች ሰውነታችን ይገለጥ ዘንድ እኛ ሕያዋኑ ስለ ኢየሱስ ሁልጊዜ ለሞት ተላልፈን እንሰጣለን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 የኢየሱስ ሕይወት ደግሞ በሚሞት ሥጋችን ይገለጥ ዘንድ እኛ ሕያዋን የሆንን ከኢየሱስ የተነሣ ዘወትር ለሞት አልፈን እንሰጣለንና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ቆሮንቶስ 4:11
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አቤቱ፥ ስም​ህን አመ​ሰ​ግን ዘንድ ሰው​ነ​ቴን ከእ​ሥ​ራት አው​ጣት፤ ዋጋ​ዬን እስ​ክ​ት​ሰ​ጠኝ ድረስ ጻድ​ቃን እኔን ይጠ​ብ​ቃሉ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ከሙ​ታን ለይቶ ያስ​ነ​ሣው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ካደ​ረ​ባ​ችሁ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ከሙ​ታን ለይቶ ያስ​ነ​ሣው እርሱ አድ​ሮ​ባ​ችሁ ባለ መን​ፈሱ ለሟች ሰው​ነ​ታ​ችሁ ሕይ​ወ​ትን ይሰ​ጣ​ታል።


መጽ​ሐፍ እን​ዳለ፥ “ስለ አንተ ዘወ​ትር ይገ​ድ​ሉ​ናል፤ እን​ደ​ሚ​ታ​ረዱ በጎ​ችም ሆነ​ናል።”


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በሆ​ነ​ውና በእ​ና​ንተ ላይ ባለኝ ትም​ክ​ህት ሁል​ጊዜ እገ​ደ​ላ​ለሁ።


የመ​ሬ​ታ​ዊ​ውን መልክ እንደ ለበ​ስን እን​ዲሁ የሰ​ማ​ያ​ዊ​ውን መልክ ደግሞ እን​ለ​ብ​ሳ​ለን።


የክ​ር​ስ​ቶስ ሕይ​ወቱ በዚህ በሟች ሰው​ነ​ታ​ችን ላይ ይገ​ለጥ ዘንድ፥ ዘወ​ትር የክ​ር​ስ​ቶ​ስን ሞት በሥ​ጋ​ችን እን​ሸ​ከ​ማ​ለን።


ስለ​ዚ​ህም ሞት በእኛ ላይ፥ ሕይ​ወ​ትም በእ​ና​ንተ ላይ ይሠ​ራል።


በዚህ ቤት ውስጥ ሳለ​ንም ከከ​ባ​ድ​ነቱ የተ​ነሣ እጅግ እና​ዝ​ና​ለን፤ ነገር ግን ሟች በሕ​ይ​ወት ይዋጥ ዘንድ ሌላ ልን​ለ​ብስ እንጂ ልን​ገ​ፈፍ አን​ወ​ድም።


እን​ደ​ማ​ይ​ታ​ወቁ ስን​ታይ የታ​ወ​ቅን ነን፤ እንደ ሰነ​ፎች ስን​ታ​ይም ልባ​ሞች ነን፤ እንደ ሙታን ስን​ታይ ሕያ​ዋን ነን፤ የተ​ቀ​ጣን ስን​ሆ​ንም አን​ገ​ደ​ልም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች