Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ቆሮንቶስ 2:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 የሞት መዓዛ የሚ​ገ​ባ​ቸው ለሞት፥ የሕ​ይ​ወት መዓዛ የሚ​ገ​ባ​ቸ​ውም ለሕ​ይ​ወት ናቸው፤ ነገር ግን ይህ የሚ​ገ​ባው ማነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ለሚጠፉት ወደ ሞት የሚወስድ የሞት ሽታ፣ ለሚድኑት ግን ወደ ሕይወት የሚወስድ የሕይወት ሽታ ነን፤ ታዲያ፣ ለዚህ ብቁ የሚሆን ማን ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ለእነዚህ ለሞት የሚሆን የሞት ሽታ፥ ለእነዚያም ለሕይወት የሚሆን የሕይወት ሽታ ነን። ለዚህም ነገር የሚበቃ ማን ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ለአንዱ የሚገድል የሞት ሽታ ነን፤ ለሌላው ሕይወትን የሚሰጥ የሕይወት መዓዛ ነን፤ ታዲያ፥ ለዚህ አገልግሎት ብቁ የሚሆን ማን ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ለእነዚህ ለሞት የሚሆን የሞት ሽታ ለእነዚያም ለሕይወት የሚሆን የሕይወት ሽታ ነን። ለዚህም ነገር የሚበቃ ማን ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ቆሮንቶስ 2:16
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በፈ​ቃ​ዳ​ች​ሁም ቢሆን በበ​ዓ​ላ​ች​ሁም ቢሆን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ ይሆን ዘንድ ስእ​ለ​ቱን አብ​ዝ​ታ​ችሁ በአ​መ​ጣ​ችሁ ጊዜ ከላም ወይም ከበግ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ወይም መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆን የእ​ሳት ቍር​ባን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቅ​ርቡ።


ስም​ዖ​ንም ባረ​ካ​ቸው፤ እና​ቱን ማር​ያ​ም​ንም እን​ዲህ አላት፤ “እነሆ፥ ይህ ሕፃን ከእ​ስ​ራ​ኤል መካ​ከል ለብ​ዙ​ዎች ለመ​ው​ደ​ቃ​ቸ​ውና ለመ​ነ​ሣ​ታ​ቸው፥ ለሚ​ቃ​ወ​ሙ​ትም ምል​ክት ይሆን ዘንድ የተ​ሠ​የመ ነው፤


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እኔ የማ​ያ​ዩት እን​ዲ​ያዩ፥ የሚ​ያ​ዩ​ትም እን​ዲ​ታ​ወሩ ወደ​ዚህ ዓለም ለፍ​ርድ መጥ​ቻ​ለሁ” አለው።


ነገር ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ አሁን እኔ ባለ​ሁ​በት አለሁ፤ ለእ​ኔም የሰ​ጠኝ ጸጋው ለከ​ንቱ የሆ​ነ​ብኝ አይ​ደ​ለም፤ እኔም ከሁሉ ይልቅ ደከ​ምሁ፤ ነገር ግን በእኔ ላይ ያደ​ረው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ አጸ​ናኝ እንጂ እኔ አይ​ደ​ለ​ሁም።


እነሆ እና​ንተ ስላ​ገ​በ​ራ​ች​ሁኝ በመ​መ​ካቴ ሰነፍ ሆንሁ፤ ለእ​ኔማ በእ​ና​ንተ ዘንድ ልከ​ብ​ርና እና​ን​ተም ምስ​ክ​ሮች ልት​ሆ​ኑኝ ይገ​ባኝ ነበር፤ እኔ እንደ ኢም​ንት ብሆ​ንም ዋና​ዎቹ ሐዋ​ር​ያት ሁሉ ከሠ​ሩት ሥራ ያጐ​ደ​ል​ሁ​ባ​ችሁ የለ​ምና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች