Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ቆሮንቶስ 10:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 እነ​ርሱ ራሳ​ቸ​ውን በአ​ሰ​ቡ​ትና በገ​መ​ገ​ሙት መጠን ራሳ​ቸ​ውን ከሚ​ያ​መ​ሰ​ግ​ኑት ሰዎች ጋር ራሳ​ች​ንን ልን​ቈ​ጥር፥ ወይም ራሳ​ች​ንን ልና​ስ​ተ​ያይ አን​ደ​ፍ​ርም፤ እነ​ርሱ ራሳ​ቸ​ውም የሚ​ና​ገ​ሩ​ትን ትር​ጕ​ሙን አያ​ው​ቁ​ትም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ራሳቸውን ከሚያመሰግኑ ሰዎች ጋራ ራሳችንን ልንመድብ ወይም ልናነጻጽር አንደፍርም፤ እነርሱ ራሳቸውን በራሳቸው ሲመዝኑና ራሳቸውንም ከራሳቸው ጋራ ሲያነጻጽሩ አስተዋዮች አይደሉም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ራሳቸውን ከሚያመሰግኑ ከአንዳንዶች ጋር ራሳችንን መቁጠር ወይም ራሳችንን ማስተያየት አንደፍርምና፤ ነገር ግን እነርሱ እርስ በራሳቸው ሲያመዛዝኑ፥ እርስ በራሳቸውም ሲተያዩ፥ አስተዋይ አይደሉም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ይሁን እንጂ ራሳቸውን ከሚያመሰግኑ ከአንዳንድ ሰዎች ጋር ራሳችንን ልናወዳድር ወይም ራሳችንን ልናነጻጽር አንደፍርም፤ እነርሱ ግን ራሳቸውን ከራሳቸው ጋር በማመዛዘናቸውና ራሳቸውንም ከራሳቸው ጋር በማወዳደራቸው አስተዋዮች አይደሉም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ራሳቸውን ከሚያመሰግኑ ከአንዳንዶች ጋር ራሳችንን ልንቆጥር ወይም ራሳችንን ልናስተያይ አንደፍርምና፤ ነገር ግን እነርሱ ራሳቸውን ከራሳቸው ጋር ሲያመዛዝኑ፥ ራሳቸውንም ከራሳቸው ጋር ሲያስተያዩ፥ አያስተውሉም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ቆሮንቶስ 10:12
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“በእ​ር​ግጥ እና​ንተ ዓይ​ነ​ተ​ኞች ሰዎች ናችሁ፤ ጥበ​ብም በእ​ና​ንተ ዘንድ ትፈ​ጸ​ማ​ለች።


ፈሪ​ሳ​ዊ​ውም ቆመና እን​ዲህ ብሎ ጸለየ፦ ‘አቤቱ እንደ ሌሎች ሰዎች፥ እንደ ቀማ​ኞ​ችና እንደ ዐመ​ፀ​ኞች፥ እንደ አመ​ን​ዝ​ሮ​ችም፥ ወይም እን​ደ​ዚህ ቀራጭ ያላ​ደ​ረ​ግ​ኸኝ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።


አሕ​ዛ​ብም እን​ዲ​ያ​ምኑ ክር​ስ​ቶስ በቃ​ልም በሥ​ራም ያደ​ረ​ገ​ል​ኝን እና​ገር ዘንድ እደ​ፍ​ራ​ለሁ።


ነገር ግን ይህን ነገር የሚ​ና​ገር ይህን ይወቅ፤ በሌ​ለ​ን​በት ጊዜ በመ​ል​እ​ክ​ታ​ችን እንደ ተገ​ለ​ጠው እንደ ቃላ​ችን፥ ባለ​ን​በ​ትም ጊዜ በሥ​ራ​ችን እን​ዲሁ ነን።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያከ​በ​ረው ብቻ ይከ​ብ​ራል እንጂ ራሱን የሚ​ያ​ከ​ብር የተ​መ​ረጠ አይ​ደ​ለም።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን አሁን ደግሞ ራሳ​ች​ንን እያ​መ​ሰ​ገን ልን​ነ​ግ​ራ​ችሁ እን​ጀ​ም​ራ​ለ​ንን? ወይስ እንደ ሌሎች ስለ እኛ ወደ እና​ንተ ደብ​ዳቤ እን​ዲ​ጽ​ፉ​ላ​ችሁ፥ ወይስ እና​ንተ ትጽ​ፉ​ልን ዘንድ የም​ን​ሻው አለን?


በዚህ ደግሞ በእ​ና​ንተ ዘንድ ራሳ​ች​ንን የም​ና​መ​ሰ​ግን አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን እኛ እን​ደ​ም​ን​መ​ካ​ባ​ችሁ፥ እና​ን​ተም በእኛ እን​ድ​ት​መኩ፥ ከልብ ሳይ​ሆን ለሰው ይም​ሰል በሚ​መኩ ሰዎች ዘንድ መልስ እን​ዲ​ሆ​ና​ችሁ ምክ​ን​ያ​ትን እን​ሰ​ጣ​ች​ኋ​ለን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች