Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 9:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ወጥ​ቤ​ቱም ወር​ቹን አም​ጥቶ በሳ​ኦል ፊት አኖ​ረው። ሳሙ​ኤ​ልም፥ “ሳኦ​ልን ለም​ስ​ክር ከባ​ል​ን​ጀ​ራህ ተለ​ይቶ ቀር​ቦ​ል​ሃ​ልና እነሆ፥ በል​ተህ የተ​ረ​ፈ​ህን በፊ​ትህ አኑር” አለው። በዚ​ያም ቀን ሳኦል ከሳ​ሙ​ኤል ጋር በላ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ወጥ ቤቱም የጭኑን ሥጋ እንዳለ አምጥቶ በሳኦል ፊት አስቀመጠው። ሳሙኤልም፣ “ይህ፣ ‘እንግዶችን ጋብዣለሁ’ ካልሁበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ተወሰነው ጊዜ ድረስ ለአንተ ተለይቶ የተቀመጠልህ ስለ ሆነ ብላው” አለው። ሳኦልም በዚያች ዕለት ከሳሙኤል ጋራ ዐብሮ በላ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ወጥ ቤቱም የጭኑን ሥጋ እንዳለ አምጥቶ በሳኦል ፊት አስቀመጠው። ሳሙኤልም፥ “ይህ፥ እንግዶችን ጋብዣለሁ ካልሁበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ተወሰነው ጊዜ ድረስ፥ ለአንተ ተለይቶ የተቀመጠልህ ስለሆነ ብላው” አለው። ሳኦልም በዚያች ዕለት ከሳሙኤል ጋር አብሮ በላ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ስለዚህም የወጥቤቱ ሠራተኛ ምርጥ የሆነውን የታናሽ ብልት ሥጋ አምጥቶ በሳኦል ፊት አስቀመጠ፤ ሳሙኤልም ሳኦልን “ተመልከት፤ ይህ ለአንተ ተለይቶ የተቀመጠልህ ምርጥ ሥጋ ነው፤ እኔ ከጋበዝኳቸው እንግዶች ጋር ሆነህ እንድትበላ ያስቀመጡልህ ስለ ሆነ እርሱን ተመገብ” አለው። ስለዚህም በዚያ ቀን ሳኦል ከሳሙኤል ጋር አብሮ ተመገበ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ወጥቤቱም ጭኑንና በእርሱ ላይ የነበረውን አምጥቶ በሳኦል ፊት አኖረው። ሳሙኤልም፦ ሕዝቡን ከጠራሁ ጀምሮ እስከ ተወሰነው ጊዜ ድረስ ለአንተ ተጠብቆአልና እነሆ፥ የተቀመጠልህን በፊትህ አኑረህ ብላው አለ። በዚያም ቀን ሳኦል ከሳሙኤል ጋር በላ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 9:24
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የበ​ጉ​ንም ስብ፥ የሆድ ዕቃ​ውን የሚ​ሸ​ፍ​ነ​ውን ስብ፥ በጉ​በ​ቱም ላይ ያለ​ውን መረብ፥ ሁለ​ቱ​ንም ኵላ​ሊ​ቶች፥ በላ​ያ​ቸ​ውም ላይ ያለ​ውን ስብ፥ የቀ​ኙ​ንም ወርች ትወ​ስ​ዳ​ለህ፤ የሚ​ቀ​ደ​ሱ​በት ነውና።


ከሚ​ካ​ኑ​በ​ትም አውራ በግ የተ​ወ​ሰደ ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ ወግ የሚ​ሆን ለመ​ሥ​ዋ​ዕት የተ​ለ​የ​ውን ፍር​ም​ባና የተ​ነ​ሣ​ውን ወርች ትቀ​ድ​ሳ​ለህ።


ቍራ​ጭ​ዋ​ንም፥ መል​ካ​ሙን ቍራጭ ሁሉ፥ ጭኑ​ንና ወር​ቹን በእ​ር​ስዋ ውስጥ ጨምር፤ የተ​መ​ረ​ጡ​ት​ንም አጥ​ን​ቶች ሙላ​ባት።


ሥጋ​ውም ለአ​ንተ ይሆ​ናል፤ እን​ደ​ሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት ፍር​ምባ እንደ ቀኙም ወርች ለአ​ንተ ይሆ​ናል።


ሳሙ​ኤ​ልም ወጥ ቤቱን፥ “በአ​ንተ ዘንድ አኑ​ረው ብዬ የሰ​ጠ​ሁ​ህን እድል ፋንታ አምጣ” አለው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች