Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 9:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ሳሙ​ኤ​ልም ሳኦ​ልን ባየ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “ያ የነ​ገ​ር​ሁህ ሰው እነሆ፤ እር​ሱም በሕ​ዝቤ ላይ ይነ​ግ​ሣል” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ሳሙኤል ሳኦልን ባየው ጊዜ እግዚአብሔር፣ “ያ የነገርሁህ ሰው እነሆ፤ እርሱም ሕዝቤን ይገዛል” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ሳሙኤል ሳኦልን ባየው ጊዜ ጌታ፥ “ያ የነገርሁህ ሰው እነሆ! እርሱም ሕዝቤን ይገዛል” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ሳሙኤልም ሳኦልን ባየው ጊዜ፥ እግዚአብሔር ሳሙኤልን “ያ የነገርኩህ ሰው እነሆ ይህ ነው፤ እርሱ ለሕዝቤ መሪ ይሆናል” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ሳሙኤልም ሳኦልን ባየ ጊዜ እግዚአብሔር፦ ያ የነገርሁህ ሰው እነሆ፥ እርሱም በሕዝቤ ላይ ይሠለጥናል አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 9:17
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከዚህ በኋላ ሰን​በት ከመ​ግ​ባቱ በፊት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በሮች ድን​ግ​ዝ​ግ​ዝታ በሆነ ጊዜ በሮ​ችዋ እን​ዲ​ዘጉ፥ ሰን​በ​ትም እስ​ኪ​ያ​ልፍ ድረስ እን​ዳ​ይ​ከ​ፈቱ አዘ​ዝሁ። በሰ​ን​በ​ትም ቀን ሸክም እን​ዳ​ይ​ገባ ከብ​ላ​ቴ​ኖች በዐ​ያ​ሌ​ዎቹ በሮ​ች​ዋን አስ​ጠ​በ​ቅሁ።


እነ​ር​ሱ​ንም ተቈ​ጣ​ኋ​ቸው፤ ረገ​ም​ኋ​ቸ​ውም፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ዐያ​ሌ​ዎ​ቹን መታሁ፤ ጠጕ​ራ​ቸ​ው​ንም ነጨሁ፤ እን​ዲ​ህም ብዬ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አማ​ል​ኋ​ቸው፥ “ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁን ለወ​ን​ዶች ልጆ​ቻ​ቸው አት​ስጡ፤ ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ለወ​ን​ዶች ልጆ​ቻ​ችሁ አት​ው​ሰዱ።


እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል የአ​ጎቴ ልጅ አና​ም​ኤል እኔ ወደ አለ​ሁ​በት ወደ ግዞቱ ቤት አደ​ባ​ባይ መጥቶ፥ “በብ​ን​ያም ሀገር በዓ​ና​ቶት ያለ​ውን እር​ሻ​ዬን ግዛ፤ የመ​ግ​ዛ​ትና የመ​ው​ረስ መብቱ የአ​ንተ ነውና፥ አንተ ታላ​ቃ​ችን ነህና፤ ለአ​ንተ ግዛው” አለኝ። ይህም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እንደ ሆነ ዐወ​ቅሁ።


በቍ​ጣዬ ንጉ​ሥን ሰጠ​ሁህ፤ በመ​ዓ​ቴም ሻር​ሁት።


ከዚ​ያም ወዲያ ንጉሥ ያነ​ግ​ሥ​ላ​ቸው ዘንድ ለመኑ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከብ​ን​ያም ነገድ የተ​ወ​ለ​ደ​ውን ሰው የቂ​ስን ልጅ ሳኦ​ልን አርባ ዓመት አነ​ገ​ሠ​ላ​ቸው።


ልጆቹ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ክፉ እን​ዳ​ደ​ረጉ ዐውቆ አል​ገ​ሠ​ጻ​ቸ​ው​ምና ስለ ልጆቹ ኀጢ​አት ለዘ​ለ​ዓ​ለም ቤቱን እን​ደ​ም​በ​ቀል አስ​ታ​ው​ቄ​ዋ​ለሁ።


ሳኦ​ልም በበሩ ወደ ሳሙ​ኤል ቀርቦ፥ “የባለ ራእዩ ቤት ወዴት እንደ ሆነ፥ እባ​ክህ፥ ንገ​ረኝ” አለው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች