Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 9:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ዳገት በወጡ ጊዜ ቈነ​ጃ​ጅት ውኃ ሊቀዱ ሲወጡ አገ​ኙና፥ “ባለ ራእይ በዚህ አለ ወይ?” አሉ​አ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 በከተማዪቱ መዳረሻ ያለውን ኰረብታ በመውጣት ላይ ሳሉ፣ ውሃ ለመቅዳት የሚወጡ ልጃገረዶችን አግኝተው፣ “ባለራእዩ እዚህ ነውን?” ሲሉ ጠየቁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 በከተማዪቱ መዳረሻ ያለውን ኰረብታ በመውጣት ላይ ሳሉ፥ ውሃ ለመቅዳት የሚወጡ ልጃገረዶችን አግኝተው፥ “ባለ ራእዩ እዚህ አለን?” ሲሉ ጠየቋቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 በዳገቱ አድርገው ወደ ከተማው ሲወጡ ውሃ ለመቅዳት የሚወጡ ልጃገረዶችን አግኝተው “ባለ ራእይ እዚህ አለን?” ብለው ጠየቁአቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 በከተማይቱም ዳገት በወጡ ጊዜ ቆነጃጅት ውኃውን ሊቀዱ ሲወጡ አገኙና፦ ባለ ራእይ በዚህ አለ ወይ? አሉአቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 9:11
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሲመ​ሽም ውኃ ቀጂ​ዎች ውኃ ሊቀዱ በሚ​መ​ጡ​በት ጊዜ ከከ​ተ​ማ​ዪቱ ውጪ በውኃ ጕድ​ጓድ አጠ​ገብ ግመ​ሎ​ቹን አሳ​ረፈ።


እን​ደ​ዚህ በልቡ ያሰ​በ​ውን መና​ገ​ሩን ሳይ​ፈ​ጽም እን​ዲህ ሆነ፦ የአ​ብ​ር​ሃም ወን​ድም የና​ኮር ሚስት የሚ​ልካ ልጅ የባ​ቱ​ኤል ሴት ልጅ ርብቃ እነሆ፥ መጣች፥ እን​ስ​ራ​ዋ​ንም በጫ​ን​ቃዋ ተሸ​ክማ ነበር።


እነ​ር​ሱም አሉ፥ “እረ​ኞች ሁሉ ካል​ተ​ሰ​በ​ሰ​ቡና ድን​ጋ​ዪ​ቱን ከጕ​ድ​ጓዱ አፍ ካላ​ነ​ሡ​አት በቀር አን​ች​ልም፤ ከዚ​ያም በኋላ በጎ​ቹን እና​ጠ​ጣ​ለን።”


እር​ሱም ገና ከእ​ነ​ርሱ ጋር ሲነ​ጋ​ገር እነሆ፥ የላባ ልጅ ራሔል የአ​ባ​ት​ዋን በጎች ይዛ ደረ​ሰች፤ እር​ስዋ የአ​ባ​ቷን በጎች ትጠ​ብቅ ነበ​ርና።


ለም​ድ​ያ​ምም ካህን ሰባት ሴቶች ልጆች ነበ​ሩት፤ የአ​ባ​ታ​ቸ​ው​ንም የዮ​ቶ​ርን በጎች ይጠ​ብቁ ነበር፤ እነ​ር​ሱም መጥ​ተው ውኃ ቀዱ፤ የአ​ባ​ታ​ቸ​ው​ንም የዮ​ቶ​ርን በጎች ሊያ​ጠጡ የው​ኃ​ዉን ገንዳ ሞሉ።


ኃጥኣንን ወደ ጻድቃን ቦታ አትውሰድ፤ በሆድህ ጥጋብም አትሳሳት፥


በብ​ዙ​ዎች ደስ​ተ​ኞች መካ​ከል መሰ​ን​ቆን ምቱ፤ በዚያ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጽ​ድቅ ሥራን፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ውስጥ ጽድ​ቅ​ንና ኀይ​ልን ያቀ​ር​ባሉ። ያን​ጊ​ዜም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ ወደ ከተ​ማ​ዎቹ ወረዱ።


ሳኦ​ልም ብላ​ቴ​ና​ውን፥ “የተ​ና​ገ​ር​ኸው ነገር መል​ካም ነው፤ ና፤ እን​ሂድ” አለ​ውና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ወዳ​ለ​በት ከተማ ሄዱ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች