Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 6:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 የኢ​ያ​ኮ​ንዩ ልጆ​ችም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳን ታቦት ተመ​ል​ክ​ተው ከቤ​ት​ሳ​ሚስ ሰዎች ጋር አል​ተ​ቀ​በ​ሉ​አ​ትም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሕ​ዝቡ አም​ስት ሺህ ሰባ ሰዎ​ችን መታ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሕዝ​ቡን በታ​ላቅ ግዳይ ስለ መታ ሕዝቡ አለ​ቀሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ነገር ግን እግዚአብሔር ከቤትሳሚስ ሰዎች ጥቂቱን መታ፤ ወደ እግዚአብሔር ታቦት ውስጥ ተመልክተዋልና ከመካከላቸው ሰባ ሰዎችን ገደለ፤ እግዚአብሔር እጅግ ስለ መታቸውም ሕዝቡ አለቀሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ጌታም ከቤትሼሜሽ ሰዎች ጥቂቱን መታ፤ ምክንያቱም ወደ ጌታ ታቦት ውስጥ በመመልከታቸው ነበር። ከመካከላቸው ሰባ ሰዎችን ገደለ፤ ጌታ እጅግ ስለ መታቸውም ሕዝቡ አለቀሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 የታቦቱን ውስጣዊ ክፍል በመመልከታቸው እግዚአብሔር ተቈጥቶ ከቤት ሼሜሽ ሰዎች መካከል ሰባ ሰዎችን ገደለ፤ እግዚአብሔርም ይህን ሁሉ እልቂት በመካከላቸው በማድረጉ የቤት ሼሜስ ሰዎች በማዘን አለቀሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ወደ እግዚአብሔርም ታቦት ውስጥ ተመልክተዋልና የቤትሳሚስን ሰዎች መታ፥ በሕዝቡም ከአምስት ሺህ ሰው ሰባ ሰዎችን መታ፥ እግዚአብሔርም ሕዝቡን በታላቅ ግዳይ ስለ መታ ሕዝቡ አለቀሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 6:19
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከእ​ነ​ርሱ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው ሥራ​ው​ንና ሸክ​ሙን ያዘ​ጋጁ፤ ነገር ግን እን​ዳ​ይ​ሞቱ ንዋየ ቅዱ​ሳ​ቱን ለድ​ን​ገት እን​ኳን ለማ​የት አይ​ግቡ።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “ውረድ፤ ይህ​ንም ለመ​ረ​ዳት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ይ​ቀ​ርቡ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ብዙ እን​ዳ​ይ​ጠፉ ለሕ​ዝቡ አስ​ጠ​ን​ቅ​ቃ​ቸው፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዖዛ ላይ ተቈጣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዚ​ያው ቀሠ​ፈው። በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት አጠ​ገብ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በዚ​ያው ሞተ።


አሮ​ንና ልጆቹ መቅ​ደ​ሱ​ንና የመ​ቅ​ደ​ሱን ዕቃ ሁሉ ሸፍ​ነው ከጨ​ረሱ በኋላ ሰፈሩ ሲነሣ የቀ​ዓት ልጆች ሊሸ​ከ​ሙት ይገ​ባሉ። እን​ዳ​ይ​ሞቱ ግን ንዋየ ቅድ​ሳ​ቱን አይ​ንኩ። በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዘንድ የቀ​ዓት ልጆች ሸክም ይህ ነው።


በመ​ታ​ለ​ልና ራስን ዝቅ በማ​ድ​ረግ ለመ​ላ​እ​ክት አም​ልኮ ትታ​ዘዙ ዘንድ ወድዶ፥ በአ​ላ​የ​ውም በከ​ንቱ የሥ​ጋው ምክር እየ​ተ​መካ የሚ​ያ​ሰ​ን​ፋ​ችሁ አይ​ኑር።


ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት ተነሥቶ የሚጀመርበት ጊዜ ደርሶአልና፤ አስቀድሞም በእኛ የሚጀመር ከሆነ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ መጨረሻቸው ምን ይሆን?


“ምስ​ጢሩ ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ የተ​ገ​ለ​ጠው ግን የዚ​ህን ሕግ ቃሎች ሁሉ እና​ደ​ርግ ዘንድ ለእ​ኛና ለል​ጆ​ቻ​ችን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነው።


ሕዝ​ቡም ይህን ክፉ ወሬ ሰም​ተው ታላቅ ኀዘን አዘኑ፤


ድን​ኳ​ን​ዋም ስት​ነሣ ሌዋ​ው​ያን ይን​ቀ​ሉ​አት፤ ድን​ኳ​ን​ዋም ስታ​ርፍ ሌዋ​ው​ያን ይት​ከ​ሉ​አት፤ ሌላ ሰው ግን ለመ​ን​ካት ቢቀ​ርብ ይገ​ደል።


“የቀ​ዓ​ትን ወገ​ኖች ነገድ ከሌ​ዋ​ው​ያን መካ​ከል አታ​ጥ​ፉ​አ​ቸው፤


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ኢዮ​አስ ወጣ፤ እር​ሱና የይ​ሁዳ ንጉሥ አሜ​ስ​ያ​ስም በይ​ሁዳ ባለች በቤ​ት​ሳ​ሚስ ላይ እርስ በር​ሳ​ቸው ተያዩ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች