Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 5:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 የአ​ዛ​ጦ​ንም ሰዎች እን​ዲህ እንደ ሆነ ባዩ ጊዜ፥ “እጁ በእ​ኛና በአ​ም​ላ​ካ​ችን በዳ​ጎን ላይ ጠን​ክ​ራ​ለ​ችና የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ታቦት ከእኛ ዘንድ አት​ቀ​መጥ” አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 የአሽዶድ ሰዎች ይህን ባዩ ጊዜ፣ “እጁ በእኛና በአምላካችን በዳጎን ላይ ጠንክሯልና የእስራኤል አምላክ ታቦት በእኛ ዘንድ መቈየት የለበትም” አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 የአሽዶድ ሰዎች ይህን ባዩ ጊዜ፥ “እጁ በእኛና በአምላካችን በዳጎን ላይ ጠንክሯልና የእስራኤል አምላክ ታቦት በእኛ ዘንድ መቆየት የለበትም” አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 የአሽዶድ ኗሪዎች የሆነውን ነገር ሁሉ ባዩ ጊዜ “ቊጣው በእኛና በአምላካችን በዳጎን ላይ ስለ በረታ የእስራኤል አምላክ ታቦት እዚህ እኛ ዘንድ መቈየት የለበትም” አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 የአዛጦንም ሰዎች እንዲህ እንደ ሆነ ባዩ ጊዜ፦ እጁ በእኛና በአምላካችን በዳጎን ላይ ጠንክራለችና የእስራኤል አምላክ ታቦት ከእኛ ዘንድ አይቀመጥ አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 5:7
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዚ​ያም ቀን ዳዊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈራና፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ወደ እኔ እን​ዴት ትገ​ባ​ለች?” አለ።


በቀ​ድሞ ሥራ​ችን አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርስ በር​ሳ​ችን አላ​ጠ​ፋ​ንም፤ በጦ​ር አል​ፈ​ለ​ገ​ን​ምና” አላ​ቸው።


የፈ​ር​ዖ​ንም ሹሞች፥ “ይህ ሰው እስከ መቼ እን​ቅ​ፋት ይሆ​ን​ብ​ናል? አም​ላ​ካ​ቸ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ል​ኩት ዘንድ ሰዎ​ችን ልቀቅ፤ ግብ​ፅስ እንደ ጠፋች ገና አታ​ው​ቅ​ምን?” አሉት።


ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም ፈጥ​ነው ከም​ድሩ ይወጡ ዘንድ ሕዝ​ቡን ያስ​ቸ​ኩ​ሉ​አ​ቸው ነበር፥ “ሁላ​ች​ንም እን​ሞ​ታ​ለን” ብለ​ዋ​ልና።


ፈር​ዖ​ንም፥ “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በም​ድረ በዳ ትሠዉ ዘንድ እለ​ቅ​ቃ​ች​ኋ​ለሁ፤ ነገር ግን በጣም ርቃ​ችሁ አት​ሂዱ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጸል​ዩ​ልኝ” አለ።


ፈር​ዖ​ንም ሙሴ​ንና አሮ​ንን ጠርቶ፥ “ጓጕ​ን​ቸ​ሮ​ቹን ከእኔ፥ ከሕ​ዝ​ቤም እን​ዲ​ያ​ርቅ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸል​ዩ​ልኝ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይሠዋ ዘንድ ሕዝ​ቡን እለ​ቅ​ቃ​ለሁ” አላ​ቸው።


እን​ግ​ዲህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸል​ዩ​ልኝ፤ የአ​ም​ላክ ነጐ​ድ​ጓድ፥ በረ​ዶ​ውም፥ እሳ​ቱም ጸጥ ይላል፤ እኔም እለ​ቅ​ቃ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከዚ​ያም በኋላ ከዚህ አት​ቀ​መ​ጡም” አላ​ቸው።


የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ የኖእ አሞ​ንን፥ ፈር​ዖ​ን​ንም፥ ግብ​ጽ​ንም፥ አማ​ል​ክ​ቶ​ች​ዋ​ንና ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ች​ዋ​ንም፥ ፈር​ዖ​ን​ንና በእ​ር​ሱም የሚ​ታ​መ​ኑ​ትን እቀ​ጣ​ለሁ።


በሥ​ራ​ሽና በመ​ዝ​ገ​ብሽ ታም​ነ​ሻ​ልና አንቺ ደግሞ ትያ​ዢ​ያ​ለሽ፤ ካሞ​ሽም ከካ​ህ​ና​ቱና ከአ​ለ​ቆቹ ጋር በአ​ን​ድ​ነት ይማ​ረ​ካል።


ወዮ​ልን! ከእ​ነ​ዚህ ኀያ​ላን አማ​ል​ክት እጅ ማን ያድ​ነ​ናል? እነ​ዚህ አማ​ል​ክት ግብ​ፃ​ው​ያ​ንን በም​ድረ በዳ በልዩ ልዩ መቅ​ሠ​ፍት የመቱ ናቸው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅ በአ​ዛ​ጦን ሰዎች ላይ ከበ​ደች፤ ክፉም ነገር አመ​ጣ​ች​ባ​ቸው፤ በእ​ነ​ር​ሱም ላይ በመ​ር​ከ​ቦች ውስጥ ወጣ፤ የአ​ዛ​ጦ​ን​ንና የአ​ው​ራ​ጃ​ዎ​ች​ዋ​ንም ሰዎች የው​ስጥ አካ​ላ​ቸ​ውን በዕ​ባጭ መታ፤ በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም መካ​ከል አይ​ጦች ወጡ፤ በከ​ተ​ማ​ውም ታላቅ መቅ​ሠ​ፍት ሆነ።


ልከ​ውም የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን አለ​ቆች ወደ እነ​ርሱ ሰበ​ሰ​ቡና፥ “በእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ታቦት ምን እና​ድ​ርግ?” አሉ፤ የጌት ሰዎ​ችም፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ታቦት ወደ እኛ ትዙር” ብለው መለሱ። የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ታቦ​ትም ወደ ጌት ሄደች።


የቤ​ት​ሳ​ሚ​ስም ሰዎች፥ “በዚህ በቅ​ዱሱ አም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ማለፍ ማን ይች​ላል? የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ከእኛ ወጥታ ወደ ማን ትሄ​ዳ​ለች?” አሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች