Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 4:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት ባሰ​ባት ጊዜ በበሩ አጠ​ገብ ካለው ከወ​ን​በሩ ወደቀ፤ እርሱ ሸም​ግሎ፥ ደን​ግ​ዞም ነበ​ርና ጀር​ባው ተሰ​ብሮ ሞተ። እር​ሱም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አርባ ዓመት ፈራጅ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ሰውየው ስለ እግዚአብሔር ታቦት በተናገረ ጊዜ፣ ዔሊ በቅጥሩ በር አጠገብ ከተቀመጠበት ወንበር ላይ በጀርባው ወደቀ፤ እርሱም ያረጀና ሰውነቱም የሚከብድ ስለ ነበር፣ ዐንገቱ ተሰብሮ ሞተ። እርሱም ለአርባ ዓመት በእስራኤል ላይ ፈራጅ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ሰውየው ስለ እግዚአብሔር ታቦት በተናገረ ጊዜ፥ ዔሊ በቅጥሩ በር አጠገብ ከተቀመጠበት ወንበር ላይ በጀርባው ወደቀ፤ እርሱም ያረጀና ሰውነቱም የሚከብድ ስለ ነበር፥ ዐንገቱ ተሰብሮ ሞተ። እርሱ ለአርባ ዓመት በእስራኤል ላይ ፈራጅ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ወሬ ነጋሪው የቃል ኪዳኑን ታቦት መማረክ ባወሳ ጊዜ ዔሊ በቅጽሩ በር አጠገብ ከተቀመጠበት ወንበር ላይ ተገልብጦ ወደ ኋላው ወደቀ፤ እርሱም ሽማግሌ ከመሆኑም በላይ በውፍረቱ ግዙፍ ስለ ነበር ከአወዳደቁ የተነሣ አንገቱ ተሰብሮ ሞተ፤ ዔሊም በእስራኤል መሪ ሆኖ የቈየበት ዘመን አርባ ዓመት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ሰውዮውም ስለ እግዚአብሔር ታቦት በተናገረ ጊዜ ዔሊ በበሩ አጠገብ ካለው ከወንበሩ ወደቀ፥ እርሱ ሸምግሎ ደንግዞም ነበርና አንገቱ ተሰብሮ ሞተ። እርሱም በእስራኤል ላይ አርባ ዓመት ፈራጅ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 4:18
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ልቤ አን​ተን አለ፦ ፊት​ህን ፈለ​ግሁ፥ አቤቱ፥ ፊት​ህን እሻ​ለሁ።


ብር​ሃ​ን​ህ​ንና ጽድ​ቅ​ህን ላክ፤ እነ​ር​ሱም ይም​ሩኝ፥ አቤቱ ወደ መቅ​ደ​ስህ ተራ​ራና ወደ ማደ​ሪ​ያህ ይው​ሰ​ዱኝ።


ሙሴም አሮ​ንን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ ወደ እኔ በሚ​ቀ​ርቡ እመ​ሰ​ገ​ና​ለሁ፤ በሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ፊት እከ​ብ​ራ​ለሁ ብሎ የተ​ና​ገ​ረው ይህ ነው” አለው፤ አሮ​ንም ደነ​ገጠ።


በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ዘመን እስ​ራ​ኤ​ልን ሃያ ዓመት ገዛ​ቸው።


በመ​ጣም ጊዜ ዔሊ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ልቡ ተና​ውጦ ነበ​ርና በመ​ን​ገድ ዳር በወ​ን​በሩ ላይ ተቀ​ምጦ ይጠ​ባ​በቅ ነበር፤ ሰው​ዬ​ውም ወደ ከተ​ማ​ዪቱ ገብቶ ባወራ ጊዜ ከተ​ማ​ዪቱ ሁሉ ተጭ​ዋ​ጭ​ዋ​ኸች።


ያም ሰው መልሶ፥ “እስ​ራ​ኤል ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ፊት ሸሹ፤ ደግ​ሞም በሕ​ዝቡ ዘንድ ታላቅ ግድያ ሆኖ​አል፥ ሁለ​ቱም ልጆ​ችህ አፍ​ኒ​ንና ፊን​ሐስ ሞተ​ዋል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት ተማ​ር​ካ​ለች” አለው።


ምራ​ቱም የፊ​ን​ሐስ ሚስት አር​ግዛ ልት​ወ​ልድ ተቃ​ርባ ነበር፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት እንደ ተማ​ረ​ከች፥ አማ​ቷና ባል​ዋም እንደ ሞቱ በሰ​ማች ጊዜ አለ​ቀ​ሰች፤ ከዚ​ያም በኋላ ወለ​ደች። ሕማ​ም​ዋም ተመ​ለ​ሰ​ባት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች