Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 4:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ያም ሰው መልሶ፥ “እስ​ራ​ኤል ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ፊት ሸሹ፤ ደግ​ሞም በሕ​ዝቡ ዘንድ ታላቅ ግድያ ሆኖ​አል፥ ሁለ​ቱም ልጆ​ችህ አፍ​ኒ​ንና ፊን​ሐስ ሞተ​ዋል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት ተማ​ር​ካ​ለች” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ወሬውን ያመጣውም ሰው፣ “እስራኤል ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፤ ሰራዊቱም ከፍተኛ ዕልቂት ደርሶበታል፤ እንዲሁም ሁለቱ ልጆችህ አፍኒንና ፊንሐስ ሞተዋል፤ የእግዚአብሔርም የኪዳኑ ታቦት ተማርኳል” ብሎ መለሰለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ወሬውን ያመጣውም ሰው፥ “እስራኤል ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፤ ሠራዊቱም ከፍተኛ እልቂት ደርሶበታል፤ እንዲሁም ሁለቱ ልጆችህ ሖፍኒና ፊንሐስ ሞተዋል፤ የእግዚአብሔርም የኪዳኑ ታቦት ተማርኳል” ብሎ መለሰለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ወሬ ነጋሪውም “እስራኤላውያን ድል ሆነው ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፤ ይህም ሽንፈት በእኛ ላይ መድረሱ እጅግ አሠቃቂ ነው፤ ከዚህም ሁሉ ጋር ልጆችህ ሖፍኒና ፊንሐስ ተገደሉ፤ የእግዚአብሔርም የቃል ኪዳን ታቦት ተማረከች” ሲል መለሰለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ወሬኛውም መልሶ፦ እስራኤል ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፥ ደግሞ በሕዝቡ ዘንድ ታላቅ ግድያ ሆኖአል፥ ሁለቱም ልጆችህ አፍኒንና ፊንሐስ ሞተዋል፥ የእግዚአብሔርም ታቦት ተማርካለች አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 4:17
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ይህ በሁ​ለቱ ልጆ​ችህ በአ​ፍ​ኒ​ንና በፊ​ን​ሐስ ላይ የሚ​መጣ ለአ​ንተ ምል​ክት ነው፤ ሁለቱ በአ​ንድ ቀን በጦር ይሞ​ታሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሳሙ​ኤ​ልን አለው፥ “እነሆ የሰ​ማ​ውን ሁሉ ሁለ​ቱን ጆሮ​ዎ​ቹን ጭው የሚ​ያ​ደ​ርግ ነገ​ሬን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አደ​ር​ጋ​ለሁ።


በዚ​ያም ቀን በቤቱ ላይ የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ትን ሁሉ በዔሊ ላይ አጸ​ና​ለሁ፤ እኔም ጀምሬ እፈ​ጽ​ም​በ​ታ​ለሁ።


ሰው​ዬ​ው​ንም፥ “አንተ ከወ​ዴት ነህ?” አለው። እር​ሱም፥ “ጦር​ነቱ ከአ​ለ​በት ስፍራ የመ​ጣሁ እኔ ነኝ፥ ዛሬም ከሰ​ልፍ ሸሸሁ” አለ። እር​ሱም፥ “ልጄ ሆይ! ነገ​ሩስ እን​ዴት ሆነ?” አለው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት ባሰ​ባት ጊዜ በበሩ አጠ​ገብ ካለው ከወ​ን​በሩ ወደቀ፤ እርሱ ሸም​ግሎ፥ ደን​ግ​ዞም ነበ​ርና ጀር​ባው ተሰ​ብሮ ሞተ። እር​ሱም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አርባ ዓመት ፈራጅ ነበረ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች