Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 3:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ስለ​ዚ​ህም የዔሊ ቤት ኀጢ​አት በዕ​ጣ​ንና በመ​ሥ​ዋ​ዕት ለዘ​ለ​ዓ​ለም እን​ዳ​ይ​ሰ​ረ​ይ​ለት ለዔሊ ቤት ምያ​ለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ስለዚህ ‘የዔሊ ቤት በደል በመሥዋዕትም ሆነ በቍርባን ፈጽሞ አይሰረይም’ ብዬ በዔሊ ቤት ላይ ምያለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ስለዚህ ‘የዔሊ ቤት በደል በመሥዋዕትም ሆነ በቁርባን ፈጽሞ አይሰረይም’ ብዬ በዔሊ ቤት ላይ ምያለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ስለዚህ የዔሊ ቤተሰብ ኃጢአት በመሥዋዕትም ሆነ በቊርባን ለዘለዓለም አይሰረይም ብዬ በመሐላ ተናግሬአለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ስለዚህም የዔሊ ቤት ኃጢአት በመሥዋዕትና በቍርባን ለዘላለም እንዳይሰረይለት ለዔሊ ቤት ምያለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 3:14
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ይህም ነገር በሠ​ራ​ዊት ጌታ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጆሮ ተሰማ፥ “እስ​ክ​ት​ሞቱ ድረስ ይህ በደል በእ​ው​ነት አይ​ሰ​ረ​ይ​ላ​ች​ሁም” ይላል የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለኝ፥ “ሙሴና ሳሙ​ኤል በፊቴ ቢቆ​ሙም፥ ልቤ ወደ​ዚህ ሕዝብ አያ​ዘ​ነ​ብ​ልም፤ እነ​ዚ​ህን ሕዝ​ቦች ከፊቴ አባ​ር​ራ​ቸው፤ ይውጡ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፥ “ስለ​ዚህ ሕዝብ አንተ አት​ጸ​ልይ፤ ይቅር እላ​ቸው ዘንድ አት​ማ​ል​ደኝ፤ የእ​ነ​ር​ሱን ነገር አል​ሰ​ማ​ህ​ምና ትለ​ም​ን​ላ​ቸው ዘንድ ወደ እኔ አት​ምጣ።”


በር​ኵ​ሰ​ትሽ ሴሰ​ኝ​ነት አለ፤ አነ​ጻ​ሁሽ፤ አል​ነ​ጻ​ሽ​ምና መዓ​ቴን በላ​ይሽ እስ​ክ​ጨ​ርስ ድረስ እን​ግ​ዲህ ከር​ኵ​ሰ​ትሽ አት​ነ​ጺም።


“እን​ዲ​ሁም በእ​ነ​ርሱ መካ​ከል ያለ​ች​ውን ድን​ኳ​ኔን ባረ​ከሱ ጊዜ፥ በር​ኩ​ስ​ነ​ታ​ቸው እን​ዳ​ይ​ሞቱ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከር​ኩ​ስ​ነ​ታ​ቸው አን​ጹ​አ​ቸው።


ሰውስ ሰውን ቢበ​ድል ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጸ​ል​ዩ​ለ​ታል፤ ሰው ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቢበ​ድል ስለ እርሱ ወደ ማን ይጸ​ል​ዩ​ለ​ታል?” እነ​ርሱ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊያ​ጠ​ፋ​ቸው ወድ​ዶ​አ​ልና የአ​ባ​ታ​ቸ​ውን ቃል አል​ሰ​ሙም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች