Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 3:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሳሙ​ኤ​ልን አለው፥ “እነሆ የሰ​ማ​ውን ሁሉ ሁለ​ቱን ጆሮ​ዎ​ቹን ጭው የሚ​ያ​ደ​ርግ ነገ​ሬን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አደ​ር​ጋ​ለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 እግዚአብሔርም ሳሙኤልን እንዲህ አለው፤ “እነሆ፤ የሰሚውን ሁሉ ጆሮ ጭው የሚያደርግ አንድ ነገር በእስራኤል ላይ አደርጋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ጌታም ሳሙኤልን እንዲህ አለው፤ “እነሆ፤ የሰሚውን ጆሮ ሁሉ ዝግንን የሚያደርግ አንድ ነገር በእስራኤል ላይ አደርጋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እግዚአብሔር እንዲህ አለው፦ “እነሆ እኔ በእስራኤል ላይ አንድ ነገር የማደርግበት ቀን ተቃርቦአል፤ ያን ነገር በጆሮው የሚሰማው ሁሉ ይዘገንነዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እግዚአብሔርም ሳሙኤልን አለው፦ እነሆ፥ የሰማውን ሁሉ ሁለቱ ጆሮቹ ጭው የሚያደርግ አንድ ነገርን በእስራኤል አደርጋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 3:11
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እናንተ የምትንቁ ሆይ፥ አንድ ቢተርክላችሁ ስንኳ የማታምኑትን ሥራ በዘመናችሁ እሠራለሁና እዩ፥ ተመልከቱ፥ ተደነቁ።


‘እነሆ፥ እና​ንተ የም​ታ​ቃ​ልሉ፥ እዩ፤ ተደ​ነ​ቁም፤ ያለ​ዚያ ግን ትጠ​ፋ​ላ​ችሁ፤ ማንም ቢነ​ግ​ራ​ችሁ የማ​ታ​ም​ኑ​ትን ሥራ እኔ በዘ​መ​ና​ችሁ እሠ​ራ​ለ​ሁና።’ ”


“የይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታ​ትና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የም​ት​ኖሩ ሆይ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ በዚህ ስፍራ ክፉ ነገ​ርን አመ​ጣ​ለሁ፤ የሰ​ማ​ውም ሰው ሁሉ ይደ​ነ​ግ​ጣል፤ ጆሮ​ዎ​ቹ​ንም ይይ​ዛል።


ስለ​ዚህ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የሚ​ሰ​ማ​ውን ሁሉ ሁለቱ ጆሮ​ቹን ጭው የሚ​ያ​ደ​ርግ ክፉ ነገ​ርን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና በይ​ሁዳ ላይ አመ​ጣ​ለሁ።


በዓ​ለም ላይ ከሚ​መ​ጣው ፍር​ሀ​ትና ሽብር የተ​ነ​ሣም የሰ​ዎች ነፍስ ትዝ​ላ​ለች፤ ያን​ጊዜ የሰ​ማ​ያት ኀይል ይና​ወ​ጣ​ልና።


ስለ​ዚህ፥ እነሆ፥ ይህ ሕዝብ በድ​ጋሚ እን​ዲ​ፈ​ልስ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ አፈ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለ​ሁም፤ የጥ​በ​በ​ኞ​ች​ንም ጥበብ አጠ​ፋ​ለሁ፤ የአ​ስ​ተ​ዋ​ዮ​ች​ንም ማስ​ተ​ዋል እሰ​ው​ራ​ለሁ።”


ባለ​ፈም ጊዜ ይወ​ስ​ዳ​ች​ኋል፤ ማለዳ ማለዳ በቀን ያል​ፋል፤ በሌ​ሊት ክፉ ተስፋ ይሆ​ናል፤ እና​ንተ ያዘ​ና​ችሁ፥ መስ​ማ​ትን ተማሩ።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መጥቶ ቆመ፤ እንደ ቀድ​ሞ​ውም ጠራው። ሳሙ​ኤ​ልም፥ “ባሪ​ያህ ይሰ​ማ​ልና ተና​ገር” አለ።


ከዚ​ህም በኋላ ተዋ​ጉ​አ​ቸው፤ እስ​ራ​ኤ​ልም በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ፊት ወደቁ፤ ሁሉም እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ወደ ድን​ኳ​ና​ቸው ሸሹ፤ እጅ​ግም ታላቅ ግድያ ሆነ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሠላሳ ሺህ እግ​ረ​ኞች ወደቁ።


እን​ጥ​ሽ​ታው ብል​ጭ​ታን ያወ​ጣል፥ ዐይ​ኖ​ቹም እንደ አጥ​ቢያ ኮከብ ናቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች