Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 28:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ሳኦ​ልም መል​ኩን ለውጦ፥ ሌላ ልብ​ስም ለብሶ ሄደ፤ ሁለ​ትም ሰዎች ከእ​ርሱ ጋር ነበሩ፤ በሌ​ሊ​ትም ወደ ሴቲቱ መጡ። ሳኦ​ልም፥ “እባ​ክሽ በመ​ና​ፍ​ስት አም​ዋ​ር​ቺ​ልኝ፤ የም​ል​ሽ​ንም አስ​ነ​ሽ​ልኝ” አላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ስለዚህ ሳኦል ሌላ ልብስ በመልበስ መልኩን ለውጦ ከሁለት ሰዎች ጋራ በሌሊት ወደ ሴቲቱ ሄደ። እርሱም፣ “እባክሽ፣ ጠንቍዪልኝ፤ የምነግርሽንም ሰው አስነሺልኝ” አላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ስለዚህ ሳኦል ሌላ ልብስ በመልበስ መልኩን ለውጦ ከሁለት ሰዎች ጋር በሌሊት ወደ ሴቲቱ ሄደ። እርሱም፥ “እባክሽ፥ መናፍስትን ጠይቂልኝ፤ የምነግርሽንም ሰው አስነሺልኝ” አላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ሳኦልም ልብሱን ለውጦ ማንነቱ እንዳይታወቅ በማድረግ በሌሊት ሁለት ሰዎች አስከትሎ ሴትዮዋን ለማየት ሄደ፤ እዚያም እንደ ደረሰ “መናፍስትን ጠይቀሽ ወደ ፊት ስለሚሆነው ነገር አስረጂኝ፤ ስሙንም የምጠራልሽን ሰው አስነሽልኝ” አላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ሳኦልም መልኩን ለውጦ ሌላ ልብስም ለብሶ ሄደ፥ ሁለትም ሰዎች ከእርሱ ጋር ነበሩ፥ በሌሊትም ወደ ሴቲቱ መጡ። እርሱም፦ እባክሽ፥ በመናፍስት አምዋርቺልኝ፥ የምልሽንም አስነሽልኝ አላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 28:8
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነ​ር​ሱም፥ “ድም​ፃ​ቸ​ውን ዝቅ አድ​ር​ገው የሚ​ና​ገ​ሩ​ትን መና​ፍ​ስት ጠሪ​ዎ​ች​ንና ጠን​ቋ​ዮ​ችን ጠይቁ” ባሉ​አ​ችሁ ጊዜ፥ ሕዝቡ ከአ​ም​ላኩ መጠ​የቅ አይ​ገ​ባ​ው​ምን? ወይስ ለሕ​ያ​ዋን ሲሉ ሙታ​ንን ይጠ​ይ​ቃ​ሉን?


እን​ዲሁ ሳኦል በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ስላ​ደ​ረ​ገው ኀጢ​አት፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዳ​ዘ​ዘው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስላ​ል​ጠ​በቀ ሞተ። ደግ​ሞም መና​ፍ​ስት ጠሪን ጠየቀ።


ኢዮ​ስ​ያስ ግን ይዋ​ጋው ዘንድ ተጽ​ናና እንጂ ፊቱን ከእ​ርሱ አል​መ​ለ​ሰም፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አፍ የተ​ነ​ገ​ረ​ውን የኒ​ካ​ዑን ቃል አል​ሰ​ማም፤ በመ​ጊ​ዶ​ንም ሸለቆ ይዋጋ ዘንድ መጣ።


የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉ​ሥም ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን፥ “ልብ​ሴን ለውጬ ወደ ጦር​ነት እገ​ባ​ለሁ፤ አንተ ግን የእ​ኔን ልብስ ልበስ” አለው። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ልብ​ሱን ለወጠ፤ ወደ ሰል​ፍም ገባ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን፥ “ልብ​ሴን ለውጬ ወደ ሰልፍ እገ​ባ​ለሁ፤ አንተ ግን የእ​ኔን ልብስ ልበስ” አለው። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ልብ​ሱን ለውጦ ወደ ሰልፍ ገባ።


ፍር​ዱም ይህ ነው፤ ብር​ሃን ወደ ዓለም መጥ​ቶ​አ​ልና፤ ሰውም ሥራው ክፉ ስለ​ሆነ ከብ​ር​ሃን ይልቅ ጨለ​ማን መር​ጦ​አ​ልና።


ሰው በስ​ውር ቦታ ቢሸ​ሸግ፥ እኔ አላ​የ​ው​ምን? ሰማ​ይ​ንና ምድ​ር​ንስ የሞ​ላሁ እኔ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


አንድ ሰውም ቀስ​ቱን ድን​ገት ገትሮ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ በሳ​ን​ባ​ውና በደ​ረቱ መካ​ከል ወጋው፤ ሰረ​ገ​ለ​ኛ​ው​ንም፥ “መል​ሰህ ንዳ፤ ተወ​ግ​ቻ​ለ​ሁና ከሰ​ልፍ ውስጥ አው​ጣኝ” አለው።


ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ምል​ክት አድ​ር​ጌ​ሃ​ለ​ሁና በፊ​ታ​ቸው ዕቃ​ህን በት​ከ​ሻህ ላይ አን​ግ​ተው፤ በጨ​ለ​ማም ተሸ​ክ​መህ ውጣ፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም እን​ዳ​ታይ ፊት​ህን ሸፍን።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች