Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 28:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ሳኦ​ልም ብላ​ቴ​ኖ​ቹን፥ “ወደ እር​ስዋ ሄጄ እጠ​ይቅ ዘንድ መና​ፍ​ስ​ትን የም​ት​ጠራ ሴት ፈል​ጉ​ልኝ” አላ​ቸው፤ ብላ​ቴ​ኖ​ቹም፥ “እነሆ፥ መና​ፍ​ስ​ትን የም​ት​ጠራ አን​ዲት ሴት በዓ​ይ​ን​ዶር አለች” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ሳኦልም አገልጋዮቹን፣ “እስኪ ሙታን ሳቢ ሴት ፈልጉልኝና ሄጄ ልጠይቃት” አላቸው። እነርሱም፣ “እነሆ፤ ሙታን የምትስብ ሴት በዓይንዶር አለች” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ሳኦልም አገልጋዮቹን፥ “እስቲ ሙታን ጠሪ ሴት ፈልጉልኝና ሄጄ ልጠይቃት” አላቸው። እነርሱም፥ “እነሆ፤ ሙታን የምትጠራ ሴት በዔንዶር አለች” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ከዚህ በኋላ ሳኦል “ሙታን ጠሪ የሆነች አንዲት ሴት ፈልጉልኝ፤ እኔም ሄጄ ምክር እጠይቃታለሁ” ሲል ባለሟሎቹን አዘዘ። እነርሱም “አንዲት ዔንዶራዊት አለች” ሲሉ መለሱለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ሳኦልም ባሪያዎቹን፦ ወደ እርስዋ ሄጄ እጠይቅ ዘንድ መናፍስትን የምትጠራ ሴት ፈልጉልኝ አላቸው፥ ባሪያዎቹም፦ እነሆ፥ መናፍስትን የምትጠራ አንዲት ሴት በዓይንዶር አለች አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 28:7
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለጸ​ሎት ስን​ሄ​ድም የም​ዋ​ር​ተ​ኛ​ነት መን​ፈስ ያደ​ረ​ባት አን​ዲት ልጅ አገ​ኘ​ችን፤ በጥ​ን​ቈ​ላም የም​ታ​ገ​ኘ​ውን ብዙ እጅ መንሻ ለጌ​ቶ​ችዋ ታገባ ነበር።


ከአ​እ​ላፍ ይልቅ በአ​ደ​ባ​ባ​ዮ​ችህ አን​ዲት ቀን ትሻ​ላ​ለች፤ በኃ​ጥ​ኣን ድን​ኳ​ኖች ከመ​ቀ​መጥ ይልቅ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት እጣል ዘንድ መረ​ጥሁ።


እን​ዲሁ ሳኦል በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ስላ​ደ​ረ​ገው ኀጢ​አት፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዳ​ዘ​ዘው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስላ​ል​ጠ​በቀ ሞተ። ደግ​ሞም መና​ፍ​ስት ጠሪን ጠየቀ።


በይ​ሳ​ኮ​ርና በአ​ሴር መካ​ከል ቤት​ሳ​ንና መን​ደ​ሮ​ችዋ፥ ዶርና መን​ደ​ሮ​ችዋ፥ መጌ​ዶና መን​ደ​ሮ​ችዋ፥ የመ​ፌታ ሦስ​ተኛ እጅና መን​ደ​ሮ​ችዋ ለም​ናሴ ነበሩ።


ራእዩ ገና እስከ ተወሰነው ጊዜ ነው፥ ወደ ፍጻሜውም ይቸኵላል፥ እርሱም አይዋሽም፣ ቢዘገይም በእርግጥ ይመጣልና ታገሠው፣ እርሱ አይዘገይም።


“ወደ መና​ፍ​ስት ጠሪ​ዎ​ችና ወደ ጠን​ቋ​ዮች አት​ሂዱ፤ እን​ዳ​ት​ረ​ክ​ሱ​ባ​ቸ​ውም አት​ፈ​ል​ጉ​አ​ቸው፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።


የግ​ብ​ፅም መን​ፈስ በው​ስ​ጣ​ቸው ትደ​ነ​ግ​ጣ​ለች፤ ምክ​ራ​ቸ​ውን አጠ​ፋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንና ጣዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን፥ ድም​ፃ​ቸ​ውን ዝቅ አድ​ር​ገው የሚ​ና​ገ​ሩ​ትን መና​ፍ​ስት ጠሪ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ይጠ​ይ​ቃሉ።


ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ሲነ​ጋ​ገር እነሆ፥ መል​እ​ክ​ተ​ኛው ወደ እርሱ ደረሰ፤ እር​ሱም፥ “እነሆ፥ ይህ ክፉ ነገር ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ነው፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ገና እጠ​ብቅ ዘንድ ምን​ድን ነኝ?” አለ።


ሳሙ​ኤል ግን ሞቶ ነበር፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ አል​ቅ​ሰ​ው​ለት ነበር፤ በከ​ተ​ማ​ውም በአ​ር​ማ​ቴም ቀብ​ረ​ውት ነበር። ሳኦ​ልም መና​ፍ​ስት ጠሪ​ዎ​ች​ንና ጠን​ቋ​ዮ​ችን ከም​ድር አጥ​ፍቶ ነበር።


በድ​ግ​ምት የሚ​ጠ​ነ​ቍ​ልም፥ መና​ፍ​ስ​ት​ንም የሚ​ጠራ፥ ጠን​ቋ​ይም፥ ሙታን ሳቢም፥ በወ​ፍም የሚ​ያ​ሟ​ርት በአ​ንተ ዘንድ አይ​ገኝ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች