Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 28:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ሴቲ​ቱም ወደ ሳኦል መጣች፤ እጅ​ግም ደን​ግጦ እንደ ነበር አይታ፥ “እነሆ፥ እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ ቃል​ህን ሰማሁ፤ ነፍ​ሴ​ንም በእጄ ጣልሁ፤ የነ​ገ​ር​ኸ​ኝ​ንም ቃል ሰማሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ሴትዮዋ ወደ ሳኦል መጥታ እጅግ መደንገጡን ባየች ጊዜ እንዲህ አለችው፤ “እነሆ፤ አገልጋይህ ቃልህን ሰምቻለሁ፤ በነፍሴም ቈርጬ የነገርኸኝን ፈጽሜአለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ሴቲቱም ወደ ሳኦል መጥታ ሲንቀጠቀጥ ስላየችው እንዲህ አለችው፦ “እኔ አገልጋይህ የአንተን ቃል ሰምቼ ሕይወቴን እስከ ማሳለፍ ደርሼ አለሁ፤ ያልከኝንም ነገር አዳመጥኩ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ሴቲቱም ወደ ሳኦል መጥታ ሲንቀጠቀጥ ስላየችው እንዲህ አለችው፦ “እኔ አገልጋይህ የአንተን ቃል ሰምቼ ሕይወቴን እስከ ማሳለፍ ደርሼአለሁ፤ ያልከኝንም ነገር አዳመጥኩ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ሴቲቱም ወደ ሳኦል መጣች፥ እጅግም ደንግጦ እንደ ነበረ አይታ፦ እነሆ፥ እኔ ባሪያህ ቃልህን ሰማሁ፥ ነፍሴንም በእጄ ጣልሁ፥ የነገርኽኝንም ቃል ሰማሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 28:21
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሚ​ያ​ድን እን​ደ​ሌ​ለም ባየሁ ጊዜ ሰው​ነ​ቴን በእጄ አሳ​ልፌ ለሞት በመ​ስ​ጠት ወደ አሞን ልጆች ተሻ​ገ​ርሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በፊቴ ጣላ​ቸው፤ ለም​ንስ ዛሬ ልት​ወ​ጉኝ ወደ እኔ መጣ​ችሁ?” አላ​ቸው።


ሥጋ​ዬን በጥ​ርሴ እይ​ዛ​ለሁ፤ ሕይ​ወ​ቴ​ንም በእጄ አጥ​ብቄ አኖ​ራ​ታ​ለሁ።


ነፍ​ሱ​ንም በእጁ ጥሎ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ዉን ገደለ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ርሱ ታላቅ መድ​ኀ​ኒት አደ​ረገ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ አይ​ተው ደስ አላ​ቸው፤ በከ​ንቱ ዳዊ​ትን ትገ​ድ​ለው ዘንድ ስለ​ምን በን​ጹሕ ደም ላይ ትበ​ድ​ላ​ለህ?”


ሳኦ​ልም በዚያ ጊዜ በቁ​መቱ ሙሉ በም​ድር ላይ ወደቀ፤ ከሳ​ሙ​ኤ​ልም ቃል የተ​ነሣ እጅግ ፈራ። በዚ​ያም ቀን ሁሉ፥ በዚ​ያም ሌሊት ሁሉ እን​ጀራ አል​በ​ላ​ምና ኀይል አል​ቀ​ረ​ለ​ትም።


አሁን እን​ግ​ዲህ አንተ ደግሞ የአ​ገ​ል​ጋ​ይ​ህን ቃል እን​ድ​ት​ሰማ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ፤ በፊ​ት​ህም ቁራሽ እን​ጀራ ላኑ​ር​ልህ፤ መን​ገ​ድም ትሄ​ዳ​ለ​ህና ትበ​ረታ ዘንድ ብላ” አለ​ችው።


የሶ​ር​ያም ንጉሥ መን​ፈስ ስለ​ዚህ እጅግ ተበ​ሳ​ጨች፤ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹ​ንም ጠርቶ፥ “ለእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ማን እን​ደ​ሚ​ነ​ግ​ረው አት​ነ​ግ​ሩ​ኝ​ምን?” አላ​ቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች