Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 26:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ዳዊ​ትም በቀ​ስታ ተነ​ሥቶ ሳኦል ወደ ሰፈ​ረ​በት ቦታ መጣ፤ ሳኦ​ልና የሠ​ራ​ዊቱ አለቃ የኔር ልጅ አቤ​ኔ​ርም የተ​ኙ​በ​ትን ስፍራ አየ፤ ሳኦ​ልም በድ​ን​ኳን ውስጥ ተኝቶ ነበር፤ ሕዝ​ቡም በዙ​ሪ​ያው ሰፍሮ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ዳዊትም ተነሥቶ ሳኦል ወደ ሰፈረበት ቦታ ሄደ፤ ሳኦልና የሰራዊቱ አለቃ፣ የኔር ልጅ አበኔር የተኙበትን ስፍራ አየ። ሳኦል በሰፈሩ መካከል ተኝቶ ሳለ፣ ሰራዊቱ በዙሪያው ሰፍሮ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ዳዊትም ተነሥቶ ሳኦል ወደ ሰፈረበት ቦታ ሄደ፤ ሳኦልና የሠራዊቱ አለቃ፥ የኔር ልጅ አበኔር የተኙበትን ስፍራ አየ። ሠራዊቱ በዙሪያው ሰፍሮ፥ ሳኦል በሰፈሩ መካከል ተኝቶ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ከዚያም በፍጥነት ተነሥቶ በመሄድ ሳኦልና የሠራዊቱ አዛዥ የኔር ልጅ አበኔር የሚተኙበትን ቦታ አረጋገጠ፤ ሳኦል በሰፈሩ መካከል ተኝቶ ሳለ ወታደሮቹ በዙሪያው ይገኙ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ዳዊትም ተነሥቶ ሳኦል ወደ ሰፈረበት ቦታ መጣ፥ ሳኦልና የሠራዊቱ አለቃ የኔር ልጅ አበኔርም የተኙበትን ስፍራ አየ፥ ሳኦልም በሰፈሩ ውስጥ ተኝቶ ነበር፥ ሕዝቡም በዙሪያው ሰፍሮ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 26:5
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውን ሊዋጋ ሲወጣ ባየ ጊዜ ለሠ​ራ​ዊቱ አለቃ ለአ​ቤ​ኔር፥ “አቤ​ኔር ሆይ፥ ይህ ብላ​ቴና የማን ልጅ ነው?” አለው። አቤ​ኔ​ርም፥ “ንጉሥ ሆይ፥ በሕ​ያው ነፍ​ስህ እም​ላ​ለሁ አላ​ው​ቅም” አለ።


ዳዊ​ትም ማልዶ ተነሣ፤ በጎ​ቹ​ንም ለጠ​ባቂ ተወ፤ እሴ​ይም ያዘ​ዘ​ውን ይዞ ሄደ፤ ጭፍ​ራ​ውም ተሰ​ልፎ ሲወጣ፥ ለሰ​ል​ፍም ሲጮኽ በሰ​ረ​ገ​ሎች ወደ ተከ​በ​በው ሰፈር መጣ።


ኔርም ቂስን ወለደ፤ ቂስም ሳኦ​ልን ወለደ፤ ሳኦ​ልም ዮና​ታ​ንን፥ ሜል​ኪ​ሳን፥ አሚ​ና​ዳ​ብን፥ አስ​በ​ኣ​ልን ወለደ።


አበ​ኔ​ርም ወደ ኬብ​ሮን በተ​መ​ለሰ ጊዜ ኢዮ​አብ በበር ውስጥ በቈ​ይታ ይና​ገ​ረው ዘንድ ወደ አጠ​ገቡ ወሰ​ደው፤ በዚ​ያም ለወ​ን​ድሙ ለአ​ሣ​ሄል ደም ተበ​ቅሎ ወገ​ቡን መታው፤ ሞተም።


ከብ​ን​ያም ልጆች ስሙ ቂስ የተ​ባለ አንድ ሰው ነበረ፥ እር​ሱም የአ​ብ​ሔል ልጅ፥ የያ​ሬድ ልጅ፥ የባ​ሔር ልጅ፥ የብ​ን​ያም ሰው፥ የአ​ፌቅ ልጅ፥ ጽኑዕ ኀያል ሰው ነበረ።


ዳዊ​ትም ሰላ​ዮ​ችን ላከ፤ ሳኦ​ልም ተዘ​ጋ​ጅቶ ወደ ቂአላ እንደ መጣ በር​ግጥ ዐወቀ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች