Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 26:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ሳኦ​ልም በየ​ሴ​ሞን ፊት ለፊት ባለው በኤ​ኬላ ኮረ​ብታ ላይ በመ​ን​ገዱ አጠ​ገብ ሰፈረ። ዳዊ​ትም በም​ድረ በዳ ውስጥ ተቀ​ምጦ ነበር፥ ዳዊ​ትም ሳኦል ሊፈ​ል​ገው ወደ ምድረ በዳ እንደ መጣ ዐወቀ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ሳኦልም በየሴሞን ትይዩ በሚገኘው በኤኬላ ኰረብታ ላይ በመንገድ ዳር ሰፈረ፤ ዳዊት ግን በምድረ በዳ ነበር። ዳዊትም ሳኦል እዚያ ድረስ እንደ ተከተለው ባወቀ ጊዜ፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ሳኦልም በየሴሞን ትይዩ በሚገኘው በሐኪላ ኰረብታ ላይ በመንገድ ዳር ሰፈረ፤ ዳዊት ግን በምድረ በዳ ነበር። ዳዊትም ሳኦል እዚያ ድረስ እንደ ተከተለው ባወቀ ጊዜ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ሳኦል በሐኪላ ተራራ ላይ በሚገኘው መንገድ አጠገብ በሔሲሞን ፊት ለፊት ሰፈረ፤ ዳዊትም በምድረ በዳ ነበር፤ ሳኦል እርሱን ለመፈለግ መምጣቱን ባየ ጊዜ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ሳኦልም በየሴሞን ፊት ለፊት ባለው በኤኬላ ኮረብታ ላይ በመንገዱ አጠገብ ሰፈረ። ዳዊትም በምድረ በዳ ውስጥ ተቀምጦ ነበር፥ ሳኦልም በስተ ኋላው ወደ ምድረ በዳ እንደ መጣ አየ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 26:3
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አቤቱ፥ ወደ አንተ የለ​መ​ን​ሁ​ትን ጸሎ​ቴን ስማኝ፥ ከጠ​ላ​ትም ጥር​ጥር ነፍ​ሴን አድ​ናት።


ዳዊ​ትም ሳኦል ሊፈ​ል​ገው እንደ ወጣ አየ፤ ዳዊ​ትም በቄኒ ዚፍ ምድረ በዳ በአ​ው​ክ​ሞ​ዲስ ውስጥ ይኖር ነበር።


የዚፍ ሰዎ​ችም ከአ​ው​ክ​ሞ​ዲስ ወደ ሳኦል ወደ ኮረ​ብ​ታው ወጥ​ተው እን​ዲህ አሉት፥ “እነሆ፥ ዳዊት በየ​ሴ​ሞን ቀኝ በጠ​ባቡ በኩል በኤ​ኬላ ኮረ​ብታ ላይ በቄኒ ውስጥ በማ​ሴ​ሬት በእኛ ዘንድ ተሸ​ሽጎ የለ​ምን?


ሳኦ​ልም ከእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ የተ​መ​ረ​ጡ​ትን ሦስት ሺህ ሰዎች ወሰደ፤ ዳዊ​ት​ንና ሰዎ​ቹ​ንም ለመ​ፈ​ለግ ዋሊ​ያ​ዎች ወደ​ሚ​ታ​ደ​ኑ​ባ​ቸው ዓለ​ቶች ሄደ።


የዚፍ ሰዎ​ችም ከአ​ው​ክ​ሞ​ዲስ ወደ ኮረ​ብ​ታው ወደ ሳኦል መጥ​ተው፥ “እነሆ፥ ዳዊት በየ​ሴ​ሞን ፊት ለፊት ባለው በኤ​ኬላ ኮረ​ብታ ላይ ከእኛ ጋር ተሸ​ሽጎ አለ” አሉት።


ዳዊ​ትም ሰላ​ዮ​ችን ላከ፤ ሳኦ​ልም ተዘ​ጋ​ጅቶ ወደ ቂአላ እንደ መጣ በር​ግጥ ዐወቀ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች