Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 26:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 አሁ​ንም በተ​ራ​ራው ላይ ሰው ቆቅን እን​ደ​ሚሻ የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ነፍ​ሴን ለመ​ሻት ወጥ​ቶ​አ​ልና ደሜ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በም​ድር ላይ አይ​ፍ​ሰስ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 አንድ ሰው በተራራ ላይ ቆቅ እንደሚያድን የእስራኤልም ንጉሥ ቍንጫ ለመፈለግ ስለ ወጣ፣ ደሜ ከእግዚአብሔር ፊት ርቆ በምድር ላይ እንዲፈስ አታድርግ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 አሁንስ ከጌታ ርቄ በባዕድ አገር እንድገደል አታድርግ፤ አሁንም በተራራው ላይ ቆቅን እንደሚሻ ሰው ይህን ያህል የእስራኤል ንጉሥ እኔን ስለምን ያሳድዳል?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ከእግዚአብሔር ርቄ በባዕድ አገር እንድገደል አታድርግ፤ ይህን ያኽል ታላቅ የሆነ የእስራኤል ንጉሥ እንደ ቁንጫ የምቈጠረውን እኔን ስለምን ያሳድዳል? እንደ በረሓ ቆቅ የሚያድነኝስ ስለምንድን ነው?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 አሁንም በተራራው ላይ ሰው ቆቅን እንደሚሻ የእስራኤል ንጉሥ ነፍሴን ለመሻት ወጥቶአልና ደሜ ከእግዚአብሔር ፊት ርቆ በምድር ላይ አይፍሰስ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 26:20
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“እነሆ፥ ብዙ ዓሣ አጥ​ማ​ጆ​ችን እል​ካ​ለሁ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እነ​ር​ሱም ያጠ​ም​ዱ​አ​ቸ​ዋል፤ ከዚ​ያም በኋላ ብዙ አድ​ዳ​ኞ​ችን እል​ካ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ከየ​ተ​ራ​ራ​ውና ከየ​ኮ​ረ​ብ​ታው ሁሉ ከየ​ድ​ን​ጋ​ዩም ስን​ጣቂ ውስጥ ያድ​ድ​ኑ​አ​ቸ​ዋል።


ጻዴ። በከ​ንቱ ነገር ጠላ​ቶች ሁሉ እንደ ወፍ ማደ​ንን አደ​ኑኝ።


ይህንም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ ይሁዳ መጣ፤ ከእርሱም ጋር ብዙ ሕዝብ ሰይፍና ጐመድ ይዘው ከካህናት አለቆችና ከሕዝቡ ሽማግሎች ዘንድ መጡ።


በዚያን ሰዓት ኢየሱስ ለሕዝቡ “ወንበዴን እንደምትይዙ ሰይፍና ጐመድ ይዛችሁ ልትይዙኝ ወጣችሁን? በመቅደስ ዕለት ዕለት እያስተማርሁ ከእናንተ ጋር ስቀመጥ ሳለሁ አልያዛችሁኝም።


ለሚ​ጸ​ልይ ጸሎ​ቱን ይሰ​ጠ​ዋል፤ የጻ​ድ​ቃ​ንን ዘመን ይባ​ር​ካል፤ የሰው ኀይል ጽኑዕ አይ​ደ​ለ​ምና።


እነሆ፥ ዛሬ በዋ​ሻው ውስጥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእጄ አሳ​ልፎ እንደ ሰጠህ ዐይ​ንህ አይ​ታ​ለች፤ አን​ተ​ንም እን​ድ​ገ​ድ​ልህ ሰዎች ተና​ገ​ሩኝ፤ እኔ ግን፦ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀባ ነውና እጄን በጌ​ታዬ ላይ አል​ዘ​ረ​ጋም ብዬ ራራ​ሁ​ልህ።


የጥ​ንት ምሳሌ፦ ‘ከኀ​ጢ​አ​ተ​ኞች ኀጢ​አት ይወ​ጣል’ እን​ደ​ሚል፥ እጄ ግን በአ​ንተ ላይ አት​ሆ​ንም።


አሁ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ማንን ለማ​ሳ​ደድ ወጥ​ተ​ሀል? አን​ተስ ማንን ታሳ​ድ​ዳ​ለህ? የሞተ ውሻን ታሳ​ድ​ዳ​ለ​ህን? ወይስ ቍን​ጫን ታሳ​ድ​ዳ​ለህ?


የሚ​ያ​ሳ​ድ​ድ​ህና ነፍ​ስ​ህን የሚሻ ሰው ቢነሣ፥ የጌ​ታዬ ነፍስ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በሕ​ይ​ወት ማሰ​ሪያ የታ​ሰ​ረች ትሆ​ና​ለች፤ የጠ​ላ​ቶ​ችህ ነፍስ ግን በወ​ን​ጭፍ እን​ደ​ሚ​ወ​ነ​ጨፍ ትሁን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች