Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 25:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 ዳዊ​ትም አቤ​ግ​ያን አላት፥ “ዛሬ እኔን ለመ​ገ​ና​ኘት አን​ቺን የላከ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 ዳዊትም አቢግያን እንዲህ አላት፤ “ዛሬ እንድታገኚኝ ወደ እኔ የላከሽ፣ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 ዳዊትም አቢጌልን እንዲህ አላት፤ “ዛሬ እንድታገኚኝ ወደ እኔ የላከሽ፥ የእስራኤል አምላክ ጌታ የተመሰገነ ይሁን!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 ዳዊትም እንዲህ አላት፤ “ከእኔ ጋር እንድትገናኚ አንቺን ወደ እኔ የላከ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 ዳዊትም አቢግያን አላት፦ ዛሬ እኔን ለመገናኘት አንቺን የሰደደ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 25:32
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“ይቅር ያለን፥ ለወ​ገ​ኖ​ቹም ድኅ​ነ​ትን ያደ​ረገ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን፤


ነገር ግን ስለ ሽን​ገ​ላ​ቸው አቈ​የ​ሃ​ቸው፥ በመ​ነ​ሣ​ታ​ቸ​ውም ጣል​ኻ​ቸው።


ዮቶ​ርም፥ “ከግ​ብ​ፃ​ው​ያን እጅና ከፈ​ር​ዖን እጅ ሕዝ​ቡን የአ​ዳነ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቡሩክ ነው።


እን​ዲ​ህም አለ፥ “ቸር​ነ​ቱ​ንና እው​ነ​ቱን ከጌ​ታዬ ያላ​ራቀ የጌ​ታዬ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን፤ ለእ​ኔም ወደ ጌታዬ ወደ አብ​ር​ሃም ወን​ድም ቤት መን​ገ​ዴን አቀ​ና​ልኝ።”


በቲቶ ልብ ስለ እና​ንተ ያን መት​ጋት የሰጠ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​መ​ሰ​ገነ ነው።


ያባ​ቶ​ቻ​ችን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያለ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ያከ​ብር ዘንድ ይህን ነገር በን​ጉሡ ልብ ያኖረ፥


ንጉ​ሡም፥ “ዐይኔ እያየ ዛሬ በዙ​ፋኔ ላይ የሚ​ቀ​መ​ጠ​ውን ዘር የሰ​ጠኝ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን” አለ።


ነገ​ሩም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ደስ አሰኘ፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በነ​ገ​ሩ​አ​ቸው ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገኑ፤ ከዚ​ያም ወዲያ የሮ​ቤል ልጆ​ችና የጋድ ልጆች፥ የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ የተ​ቀ​መ​ጡ​ባ​ትን ምድር ያጠፉ ዘንድ ለመ​ው​ጋት አን​ወ​ጣም ተባ​ባሉ።


እር​ሱም አለ፥ “ለአ​ባቴ ለዳ​ዊት በአፉ የተ​ና​ገረ፥ በእ​ጁም የፈ​ጸመ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች