Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 24:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 የዳ​ዊ​ትም ሰዎች፥ “እነሆ፥ ጠላ​ት​ህን በእ​ጅህ አሳ​ልፌ እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ፤ በዐ​ይ​ን​ህም ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኝ​ህን ታደ​ር​ግ​በ​ታ​ለህ ብሎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የነ​ገ​ረህ ቀን እነሆ ዛሬ ነው” አሉት። ዳዊ​ትም ተነ​ሥቶ የሳ​ኦ​ልን መጐ​ና​ጸ​ፊያ ዘርፍ በቀ​ስታ ቈረጠ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ዳዊት የሳኦልን ልብስ ጫፍ በመቍረጡ ልቡ በሐዘን ተመታ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 የዳዊት ሰዎችም ዳዊትን፥ “ጌታ፥ ‘የወደድኸውን ታደርግበት ዘንድ ጠላትህን በእጅህ አሳልፌ እሰጥሃለሁ’ ብሎ ለአንተ የተናገረው ቀን ዛሬ ነው” አሉት። ዳዊትም በልቡ እየተሳበ ሄዶ የሳኦልን ልብስ ጫፍ ማንም ሳያውቅ ቆርጦ ወሰደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ነገር ግን ዳዊትን የኅሊና ወቀሳ አስጨነቀው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ከዚያም በኋላ እንዲህ ሆነ፥ የሳኦልን የልብሱን ዘርፍ ስለቆረጠ የዳዊት ልብ በኅዘን ተመታ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 24:5
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሕዝ​ቡ​ንም ከቈ​ጠረ በኋላ ዳዊ​ትን ልቡ መታው፤ ዳዊ​ትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን፥ “ባደ​ረ​ግ​ሁት ነገር እጅግ በድ​ያ​ለሁ፤ አሁን ግን አቤቱ! ታላቅ ስን​ፍና አድ​ር​ጌ​አ​ለ​ሁና የባ​ሪ​ያ​ህን ኀጢ​አት ታርቅ ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ” አለው።


ልብ​ህን አላ​ደ​ነ​ደ​ን​ህ​ምና፥ እነ​ር​ሱም ለጥ​ፋ​ትና ለመ​ር​ገም እን​ዲ​ሆኑ በዚህ ስፍ​ራና በሚ​ኖ​ሩ​በት ላይ የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ትን ሰም​ተህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ተዋ​ር​ደ​ሃ​ልና፥ ልብ​ስ​ህን ቀድ​ደ​ሃ​ልና፥ በፊ​ቴም አል​ቅ​ሰ​ሃ​ልና እኔ ደግሞ ሰም​ቼ​ሃ​ለሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


አሁ​ንስ በፊቱ ክፉ ትሠራ ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ነገር ለምን አቃ​ለ​ልህ? ኬጤ​ያ​ዊ​ውን ኦር​ዮን በሰ​ይፍ መት​ተ​ሃል፤ ሚስ​ቱ​ንም ለአ​ንተ ሚስት ትሆን ዘንድ ወስ​ደ​ሃል፤ እር​ሱ​ንም በአ​ሞን ልጆች ሰይፍ ገድ​ለ​ሃል።


አቢ​ሳም ዳዊ​ትን፥ “ዛሬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠላ​ት​ህን በእ​ጅህ አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​ታል፤ አሁ​ንም እኔ በጦር አንድ ጊዜ ከም​ድር ጋር ላጣ​ብ​ቀው፤ ሁለ​ተ​ኛም አል​ደ​ግ​መ​ውም” አለው።


በመ​ከ​ራ​ችን ረድ​ኤ​ትን ስጠን፥ በሰ​ውም መታ​መን ከንቱ ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች