Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 24:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ሳኦ​ልም ከእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ የተ​መ​ረ​ጡ​ትን ሦስት ሺህ ሰዎች ወሰደ፤ ዳዊ​ት​ንና ሰዎ​ቹ​ንም ለመ​ፈ​ለግ ዋሊ​ያ​ዎች ወደ​ሚ​ታ​ደ​ኑ​ባ​ቸው ዓለ​ቶች ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ሳኦልም በመንገድ ዳር ወዳለው ወደ አንድ የበጎች ማደሪያ በደረሰ ጊዜ፣ ዋሻ አግኝቶ ወገቡን ሊሞክር ወደዚያ ገባ። ዳዊትና ሰዎቹም ከዋሻው በውስጠኛው ቦታ ተቀምጠው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ስለዚህ ሳኦል ከመላው እስራኤል የተመረጡ ሦስት ሺህ ሰዎችን ይዞ ዳዊትንና ሰዎቹን ለመፈለግ “የሜዳ ፍየሎች ዓለት” ወደ ተባለው ቦታ አቅራቢያ ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 በመንገድ ዳር ባሉት የበጎች ማደሪያዎች አቅራቢያ ወደሚገኘው ወደ አንድ ዋሻ ወገቡን ሊሞክር ወደ ውስጥ ገባ፤ በዚያም እርሱ ከተቀመጠበት ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ዳዊትና ተከታዮቹ ተደብቀው የሚኖሩበት ክፍል ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 በመንገድም አጠገብ ወዳሉት የበጎች ማደሪያዎች መጣ፥ በዚያም ዋሻ ነበረ፥ ሳኦልም ወገቡን ይሞክር ዘንድ ከዚያ ገባ፥ ዳዊትና ሰዎቹም ከዋሻው በውስጠኛው ቦታ ተቀምጠው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 24:3
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እጅግ ተዋ​ር​ጃ​ለ​ሁና ወደ ልመ​ናዬ ተመ​ል​ከት፤ በር​ት​ተ​ው​ብ​ኛ​ልና ከከ​በ​ቡኝ አድ​ነኝ።


ናዖ​ድም ከሄደ በኋላ አገ​ል​ጋ​ዮቹ መጡ፤ የሰ​ገ​ነ​ቱም ደጅ ተቈ​ልፎ ባዩ ጊዜ፥ “ምና​ል​ባት በበጋ ሰገ​ነቱ ውስጥ ወገ​ቡን ይሞ​ክር ይሆ​ናል” አሉ።


ያን​ጊ​ዜም ሳኦል ሦስት ሺህ ሰዎ​ችን ከእ​ስ​ራ​ኤል መረጠ፤ ሁለ​ቱም ሺህ በማ​ኪ​ማ​ስና በቤ​ቴል ተራራ ከሳ​ኦል ጋር ነበሩ፤ አን​ዱም ሺህ በብ​ን​ያም ገባ​ዖን ከልጁ ከዮ​ና​ታን ጋር ነበሩ፤ የቀ​ረ​ው​ንም ሕዝብ እያ​ን​ዳ​ን​ዱን ወደ ድን​ኳኑ አሰ​ና​በተ።


ሳኦ​ልም ተነ​ሥቶ ዳዊ​ትን በዚፍ ምድረ በዳ ይሻ ዘንድ ከእ​ስ​ራ​ኤል የተ​መ​ረጡ ሦስት ሺህ ሰዎ​ችን ይዞ ወደ ዚፍ ምድረ በዳ ወረደ።


ሳኦ​ልም በየ​ሴ​ሞን ፊት ለፊት ባለው በኤ​ኬላ ኮረ​ብታ ላይ በመ​ን​ገዱ አጠ​ገብ ሰፈረ። ዳዊ​ትም በም​ድረ በዳ ውስጥ ተቀ​ምጦ ነበር፥ ዳዊ​ትም ሳኦል ሊፈ​ል​ገው ወደ ምድረ በዳ እንደ መጣ ዐወቀ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች