Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 24:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 እን​ግ​ዲህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዳኛ ይሁን፤ በእ​ኔና በአ​ን​ተም መካ​ከል ይፍ​ረድ፤ አይ​ቶም ለእኔ ይፍ​ረድ፤ ከእ​ጅ​ህም ያድ​ነኝ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ዳዊት ይህን ተናግሮ ሲያበቃ ሳኦል፣ “ልጄ ዳዊት ሆይ፤ ይህ የአንተ ድምፅ ነውን?” ሲል ጠየቀው፤ ጮኾም አለቀሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 አሁንም ጌታ ዳኛ ሆኖ በመካከላችን ይፍረድ፤ ጉዳዬን ተመልክቶ እርሱው ይሟገትልኝ፤ እኔንም ከእጅህ ነጻ ያውጣኝ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ዳዊትም ይህን ተናግሮ እንደ ጨረሰ ሳኦል “ልጄ ዳዊት ሆይ! በእውነት ይህ የአንተ ድምፅ ነውን?” ብሎ ማልቀስ ጀመረ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 እንዲህም ሆነ፥ ዳዊት ይህን ቃል ለሳኦል መናገር በፈጸመ ጊዜ፥ ሳኦል፥ ልጄ ሆይ ዳዊት፥ ይህ ድምፅህ ነውን? አለ፥ ሳኦልም ድምፁን ከፍ አድርጎ አለቀሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 24:16
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሳኦ​ልም የዳ​ዊት ድምፅ እንደ ሆነ ዐውቆ፥ “ልጄ ዳዊት ሆይ! ይህ ድም​ፅህ ነውን?” አለው። ዳዊ​ትም፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! አዎ እኔ ባሪ​ያህ ነኝ” አለው።


ነገር ግን ይቃ​ወ​ሙት ዘንድ አል​ቻ​ሉም፤ በጥ​በ​ብና በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ይከ​ራ​ከ​ራ​ቸው ነበ​ርና።


በእ​ና​ንተ ላይ የሚ​ነሡ ሊመ​ል​ሱ​ላ​ች​ሁና ሊከ​ራ​ከ​ሯ​ችሁ እን​ዳ​ይ​ችሉ እኔ አፍ​ንና ጥበ​ብን እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ።


ቍጣ ጥበበኞችን ታጠፋለች፤ የለዘበ ቃል ቍጣን ይመልሳል፥ ሻካራ ቃል ግን ጠብን ያነሣሣል።


የእ​ው​ነ​ተኛ ሰው ቃል ሐሰ​ትን ይመ​ስ​ላል፥ ከእ​ና​ንተ ዘንድ ኀይ​ልን የም​ጠ​ይቅ አይ​ደ​ለ​ምና።


ዔሳ​ውም ሊገ​ና​ኘው ሮጠ፤ አን​ገ​ቱ​ንም አቅፎ ሳመው፤ ሁለ​ቱም በአ​ን​ድ​ነት አለ​ቀሱ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሠ​ራ​ውን ሥራ በስ​ድ​ስ​ተ​ኛው ቀን ፈጸመ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ከሠ​ራው ሥራ ሁሉ ዐረፈ።


ሦራም አብ​ራ​ምን፥ “ከአ​ንተ የተ​ነሣ እገ​ፋ​ለሁ፤ እኔ አገ​ል​ጋ​ዬን በብ​ብ​ትህ ሰጠ​ሁህ፤ እንደ ፀነ​ሰ​ችም ባየች ጊዜ እኔን ማክ​በ​ርን ተወች፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል ይፍ​ረድ” አለ​ችው።


እኔ አል​በ​ደ​ል​ሁ​ህም፤ አንተ ግን ከእኔ ጋር ትዋጋ ዘንድ ክፉ አታ​ድ​ር​ግ​ብኝ፤ ፈራጁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችና በአ​ሞን ልጆች መካ​ከል ዛሬ ይፍ​ረድ።”


ነፍ​ስ​ህም ዛሬ በዐ​ይኔ ፊት እንደ ከበ​ረች እን​ዲሁ ነፍሴ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ትክ​በር፤ ከመ​ከ​ራም ሁሉ ይሰ​ው​ረኝ፤ ያድ​ነ​ኝም።”


መን​ፈ​ስም በሠ​ላ​ሳው አለቃ በዓ​ማ​ሣይ ላይ መጣ፤ እር​ሱም፥ “ዳዊት ሆይ፥ እኛ ያንተ ነን፤ የእ​ሴይ ልጅ ሆይ፥ እኛ ከአ​ንተ ጋር ነን፤ ውጣ አም​ላ​ክህ ይረ​ዳ​ሃ​ልና ሰላም ሰላም ለአ​ንተ ይሁን፤ ለሚ​ረ​ዱ​ህም ሰላም ይሁን” አለ። ዳዊ​ትም ተቀ​በ​ላ​ቸው፤ የጭ​ፍ​ራም አለ​ቆች አደ​ረ​ጋ​ቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች