Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 23:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም ወደ ቂአላ ሄዱ፤ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ጋር ተዋጉ፤ እነ​ር​ሱም ከፊቱ ሸሹ፤ እን​ስ​ሶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ማረኩ፤ በታ​ላ​ቅም አገ​ዳ​ደል ገደ​ሉ​አ​ቸው። ዳዊ​ትም በቂ​አላ የሚ​ኖ​ሩ​ትን አዳነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ስለዚህ ዳዊትና ሰዎቹ ወደ ቅዒላ ሄደው፣ ፍልስጥኤማውያንን ወጉ፤ እንስሶቻቸውን ማርከው ወሰዱ፤ በፍልስጥኤማውያን ላይ ከባድ ጕዳት አደረሱ፤ ዳዊትም የቅዒላን ሕዝብ ታደገ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ስለዚህ ዳዊትና ሰዎቹ ወደ ቅዒላ ሄደው፥ ፍልስጥኤማውያንን ወጉ፤ እንስሶቻቸውን ማርከው ወሰዱ፤ በፍልስጥኤማውያን ላይ ከባድ ጉዳት አደረሱ፤ ዳዊትም የቅዒላን ሕዝብ ታደገ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ስለዚህም ዳዊትና ተከታዮቹ ወደ ቀዒላ ሄደው በፍልስጥኤማውያን ላይ አደጋ ጣሉባቸው፤ ከእነርሱም ብዙዎቹን ገድለው የከብትና የበግ መንጋዎቻቸውን ዘርፈው ወሰዱ፤ በዚህም ዐይነት ዳዊት ከተማይቱን ከጥፋት አዳናት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ዳዊትና ሰዎቹም ወደ ቅዒላ ሄዱ፥ ከፍልስጥኤማውያንም ጋር ተዋጉ፥ እንስሶቻቸውንም ማረኩ፥ በታላቅም አገዳደል ገደሉአቸው። ዳዊትም በቅዒላ የሚኖሩትን አዳነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 23:5
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በጦ​ር​ነ​ትም ጊዜ በኀ​ይል ታጸ​ና​ኛ​ለህ፤ በላዬ የቆ​ሙ​ት​ንም በበ​ታቼ ታስ​ገ​ዛ​ቸ​ዋ​ለህ።


ደግ​ሞም ጦር​ነት ሆነ፤ ዳዊ​ትም ወጥቶ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጋር ተዋጋ፤ ታላቅ ግዳ​ይም ገደ​ላ​ቸው፤ ከፊ​ቱም ሸሹ።


ዳዊ​ትም ደግሞ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠየቀ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መልሶ፥ “ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን በእ​ጅህ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለ​ሁና ተነ​ሥ​ተህ ወደ ቂአላ ውረድ” አለው።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ የአ​ቤ​ሜ​ሌክ ልጅ አብ​ያ​ታር ወደ ዳዊት ወደ ቂአላ በኰ​በ​ለለ ጊዜ ኤፉ​ዱን ይዞ ወርዶ ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች