Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 23:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 የዳ​ዊ​ትም ሰዎች፥ “እነሆ፥ በዚህ በይ​ሁዳ መቀ​መጥ እን​ፈ​ራ​ለን፤ ይል​ቁ​ንስ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ለመ​ዝ​ረፍ ወደ ቂአላ ብን​ሄድ እን​ዴት እን​ሆ​ና​ለን?” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 የዳዊት ሰዎች ግን፣ “እዚሁ በይሁዳ ምድር እያለን እየፈራን ነው፤ የፍልስጥኤማውያንን ሰራዊት ለመውጋት ወደ ቅዒላ የምንሄድ ከሆነማ ምን ያህል የሚያስፈራ ነው?” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 የዳዊት ሰዎች ግን፥ “እዚሁ በይሁዳ ምድር እያለን እየፈራን ነው፤ የፍልስጥኤማውያንን ሠራዊት ለመውጋት ወደ ቅዒላ የምንሄድ ከሆነማ ምን ያህል የሚያስፈራ ነው?” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ነገር ግን የዳዊት ተከታዮች “በዚህ በይሁዳ ስንኖር የምንፈራው ብዙ ነገር አለ፤ አሁን ደግሞ ወደ ቀዒላ ሄደን በፍልስጥኤማውያን ሠራዊት ላይ አደጋ ብንጥል ችግራችን የባሰ ችግር ይገጥመናል!” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 የዳዊትም ሰዎች፦ እነሆ፥ በዚህ በይሁዳ መቀመጥ እንፈራለን፥ ይልቁንስ በፍልስጥኤማውያን ጭፍሮች ላይ ወደ ቅዒላ ብንሄድ እንዴት ነው? አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 23:3
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አቤቱ፥ አድ​ነኝ፥ ደግ ሰው አል​ቆ​አ​ልና፥ ከሰው ልጆ​ችም መተ​ማ​መን ጐድ​ሎ​አ​ልና።


እግ​ሮ​ችህ ሮጠው ይደ​ክ​ማሉ፤ ፈረ​ሶ​ችን ለምን ታስ​ጌ​ጣ​ለህ? በሰ​ላ​ምም ምድር ላይ ለምን ትታ​መ​ና​ለህ? በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስስ ጩኸት ለምን እን​ዲህ ታደ​ር​ጋ​ለህ?


ዳዊ​ትም ሳኦል ሊፈ​ል​ገው እንደ ወጣ አየ፤ ዳዊ​ትም በቄኒ ዚፍ ምድረ በዳ በአ​ው​ክ​ሞ​ዲስ ውስጥ ይኖር ነበር።


ዳዊ​ትም፥ “ልሂ​ድን? እነ​ዚ​ህ​ንስ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ልም​ታን?” ብሎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠየቀ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ሂድ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ምታ፤ ቂአ​ላ​ንም አድን” አለው።


እን​ግ​ዲህ ዕወቁ፤ ከአ​ያ​ችሁ በኋላ ከእ​ና​ንተ ጋር እን​ሄ​ዳ​ለን፤ በዚ​ያ​ችም ምድር ካለ በይ​ሁዳ አእ​ላፍ ሁሉ እፈ​ት​ሻ​ታ​ለሁ።”


ሳኦ​ልና ሰዎ​ቹም በተ​ራ​ራው በአ​ንድ ወገን ሄዱ፤ ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም በተ​ራ​ራው በሌ​ላው ወገን ሄዱ። ዳዊ​ትም ከሳ​ኦል ፊት ያመ​ልጥ ዘንድ ተሰ​ውሮ ነበር። ሳኦ​ልና ሰዎቹ ዳዊ​ት​ንና ሰዎ​ቹን ለመ​ያዝ ከብ​በ​ዋ​ቸው ነበ​ርና።


ዳዊ​ትም ደግሞ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠየቀ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መልሶ፥ “ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን በእ​ጅህ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለ​ሁና ተነ​ሥ​ተህ ወደ ቂአላ ውረድ” አለው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች