Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 23:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ሳኦ​ልና ሰዎ​ቹም በተ​ራ​ራው በአ​ንድ ወገን ሄዱ፤ ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም በተ​ራ​ራው በሌ​ላው ወገን ሄዱ። ዳዊ​ትም ከሳ​ኦል ፊት ያመ​ልጥ ዘንድ ተሰ​ውሮ ነበር። ሳኦ​ልና ሰዎቹ ዳዊ​ት​ንና ሰዎ​ቹን ለመ​ያዝ ከብ​በ​ዋ​ቸው ነበ​ርና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ሳኦል በተራራው በአንዱ በኩል ሆኖ ሲያሳድድ፣ ዳዊትና ሰዎቹ ደግሞ በተራራው በሌላ በኩል ከሳኦል ለማምለጥ ይጣደፉ ነበር። ሳኦልና ወታደሮቹ ዳዊትንና ሰዎቹን ከብበው ለመያዝ ተቃርበው ሳሉ፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ሳኦል በተራራው በአንዱ በኩል ሆኖ ሲያሳድድ፥ ዳዊትና ሰዎቹ ደግሞ በተራራው በሌላ በኩል ከሳኦል ለማምለጥ ይጣደፉ ነበር። ሳኦልና ወታደሮቹ ዳዊትንና ሰዎቹን ከበው ለመያዝ ተቃርበው ሳሉ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ሳኦልና ወታደሮቹ ከኮረብታው በአንድ በኩል ሲሆኑ፥ ዳዊትና ተከታዮቹም ከኮረብታው በሌላ በኩል ነበሩ፤ ዳዊትና ተከታዮቹም ሊማርኩአቸው ከተቃረቡት ከሳኦልና ከወታደሮቹ ለማምለጥ በመጣደፍ ላይ ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ሳኦልም በተራራው በአንድ ወገን ሄደ፥ ዳዊትና ሰዎቹም በተራራው በሌላው ወገን ሄዱ። ሳኦልና ሰዎቹም ዳዊትንና ሰዎቹን ለመያዝ ከብበዎቸው ነበርና ዳዊት ከሳኦል ፊት ያመልጥ ዘንድ ፈጠነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 23:26
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሰማ​ዮ​ችን ዝቅ ዝቅ አደ​ረገ፥ ወረ​ደም፥ ጭጋግ ከእ​ግሩ በታች ነበረ።


ወደ ምድርም ስፋት ወጡ፤ የቅዱሳንንም ሰፈርና የተወደደችውን ከተማ ከበቡ፤ እሳትም ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወርዳ በላቻቸው።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ በእ​ስያ መከራ እንደ ተቀ​በ​ልን ልታ​ውቁ እወ​ዳ​ለሁ፤ ለሕ​ይ​ወ​ታ​ችን ተስፋ እስ​ክ​ን​ቈ​ርጥ ድረስ ከዐ​ቅ​ማ​ችን በላይ እጅግ መከራ ጸን​ቶ​ብን ነበ​ርና።


መሰ​ወ​ሪ​ያ​ውን ጨለማ አደ​ረገ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ድን​ኳኑ፤ ውኃ​ዎች በደ​መ​ና​ዎች ውስጥ ጠቈሩ።


አም​ላ​ካ​ችን ሆይ፥ አንተ አት​ፈ​ር​ድ​ባ​ቸ​ው​ምን? ይህን የመ​ጣ​ብ​ንን ታላቅ ወገን መቃ​ወም እን​ችል ዘንድ ኀይል የለ​ንም፤ የም​ና​ደ​ር​ግ​ባ​ቸ​ው​ንም አና​ው​ቅም፤ ነገር ግን ዐይ​ኖ​ቻ​ችን ወደ አንተ ናቸው።”


ዳዊ​ትም ከእ​ርሱ ጋር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያሉ​ትን አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን ሁሉ፥ “ተነሡ እን​ሽሽ፤ ከአ​ቤ​ሴ​ሎም እጅ የም​ን​ድ​ን​በት የለ​ን​ምና፤ ፈጥኖ እን​ዳ​ይ​ዘን፥ ክፉም እን​ዳ​ያ​መ​ጣ​ብን፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም በሰ​ልፍ ስለት እን​ዳ​ይ​መታ ፈጥ​ና​ችሁ እን​ሂድ” አላ​ቸው።


ዮና​ታ​ንም ደግሞ፥ “ቶሎ ፍጠን፤ አት​ቈይ” ብሎ ወደ ብላ​ቴ​ናው ጮኸ፤ የዮ​ና​ታ​ንም ብላ​ቴና ፍላ​ጻ​ዎ​ቹን ሰብ​ስቦ ወደ ጌታው መጣ።


ሜል​ኮ​ልም ዳዊ​ትን በመ​ስ​ኮት አወ​ረ​ደ​ችው፤ ሄደም፤ ሸሽ​ቶም አመ​ለጠ።


ለጋዛ ሰዎ​ችም፥ “ሶም​ሶን ወደ​ዚህ መጥ​ቶ​አል” ብለው ነገ​ሩ​አ​ቸው፤ ከበ​ቡ​ትም። ሌሊ​ቱ​ንም ሁሉ በከ​ተ​ማ​ዪቱ በር ሸመ​ቁ​በት፥ “ማለዳ እን​ገ​ድ​ለ​ዋ​ለን” ብለ​ውም ሌሊ​ቱን ሁሉ በዝ​ምታ ተቀ​መጡ።


ሳኦ​ልና ሰዎ​ቹም ሊፈ​ል​ጉት ሄዱ፤ ለዳ​ዊ​ትም ነገ​ሩት፤ እር​ሱም በማ​ዖን ምድረ በዳ ወዳ​ለው ዓለት ወረደ፤ ሳኦ​ልም ያን በሰማ ጊዜ ዳዊ​ትን በማ​ዖን ምድረ በዳ ተከ​ትሎ አሳ​ደ​ደው።


ወደ ሳኦ​ልም መል​እ​ክ​ተኛ መጥቶ፥ “ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሀገ​ሩን ወር​ረ​ው​ታ​ልና ፈጥ​ነህ ና” አለው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች