Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 21:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ዳዊ​ትም አቤ​ሜ​ሌ​ክን፥ “የን​ጉሥ ጉዳይ ስላ​ስ​ቸ​ኰ​ለኝ ሰይ​ፌ​ንና መሣ​ሪ​ያ​ዬን አላ​መ​ጣ​ሁ​ምና በአ​ንተ ዘንድ ጦር ወይም ሰይፍ እን​ዳለ እይ​ልኝ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ዳዊት አቢሜሌክን፣ “የንጉሡ ጕዳይ ስላስቸኰለኝ፣ ሰይፌንም ሆነ ሌላ የጦር መሣሪያ አላመጣሁም፤ እዚህ ካንተ ዘንድ ጦር ወይም ሰይፍ አይገኝምን?” ሲል ጠየቀው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ዳዊት አቢሜሌክን፥ “የንጉሡ ጉዳይ ስላስቸኮለኝ፥ ሰይፌንም ሆነ ሌላ የጦር መሣሪያ አላመጣሁም፤ እዚህ ካንተ ዘንድ ጦር ወይም ሰይፍ አይገኝምን?” ሲል ጠየቀው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ዳዊትም አቤሜሌክን “የምትሰጠኝ ጦር ወይም ሰይፍ በአንተ ዘንድ ይገኛልን? የንጉሡ ትእዛዝ አስቸኳይ ስለ ሆነ ጦሬንም ሆነ ሌላውንም መሣሪያዬን ለመያዝ ጊዜ አላገኘሁም ነበር” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ዳዊትም አቢሜሌክን፦ የንጉሥ ጉዳይ ስላስቸኮለኝ ሰይፌንና መሣሪያዬን አላመጣሁምና በአንተ ዘንድ ጦር ወይም ሰይፍ አለ ወይ? አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 21:8
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከረ​ጢ​ትም፥ ስል​ቻም፥ ጫማም፥ ምንም ምን አት​ያዙ፤ በመ​ን​ገ​ድም ማን​ንም ሰላም አት​በሉ።


በዚ​ያም ቀን ከሳ​ኦል አገ​ል​ጋ​ዮች አንድ ሰው በኔ​ሴራ አቅ​ራ​ቢያ በዚያ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ነበር፤ ስሙም ሶር​ያ​ዊው ዶይቅ ነበረ፤ የሳ​ኦ​ልም በቅ​ሎ​ዎች ጠባቂ ነበረ።


ካህ​ኑም፥ “በኤላ ሸለቆ የገ​ደ​ል​ኸው የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊው የጎ​ል​ያድ ሰይፍ እነሆ፥ በመ​ጐ​ና​ጸ​ፊያ ተጠ​ቅ​ልላ አለች፤ የም​ት​ወ​ስ​ዳት ከሆነ ውሰ​ዳት፤ ከእ​ር​ስዋ በቀር ሌላ ከዚህ የለ​ምና” አለው። ዳዊ​ትም፥ “ከእ​ር​ስዋ በቀር ሌላ ከሌለ እር​ስ​ዋን ስጠኝ” አለው። እር​ሱም ሰጠው።


ዳዊት አብ​ያ​ታ​ርን፦ ሶር​ያ​ዊው ዶይቅ በዚያ መኖ​ሩን ባየሁ ጊዜ፥ “ለሳ​ኦል በር​ግጥ ይነ​ግ​ራል ብዬ በዚያ ቀን አው​ቄ​ዋ​ለሁ፤ ለአ​ባ​ትህ ቤት ነፍስ ሁሉ ጥፋት በደ​ለ​ኛው እኔ ነኝ።


የሳ​ኦ​ልም በቅ​ሎ​ዎች ጠባቂ ሶር​ያ​ዊው ዶይቅ መልሶ፥ “የእ​ሴይ ልጅ ወደ ኖብ ወደ አኪ​ጦብ ልጅ ወደ ካህኑ አቤ​ሜ​ሌክ ሲመጣ አይቼ​ዋ​ለሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች