Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 21:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 አን​ኩ​ስም ብላ​ቴ​ኖ​ቹን፥ “እነሆ፥ ይህ ሰው እብድ እንደ ሆነ አይ​ታ​ች​ኋል፤ ለምን ወደ እኔ አመ​ጣ​ች​ሁት?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 አንኩስም አገልጋዮቹን እንዲህ አላቸው፤ “ሰውየውን እስኪ ተመልከቱት፤ እብድ እኮ ነው! ታዲያ ወደ እኔ ያመጣችሁት ለምንድን ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 አኪሽም አገልጋዮቹን እንዲህ አላቸው፤ “ሰውየውን እስቲ ተመልከቱት፤ እብድ እኮ ነው! ታዲያ ወደ እኔ ያመጣችሁት ለምንድን ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 አኪሽም ባለሟሎቹ ለሆኑት ባለሥልጣኖች “እነሆ! ይህ ሰው እብድ ነው! ታዲያ፥ ስለምን ወደ እኔ አመጣችሁት?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14-15 አንኩስም ባሪያዎቹን፦ እነሆ፥ ይህ ሰው እብድ እንደ ሆነ አይታችኋል፥ ለምን ወደ እኔ አመጣችሁት? በፊቴ ያብድ ዘንድ ይህን ያመጣችሁት እብድ ጠፍቶብኝ ነውን? እንዲህ ያለውስ ወደ ቤቴ ይገባልን? አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 21:14
4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አቤቱ፥ የሚ​በ​ድ​ሉ​ኝን በድ​ላ​ቸው፥ የሚ​ዋ​ጉ​ኝ​ንም ተዋ​ጋ​ቸው።


ግፍ ጠቢ​ብን ያሳ​ብ​ደ​ዋል፥ የል​ቡ​ንም ትዕ​ግ​ሥት ያጠ​ፋ​ዋል።


በፊ​ቱም መል​ኩን ለወጠ፤ በዚ​ያ​ችም ቀን አመ​ለጠ። በከ​ተ​ማ​ውም በር ከበሮ ይዞ በእጁ መታ፤ በበ​ሩም መድ​ረክ ላይ ተን​ፈ​ራ​ፈረ፤ ልጋ​ጉም በጢሙ ላይ ይወ​ርድ ነበር።


በፊቴ ያብድ ዘንድ ይህን ያመ​ጣ​ች​ሁት እኔ የእ​ብ​ዶች አለቃ ነኝን? እን​ዲህ ያለ​ውስ ወደ ቤቴ ይገ​ባ​ልን?” አላ​ቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች