Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 20:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ዮና​ታ​ንም ዳዊ​ትን አለው፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያው​ቃል፤ እስከ ሦስት ቀን ድረስ በዚህ ጊዜ አባ​ቴን መር​ምሬ እነሆ፥ በዳ​ዊት ላይ መል​ካም ቢያ​ስብ፥ እነሆ፥ ወደ ሜዳ ወደ አንተ አል​ል​ክም፤ ይህም ምል​ክት ይሁ​ንህ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ከዚያም ዮናታን ዳዊትን እንዲህ አለው፤ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ምስክር ይሁንብኝ፤ አባቴን ነገ መርምሬ ነገ ወይም ከነገ ወዲያ በዚህ ሰዓት እልክብሃለሁ፤ ስለ አንተ ያለው አመለካከት በጎ ከሆነም አሳውቅሃለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ዮናታን ዳዊትን እንዲህ አለው፦ “የእስራኤል አምላክ ጌታ ምስክር ይሁን! ነገ በዚህ ሰዓት ወይም በሦስተኛው ቀን፥ ስለ አንተ መልካም አስተሳሰብ ያለው መሆኑን አባቴን ጠይቄ ከተረዳሁ በኋላ፥ ስለዚሁ ጉዳይ የሚገልጥልህ መልእክተኛ እልክብሃለሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ዮናታን ዳዊትን እንዲህ አለው፦ “ነገ በዚህ ሰዓት ወይም በሦስተኛው ቀን ስለ አንተ መልካም አስተሳሰብ ያለው መሆኑን አባቴን ጠይቄ ከተረዳሁ በኋላ ስለዚሁ ጉዳይ የሚገልጥልህ መልእክተኛ እልክብሃለሁ፤ ለዚህም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ምስክር ይሁን!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ዮናታንም ዳዊትን አለው፦ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ምስክር ይሁን፥ ነገ ወይም ከነገ ወዲያ በዚህ ጊዜ አባቴን መርምሬ፥ እነሆ፥ በዳዊት ላይ መልካም ቢያስብ ልኬ እገልጥልሃለሁ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 20:12
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ንጉ​ሡም በእ​ነ​ርሱ መካ​ከል፥ በዳ​ዊ​ትና በሳ​ኦል ልጅ በዮ​ና​ታን መካ​ከል ስለ ነበ​ረው ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሐላ የሳ​ኦ​ልን ልጅ የዮ​ና​ታ​ንን ልጅ ሜም​ፌ​ቡ​ስ​ቴን ራራ​ለት።


እርሱ መን​ገ​ዴን የሚ​ያይ አይ​ደ​ለ​ምን? እር​ም​ጃ​ዬ​ንስ ሁሉ የሚ​ቈ​ጥር አይ​ደ​ለ​ምን?


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በጠ​ራ​ሁት ጊዜ ከጠ​ላ​ቶቼ እድ​ና​ለሁ።


ምክር በሰው ልብ እንደ ጥልቅ ውኃ ነው፤ አእምሮ ያለው ሰው ግን ይቀዳዋል።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ነው፤ ጌታም ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ማ​ል​ክት አም​ላክ ነው፤ እርሱ ያው​ቃል። እስ​ራ​ኤ​ልም ያው​ቀ​ዋል። በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያደ​ረ​ግ​ነው ለበ​ደ​ልና ለመ​ካድ ከሆነ ዛሬ አያ​ድ​ነን፤


ዮና​ታ​ንም ዳዊ​ትን፥ “ና፤ ወደ ሜዳ እን​ውጣ” አለው። ሁለ​ቱም ወደ ሜዳ ወጡ።


አባ​ቴም በአ​ንተ ላይ ክፋት ማድ​ረግ ቢወ​ድድ፥ እኔም ባላ​ስ​ታ​ው​ቅህ፥ በሰ​ላ​ምም ትሄድ ዘንድ ባላ​ሰ​ና​ብ​ትህ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዮ​ና​ታን ይህን ያድ​ርግ፤ ይህ​ንም ይጨ​ምር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከአ​ባቴ ጋር እንደ ነበረ ከአ​ንተ ጋር ይሁን።


ሁለ​ቱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቃል ኪዳን አደ​ረጉ፤ ዳዊ​ትም በቄኒ ውስጥ ተቀ​መጠ፤ ዮና​ታ​ንም ወደ ቤቱ ሄደ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች