Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 2:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 ከቤ​ት​ህም የቀ​ረው ሁሉ ይመ​ጣል፤ ከካ​ህ​ና​ትም ወደ አን​ዲቱ ዕጣ፥ እን​ጀራ ወደ​ም​በ​ላ​በት እባ​ክህ ላከኝ ብሎ ለአ​ንድ ብር መሐ​ልቅ ለቍ​ራሽ እን​ጀራ በፊቱ ይሰ​ግ​ዳል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 ከዘሮችህም መካከል የተረፈው ማንኛውም ሰው፣ ለአንዲት ጥሬ ብርና ለቍራሽ እንጀራ ሲል በፊቱ ወድቆ ይሰግዳል፤ “የዕለት ጕርሴን እንዳገኝ እባክህ በማንኛውም የክህነት ሥራ ላይ መድበኝ” በማለት ይለምናል።’ ”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 ከቤትህም የቀረው ሁሉ ይመጣል፤ በፊቱም ሰግዶ፦ ቁራሽ እንጀራ እንድበላ ከካህናት ስፍራ ወደ አንዲቱ፥ እባክህ፥ ስደደኝ ብሎ የዕለት ምግብ ብቻ ለማግኘት ይለምናል።’”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 ከአንተ ዘሮች መካከል በሕይወት የሚተርፍ ሁሉ ወደዚያ ካህን ዘንድ እየሄደ ለጥ ብሎ እጅ በመንሣት ከእርሱ ገንዘብና ምግብ ይለምናል፤ የዕለት ምግብ ብቻ ለማግኘትም ሲል ካህናትን በረዳትነት ማገልገል እንዲፈቀድለት ይለምናል።’ ”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 ከቤትህም የቀረው ሁሉ ይመጣል፥ በፊቱም ሰግዶ፦ ቁራሽ እንጀራ እበላ ዘንድ ከካህናት ወደ አንዲቱ ዕጣ፥ እባክህ፥ ስደደኝ ብሎ አንድ ብር አንድ እንጀራም ይለምናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 2:36
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በሴ​ሎም በዔሊ ቤት ላይ የተ​ና​ገ​ረው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ይፈ​ጸም ዘንድ ሰሎ​ሞን አብ​ያ​ታ​ርን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክህ​ነት አወ​ጣው።


እናንተ፦ እነሆ፥ ይህ ድካም ነው ብላችሁ ጢቅ አላችሁበት፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ በቅሚያ የያዛችሁትንም አንካሳውንም የታመመውንም አቅርባችኋል፣ እንዲሁ ቍርባንን ታመጣላችሁ፣ በውኑ ከእጃችሁ ይህን ልቀበለውን? ይላል እግዚአብሔር።


የታ​መነ ካህን ለእኔ አስ​ነ​ሣ​ለሁ፤ በል​ቤም፥ በነ​ፍ​ሴም እን​ዳለ እን​ዲሁ ያደ​ር​ጋል፤ እኔም የታ​መነ ቤት እሠ​ራ​ለ​ታ​ለሁ፤ ዘመ​ኑን ሁሉ እኔ በቀ​ባ​ሁት ሰው ፊት ይሄ​ዳል።


ብላ​ቴ​ናው ሳሙ​ኤ​ልም በዔሊ ፊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያገ​ለ​ግል ነበር፤ በዚ​ያም ዘመን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ክቡር ነበረ፤ ራእ​ይም አይ​ገ​ለ​ጥም ነበር።


ክፉዎች በደጎች ፊት ይሰነካከላሉ፥ ኃጥኣን ግን በጻድቃን በር ያገለግላሉ።


ሚካም፥ “በእኔ ዘንድ ተቀ​መጥ፤ አባ​ትና ካህ​ንም ሁነኝ፤ እኔም ልብ​ሶ​ች​ንና ምግ​ብ​ህን፥ በየ​ዓ​መ​ቱም ዐሥር ብር እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ” አለው።


የኮ​ረ​ብ​ታው መስ​ገ​ጃ​ዎች ካህ​ናት ግን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወዳ​ለው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ አይ​መ​ጡም ነበር፤ ብቻ በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው መካ​ከል ቂጣ እን​ጀራ ይበሉ ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች