Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 2:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 ይህ በሁ​ለቱ ልጆ​ችህ በአ​ፍ​ኒ​ንና በፊ​ን​ሐስ ላይ የሚ​መጣ ለአ​ንተ ምል​ክት ነው፤ ሁለቱ በአ​ንድ ቀን በጦር ይሞ​ታሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 “ ‘በሁለቱ ልጆችህ በአፍኒንና በፊንሐስ ላይ የሚደርሰው ላንተ ምልክት ይሆንሃል፣ ሁለቱም በአንድ ቀን ይሞታሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 ይህ በሁለቱ ልጆችህ በሖፍኒና በፊንሐስ ላይ የሚመጣ ለአንተ ምልክት ነው፤ ሁለቱም በአንድ ቀን ይሞታሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 የሁለቱ ልጆችህ የሖፍኒና የፊንሐስ ዕድል ፈንታ ምልክት ይሆንሃል፤ ሁለቱም በአንድ ቀን ይሞታሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 ይህ በሁለቱ ልጆችህ በአፍኒንና በፊንሐስ ላይ የሚመጣ ለአንተ ምልክት ነው፥ ሁለቱ በአንድ ቀን ይሞታሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 2:34
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዚ​ያም ቀን፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ረው ቃል ይህ ነው፤ “እነሆ፥ መሠ​ዊ​ያው ይሰ​ነ​ጠ​ቃል፤ በው​ስ​ጡም ያለው ስብ ይፈ​ስ​ሳል” ብሎ ምል​ክት ሰጠ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት ተማ​ረ​ከች፤ ሁለ​ቱም የዔሊ ልጆች አፍ​ኒ​ንና ፊን​ሐስ ሞቱ።


ያም ሰው መልሶ፥ “እስ​ራ​ኤል ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ፊት ሸሹ፤ ደግ​ሞም በሕ​ዝቡ ዘንድ ታላቅ ግድያ ሆኖ​አል፥ ሁለ​ቱም ልጆ​ችህ አፍ​ኒ​ንና ፊን​ሐስ ሞተ​ዋል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት ተማ​ር​ካ​ለች” አለው።


እን​ግ​ዲህ ተነ​ሥ​ተሽ ወደ ቤትሽ ሂጂ፤ እግ​ር​ሽም ወደ ከተማ በገባ ጊዜ ልጅሽ ይሞ​ታል።


በዚ​ያም ቀን በቤቱ ላይ የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ትን ሁሉ በዔሊ ላይ አጸ​ና​ለሁ፤ እኔም ጀምሬ እፈ​ጽ​ም​በ​ታ​ለሁ።


ለእ​ና​ን​ተም ምል​ክቱ እን​ዲህ ነው፦ ሕፃን አውራ ጣቱን ታስሮ፥ በጨ​ር​ቅም ተጠ​ቅ​ልሎ በበ​ረት ውስጥ ተኝቶ ታገ​ኛ​ላ​ቸሁ።”


በዐ​ይ​ኖቹ የሚ​ፈ​ጽም በነ​ፍ​ሱም የሚ​ተጋ ሰውን ከመ​ሠ​ዊ​ያዬ አላ​ጠ​ፋም። ከቤ​ትህ የሚ​ቀ​ሩት ሰዎች ሁሉ ግን በጐ​ል​ማ​ሶች ሰይፍ ይሞ​ታሉ።


እነ​ዚ​ህም ምል​ክ​ቶች በደ​ረ​ሱህ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነውና እጅህ የም​ት​ች​ለ​ውን ሁሉ አድ​ርግ።


እር​ስ​ዋም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ስለ ተማ​ረ​ከች፥ ስለ አማ​ቷና ስለ ባል​ዋም፦ የሕ​ፃ​ኑን ስም ዊቦ​ር​ኮ​ኢ​ቦት ብላ ጠራ​ችው።


እነ​ር​ሱም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ተማ​ር​ካ​ለ​ችና ክብር ከእ​ስ​ራ​ኤል ለቀቀ” አሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች