Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 2:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 እር​ሱም አላ​ቸው፥ “ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ ሁሉ አፍ የም​ሰ​ማ​ውን ይህን ነገር ለምን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ስለዚህም እንዲህ አላቸው፤ “ስለምትፈጽሙት ክፉ ድርጊት ከመላው ሕዝብ እሰማለሁ፤ ለምን እንዲህ ያለ ነገር ታደርጋላችሁ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 እርሱም እንዲህ አላቸው፦ “ስለ ክፉ ሥራችሁ ከዚህ ሕዝብ ሁሉ ሰምቻለሁና፥ ስለምን እንዲህ ያለ ነገር ታደርጋላችሁ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ስለዚህም እንዲህ አላቸው፤ “ስለምን ይህን ክፉ ነገር ታደርጋላችሁ? የምታደርጉትን ክፉ ነገር ሁሉ ከእያንዳንዱ ሰው ሰምቼዋለሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 እርሱም አላቸው፦ ስለ ክፉ ሥራችሁ ከዚህ ሕዝብ ሁሉ ሰምቻለሁና ስለምን እንዲህ ያለ ነገር ታደርጋላችሁ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 2:23
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አባ​ቱም፥ “ከቶ ለምን እን​ዲህ ታደ​ር​ጋ​ለህ?” ብሎ አል​ከ​ለ​ከ​ለ​ውም ነበር፤ እር​ሱም ደግሞ መልኩ እጅግ ያማረ ሰው ነበረ፤ እር​ሱ​ንም ከአ​ቤ​ሴ​ሎም በኋላ ወል​ዶት ነበር።


ዛሬም ክብ​ራ​ቸው ተዋ​ር​ዷ​ልና፥ ፊታ​ቸ​ውም አፍ​ሯ​ልና ኀጢ​አ​ታ​ቸው እንደ ሰዶ​ምና እንደ ገሞራ ኀጢ​አት ተቃ​ወ​መ​ቻ​ቸው፤ በላ​ያ​ቸ​ውም ተገ​ልጣ ታወ​ቀች።


ለጕ​ስ​ቍ​ል​ናሽ ከብ​ዙ​ዎች እረ​ኞች ጋር ኖርሽ የአ​መ​ን​ዝ​ራም ሴት ፊት ነበ​ረ​ብሽ፥ በሁ​ሉም ዘንድ ያለ ኀፍ​ረት ሄድሽ። ስለ​ዚህ የመ​ከ​ርና የበ​ልግ ዝናም ተከ​ለ​ከለ።


አስ​ጸ​ያፊ ነገ​ርን ስለ ሠሩ አፍ​ረ​ዋ​ልን? ምንም አላ​ፈ​ሩም፤ እፍ​ረ​ት​ንም አላ​ወ​ቁም፤ ስለ​ዚህ ከሚ​ወ​ድቁ ጋር ይወ​ድ​ቃሉ፤ በጐ​በ​ኘ​ኋ​ቸ​ውም ጊዜ ይዋ​ረ​ዳሉ፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እን​ዲ​ህም አሉ​አ​ቸው፥ “እና​ንተ ሰዎች፥ ይህን ነገር ለምን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ? እኛስ እንደ እና​ንተ የም​ን​ሞት ሰዎች አይ​ደ​ለ​ን​ምን? ነገር ግን ይህን ከንቱ ነገር ትታ​ችሁ ሰማ​ይና ምድ​ርን፥ ባሕ​ር​ንም በው​ስ​ጣ​ቸ​ውም ያለ​ውን ሁሉ ወደ ፈጠረ ወደ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትመ​ለሱ ዘንድ ወን​ጌ​ልን እና​ስ​ተ​ም​ራ​ች​ኋ​ለን።


በም​ድር ላይም ወደቀ፤ ወዲ​ያ​ውም፥ “ሳውል፥ ሳውል፥ ለምን ታሳ​ድ​ደ​ኛ​ለህ?” የሚ​ለ​ውን ቃል ሰማ።


እነ​ዚ​ህም ፍጻ​ሜ​ያ​ቸው ለጥ​ፋት የሆነ፥ ሆዳ​ቸ​ውን የሚ​ያ​መ​ልኩ፥ ክብ​ራ​ቸ​ውም ውር​ደት የሆ​ነ​ባ​ቸው፥ ምድ​ራ​ዊ​ዉ​ንም የሚ​ያ​ስቡ ናቸው።


ዔሊም እጅግ አረጀ፤ ልጆ​ቹም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ያደ​ረ​ጓ​ቸ​ውን፥ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ከሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉት ሴቶ​ችም ጋር እን​ደ​ሚ​ተኙ ሰማ።


ልጆቼ ሆይ፥ ይህ አይ​ሆ​ንም፤ እኔ የም​ሰ​ማው ይህ ነገር መል​ካም አይ​ደ​ለ​ምና እን​ዲህ አታ​ድ​ርጉ። ሕዝ​ቡ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከማ​ገ​ል​ገል አት​ከ​ል​ክ​ሉ​አ​ቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች