Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 19:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ሳኦ​ልም ጦሩን ይዞ በቤቱ ተቀ​ምጦ ሳለ ክፉ መን​ፈስ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ያዘው። ዳዊ​ትም በእጁ በገና ይመታ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ነገር ግን ሳኦል ጦሩን ይዞ በቤቱ ተቀምጦ ሳለ፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ክፉ መንፈስ መጣበት፤ ዳዊት በገናውን ይደረድር ነበር፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ነገር ግን ሳኦል ጦሩን ይዞ በቤቱ ተቀምጦ ሳለ፥ ከጌታ ዘንድ ክፉ መንፈስ መጣበት፤ ያንጊዜ ዳዊት በገናውን ይደረድር ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 አንድ ቀን ከእግዚአብሔር የተላከ ክፉ መንፈስ ሳኦልን ተቈራኘው፤ እርሱም ጦሩን በእጁ እንደ ያዘ በቤቱ ውስጥ ተቀምጦ ነበር፤ ዳዊትም በዚያው በገናውን ይደረድር ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ሳኦልም ጦሩን ይዞ በቤቱ ተቀምጦ ሳለ ክፉ መንፈስ ከእግዚአብሔር ዘንድ ያዘው። ዳዊትም በእጁ በገና ይመታ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 19:9
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ በምን ታስ​ተ​ዋ​ለህ? አለው፤ እር​ሱም ወጥቼ በነ​ቢ​ያቱ ሁሉ አፍ ሐሰ​ተኛ መን​ፈስ እሆ​ና​ለሁ አለ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ ማሳ​ሳ​ትስ ታሳ​ስ​ተ​ዋ​ለህ፤ ይሆ​ን​ል​ሃ​ልም፤ ውጣ፤ እን​ዲ​ሁም አድ​ርግ አለ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ ከሳ​ኦል ራቀ፤ ክፉም መን​ፈስ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ አስ​ጨ​ነ​ቀው።


የሳ​ኦ​ልም ብላ​ቴ​ኖች፥ “እነሆ፥ ክፉ መን​ፈስ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ያስ​ጨ​ን​ቅ​ሃል፤


አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ በፊ​ትህ ይና​ገሩ፤ በበ​ገና የሚ​ዘ​ምር ሰውም ለጌ​ታ​ቸው ይፈ​ል​ጉ​ለት፤ ክፉ መን​ፈ​ስም በመ​ጣ​ብህ ጊዜ በገ​ና​ውን ሲመታ አንተ ደኅና ትሆ​ና​ለህ፤ እር​ሱም ያሳ​ር​ፍ​ሃል” አሉት።


ደግ​ሞም ጦር​ነት ሆነ፤ ዳዊ​ትም ወጥቶ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጋር ተዋጋ፤ ታላቅ ግዳ​ይም ገደ​ላ​ቸው፤ ከፊ​ቱም ሸሹ።


ሳኦ​ልም ዳዊ​ትና ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩት ሰዎች ያሉ​በት ቦታ እንደ ታወቀ ሰማ። ሳኦ​ልም በራማ በሚ​ገ​ኘው በመ​ሰ​ማ​ር​ያው ቦታ በኮ​ረ​ብ​ታው ላይ ተቀ​ምጦ በእ​ጁም ጦር ይዞ ነበር፤ ብላ​ቴ​ኖ​ቹም ሁሉ በአ​ጠ​ገቡ ቆመው ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች