Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 19:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ዮና​ታ​ንም ዳዊ​ትን ጠርቶ ይህን ነገር ሁሉ ነገ​ረው፤ ዮና​ታ​ንም ዳዊ​ትን ወደ ሳኦል አመ​ጣው፤ እንደ ቀድ​ሞ​ውም በፊቱ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ስለዚህም ዮናታን ዳዊትን ጠርቶ የተባባሉትን ሁሉ ነገረው፤ ወደ ሳኦልም አመጣው፤ ዳዊትም እንደ ቀድሞው በፊቱ ቆመ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ስለዚህም ዮናታን ዳዊትን ጠርቶ የተባባሉትን ሁሉ ነገረው፤ ወደ ሳኦልም አመጣው፤ ዳዊትም እንደ ቀድሞው በፊቱ ቆመ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ስለዚህ ዮናታን ዳዊትን ጠርቶ ይህን ሁሉ ከነገረው በኋላ ወደ ሳኦል አቀረበው፤ ዳዊትም ከዚያ በፊት ያደርገው እንደ ነበር በንጉሡ ፊት እንደ ቀድሞው ማገልገሉን ቀጠለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ዮናታንም ዳዊትን ጠርቶ ይህን ነገር ሁሉ ነገረው፥ ዮናታንም ዳዊትን ወደ ሳኦል አመጣው፥ እንደ ቀድሞውም በፊቱ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 19:7
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ያዕ​ቆ​ብም የላ​ባን ፊት አየ፤ እነ​ሆም፥ ከእ​ርሱ ጋር እንደ ዱሮው አል​ሆ​ነም።


አስ​ቀ​ድሞ ሳኦል ንጉሥ ሆኖ ሳለ እስ​ራ​ኤ​ልን የም​ታ​ወ​ጣና የም​ታ​ገባ አንተ ነበ​ርህ፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ ሕዝ​ቤን እስ​ራ​ኤ​ልን አንተ ትጠ​ብ​ቃ​ለህ፤ በሕ​ዝ​ቤም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አለቃ ትሆ​ና​ለህ” አለህ።


ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አለው፥ “ጌታ ሆይ፥ እማ​ል​ድ​ሃ​ለሁ፤ ትና​ንት፥ ከት​ና​ንት ወዲያ ባሪ​ያ​ህን ከተ​ና​ገ​ር​ኸኝ ጀምሮ አፈ ትብ ሰው አይ​ደ​ለ​ሁም። እኔ አፌ ኰል​ታፋ፥ ምላ​ሴም ተብ​ታባ የሆነ ሰው ነኝ።”


ከቀ​ድ​ሞም ጀምሮ የማ​ቃ​ጠያ ስፍራ ተዘ​ጋ​ጅ​ታ​ለች፤ ለን​ጉ​ሥም ተበ​ጅ​ታ​ለች፤ ጥል​ቅና ሰፊም አድ​ር​ጎ​አ​ታል፤ እሳ​ትና ብዙ ማገዶ ተከ​ም​ሮ​አል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቍጣ እንደ ዲን ፈሳሽ ያቃ​ጥ​ለ​ዋል።


ዳዊ​ትም ወደ ሳኦል መጣ፤ በፊ​ቱም ቆመ፤ እጅ​ግም ወደ​ደው፤ ለእ​ር​ሱም ጋሻ ጃግ​ሬው ሆነ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በነ​ጋው ሳኦ​ልን ክፉ መን​ፈስ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ያዘው፤ በቤ​ቱም ውስጥ ትን​ቢት ተና​ገረ። ዳዊ​ትም በየ​ቀኑ ያደ​ርግ እንደ ነበረ በእጁ በገና ይመታ ነበር። ሳኦ​ልም ጦሩን በእጁ ይዞ ነበር።


ስለ​ዚ​ህም ሳኦል ከእ​ርሱ አራ​ቀው፤ የሺህ አለ​ቃም አድ​ርጎ ሾመው፤ በሕ​ዝ​ቡም ፊት ይወ​ጣና ይገባ ነበር።


በዚ​ያም ቀን ሳኦል ወሰ​ደው፤ ወደ አባ​ቱም ቤት ይመ​ል​ሰው ዘንድ አል​ፈ​ቀ​ደ​ለ​ትም።


ሳኦ​ልም የዮ​ና​ታ​ንን ቃል ሰማ፤ ሳኦ​ልም፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ዳዊት አይ​ገ​ደ​ልም” ብሎ ማለ።


ደግ​ሞም ጦር​ነት ሆነ፤ ዳዊ​ትም ወጥቶ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጋር ተዋጋ፤ ታላቅ ግዳ​ይም ገደ​ላ​ቸው፤ ከፊ​ቱም ሸሹ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች