Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 19:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ዳዊ​ትም ሸሽቶ አመ​ለጠ፤ ወደ አር​ማ​ቴ​ምም ወደ ሳሙ​ኤል መጣ፤ ሳኦ​ልም ያደ​ረ​ገ​በ​ትን ሁሉ ነገ​ረው፤ እር​ሱና ሳሙ​ኤ​ልም ሄዱ፤ በአ​ው​ቴ​ዘ​ራ​ማም ተቀ​መጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ዳዊት ሸሽቶ ካመለጠ በኋላ፣ ወደ አርማቴም ወደ ሳሙኤል ሄደ፣ ሳኦል ያደረገበትን ሁሉ ነገረው። ከዚያም እርሱና ሳሙኤል ወደ ነዋት ሄደው ተቀመጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ዳዊት ሸሽቶ ካመለጠ በኋላ፥ ወደ ራማ ወደ ሳሙኤል ሄደ፥ ሳኦል ያደረገበትን ሁሉ ነገረው። ከዚያም እርሱና ሳሙኤል ወደ ናዮት ሄደው በዚያ ተቀመጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ዳዊትም አምልጦ ሳሙኤል ወደነበረበት ወደ ራማ መጣ፤ ሳኦል ያደረገበትንም በደል ሁሉ ነገረው፤ ከዚህም በኋላ ሳሙኤልና ዳዊት በራማ ወደምትገኘው ወደ ናዮት ሄደው በዚያ ተቀመጡ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ዳዊትም ሸሽቶ አመለጠ፥ ወደ አርማቴምም ወደ ሳሙኤል መጣ፥ ሳኦልም ያደረገበትን ሁሉ ነገረው፥ እርሱና ሳሙኤልም ሄዱ በነዋትዘራማም ተቀመጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 19:18
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እርስ በርሳችሁ በኀጢአታችሁ ተናዘዙ። ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኀይል ታደርጋለች።


ማል​ደ​ውም ተነ​ሥ​ተው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰግ​ደው ሄዱ፤ ወደ ቤታ​ቸ​ውም ወደ አር​ማ​ቴም ደረሱ፤ ሕል​ቃ​ናም ሚስ​ቱን ሐናን ዐወ​ቃት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አሰ​ባት፤ ፀነ​ሰ​ችም።


ሳሙ​ኤ​ልም ወደ አር​ማ​ቴም ሄደ፤ ሳኦ​ልም ወደ ቤቱ ወደ ገባ​ዖን ወጣ።


ለሳ​ኦ​ልም፥ “ዳዊት እነሆ፥ በአ​ው​ቴ​ዘ​ራማ ተቀ​ም​ጦ​አል” ብለው ነገ​ሩት።


ሳኦ​ልም እጅግ ተቈጣ፤ እር​ሱም ደግሞ ወደ አር​ማ​ቴም መጣ፤ በመ​ሴ​ፋም አው​ድማ ወዳ​ለው ወደ ታላቁ የውኃ ጕድ​ጓድ ደረሰ። “ሳሙ​ኤ​ልና ዳዊት የት ናቸው?” ብሎ ጠየቀ፤ “እነሆ፥ በአ​ው​ቴ​ዘ​ራማ ናቸው” አሉት።


ወደ አው​ቴ​ዘ​ራ​ማም ሄደ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በእ​ርሱ ደግሞ ወረደ፤ እር​ሱም ሄደ፤ ወደ አው​ቴ​ዘ​ራ​ማም እስ​ኪ​መጣ ድረስ ትን​ቢት ይና​ገር ነበር።


ዳዊ​ትም ከአ​ው​ቴ​ዘ​ራማ ሸሸ፤ ወደ ዮና​ታ​ንም መጣ፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “ምን አደ​ረ​ግሁ? ምንስ በደ​ልሁ? ነፍ​ሴ​ንም ይሻት ዘንድ በአ​ባ​ትህ ፊት ጥፋ​ቴና ኀጢ​አቴ ምን​ድን ነው?”


የአ​ን​ኩስ ብላ​ቴ​ኖ​ችም፥ “ይህ ዳዊት የሀ​ገሩ ንጉሥ አይ​ደ​ለ​ምን? ሳኦል ሺህ፥ ዳዊ​ትም ዐሥር ሺህ ገደለ ብለው ሴቶች በዘ​ፈን የዘ​መ​ሩ​ለት እርሱ አይ​ደ​ለ​ምን?” አሉት።


ሳሙ​ኤል ግን ሞቶ ነበር፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ አል​ቅ​ሰ​ው​ለት ነበር፤ በከ​ተ​ማ​ውም በአ​ር​ማ​ቴም ቀብ​ረ​ውት ነበር። ሳኦ​ልም መና​ፍ​ስት ጠሪ​ዎ​ች​ንና ጠን​ቋ​ዮ​ችን ከም​ድር አጥ​ፍቶ ነበር።


ቤቱም በዚያ ነበ​ረና ወደ አር​ማ​ቴም ይመ​ለስ ነበር፤ በዚ​ያም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ይፈ​ርድ ነበር፤ በዚ​ያም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ሠራ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች