Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 18:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 የሳ​ኦ​ልም ብላ​ቴ​ኖች ይህን ቃል በዳ​ዊት ጆሮ ተና​ገሩ፤ ዳዊ​ትም፥ “እኔ የተ​ዋ​ረ​ድ​ሁና ክብር የሌ​ለኝ ሰው ስሆን ለን​ጉሥ አማች እሆን ዘንድ ለእ​ና​ንተ ትንሽ ነገር ይመ​ስ​ላ​ች​ኋ​ልን?” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 እነርሱም ይህንኑ ለዳዊት ደግመው ነገሩት፤ ዳዊት ግን “ለመሆኑ የንጉሥ አማች መሆንን እስከዚህ ትንሽ ነገር አድርጋችሁ ትቈጥራላችሁን? እኔ አንድ ምስኪን ድኻና እምብዛም የማልታወቅ ሰው ነኝ” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 እነርሱም ይህንኑ ለዳዊት ደግመው ነገሩት፤ ዳዊት ግን “ለመሆኑ የንጉሥ ዐማች መሆንን እስከዚህ ትንሽ ነገር አድርጋችሁ ትቆጥራላችሁን? እኔ አንድ ምስኪን ድኻና እውቅና የሌለኝ መሆኔን አጣችሁትን?” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ስለዚህ የሳኦል ባለሟሎች ይህን ጉዳይ ለዳዊት በምሥጢር ነገሩት፤ እርሱም፦ “እንደእኔ ላለ ዝቅተኛ ድኻ ሰው የንጉሥ ዐማች መሆን ቀላል ይመስላችኋልን?” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 የሳኦልም ባሪያዎች ይህን ቃል በዳዊት ጆሮ ተናገሩ፥ ዳዊትም፦ እኔ ድሀ የተጠቃሁም ሰው ስሆን ለንጉሥ አማች እሆን ዘንድ ለእናንተ ትንሽ ነገር ይመስላችኋልን? አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 18:23
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ያዕ​ቆ​ብም ስለ ራሔል ሰባት ዓመት ተገዛ፤ እር​ስ​ዋ​ንም ይወ​ድ​ዳት ስለ​ነ​በረ በእ​ርሱ ዘንድ ጥቂት ቀን ሆነ​ለት።


ብዙ ማጫ አምጣ በሉኝ፤ በም​ት​ጠ​ይ​ቁ​ኝም መጠን እሰ​ጣ​ለሁ፤ ይህ​ችን ብላ​ቴና ግን ሚስት ትሆ​ነኝ ዘንድ ስጡኝ።”


ባለጠጎች ወዳጆች ድሆች ወዳጆችን ይጠላሉ፤ የባለጠጎች ወዳጆች ግን ብዙዎች ናቸው።


የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፥ እንዲሁም ነን። ስለዚህ ምክንያት ዓለም እርሱን ስላላወቀው እኛን አያውቀንም።


ዳዊ​ትም ሳኦ​ልን፥ “ለን​ጉሥ አማች እሆን ዘንድ እኔ ማን ነኝ? ሰው​ነ​ቴስ ምን​ድን ናት? የአ​ባ​ቴስ ወገን በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ምን​ድን ነው?” አለው።


ሳኦ​ልም ብላ​ቴ​ኖ​ቹን፥ “እነሆ፥ ንጉሥ እጅግ ወድ​ዶ​ሃል፤ ቤተ ሰቡም ሁሉ ወድ​ደ​ው​ሃል፤ አሁ​ንም ለን​ጉሥ አማች ሁን ብላ​ችሁ በስ​ውር ለዳ​ዊት ንገ​ሩት” ብሎ አዘ​ዛ​ቸው።


የሳ​ኦ​ልም ብላ​ቴ​ኖች፦ ዳዊት እን​ዲህ ብሎ ተና​ገረ ብለው ነገ​ሩት።


ሳኦ​ልም መልሶ፥ “እኔ ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ዶች ከሚ​ያ​ንስ ወገን የሆ​ንሁ ብን​ያ​ማዊ ሰው አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? ወገ​ኔስ ከብ​ን​ያም ነገድ ወገ​ኖች ሁሉ የሚ​ያ​ንስ አይ​ደ​ለ​ምን? እን​ዲ​ህስ ያለ​ውን ነገር ለምን ነገ​ር​ኸኝ?” አለ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች