Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 18:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 የሳ​ኦ​ልም ልጅ ሜል​ኮል ዳዊ​ትን ወደ​ደች፤ ይህም ወሬ ለሳ​ኦል ደረ​ሰ​ለት፤ ነገ​ሩም ደስ አሰ​ኘው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 በዚህ ጊዜ የሳኦል ልጅ ሜልኮል ዳዊትን ወደደችው፤ ሳኦልም ይህን ሲሰማ ደስ አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 በዚህ ጊዜ የሳኦል ልጅ ሜልኮል ዳዊትን ወደደችው፤ ሳኦልም ይህን ሲሰማ ደስ አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ይሁን እንጂ ሜልኮል ተብላ የምትጠራው የሳኦል ልጅ ዳዊትን ወደደች፤ ሳኦልም ይህን በሰማ ጊዜ ደስ አለው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 የሳኦልም ልጅ ሜልኮል ዳዊትን ወደደች፥ ይህም ወሬ ለሳኦል ደረሰለት፥ ነገሩም ደስ አሰኘው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 18:20
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዳዊ​ትም፥ “ይሁን፤ በመ​ል​ካም ፈቃ​ደ​ኛ​ነት ከአ​ንተ ጋር ቃል ኪዳን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ነገር ግን አንድ ነገር ከአ​ንተ እሻ​ለሁ፤ ፊቴን ለማ​የት በመ​ጣህ ጊዜ፥ የሳ​ኦ​ልን ልጅ ሜል​ኮ​ልን ካላ​መ​ጣ​ህ​ልኝ ፊቴን አታ​ይም” አለው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ በደ​ረ​ሰች ጊዜ የሳ​ኦል ልጅ ሜል​ኮል በመ​ስ​ኮት ሆና ተመ​ለ​ከ​ተች፤ ንጉ​ሡም ዳዊት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ሲዘ​ል​ልና ሲዘ​ምር አየ​ችው፥ በል​ብ​ዋም ናቀ​ችው።


ዳዊ​ትም ቤተ ሰቡን ሊመ​ርቅ ተመ​ለሰ። የሳ​ኦል ልጅ ሜል​ኮ​ልም ዳዊ​ትን ለመ​ቀ​በል ወጣ​ችና ሰላ​ምታ ሰጠ​ችው፥ “ከሚ​ዘ​ፍ​ኑት አንዱ እን​ደ​ሚ​ገ​ለጥ የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ በአ​ገ​ል​ጋ​ዮቹ ሚስ​ቶች ፊት በመ​ገ​ለጡ ምንኛ የተ​ከ​በረ ነው!” አለች።


የሳ​ኦ​ልም ወን​ዶች ልጆች ዮና​ታን፥ የሱዊ፥ ሚል​ኪሳ ነበሩ፤ የሁ​ለ​ቱም ሴቶች ልጆቹ ስም ይህ ነበረ፤ የታ​ላ​ቂቱ ስም ሜሮብ፥ የታ​ና​ሺ​ቱም ስም ሜል​ኮል ነበረ።


ሳኦ​ልም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዳ​ዊት ጋር እንደ ሆነ አየ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ወደ​ዱት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች