Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 17:44 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

44 ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውም ዳዊ​ትን፥ “ወደ እኔ ና፤ ሥጋ​ህ​ንም ለሰ​ማይ ወፎ​ችና ለም​ድር አራ​ዊት እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

44 ፍልስጥኤማዊውም፣ “እስኪ ወደኔ ና! ሥጋህን ለሰማይ አሞሮችና፣ ለምድር አራዊት እሰጣለሁ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

44 እርሱም ዳዊትን፥ “እስቲ ወደኔ ና! ሥጋህን ለሰማይ አሞሮችና፥ ለምድር አራዊት እሰጣለሁ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

44 ቀጥሎም “ወዲህ ና! ሥጋህን ለሰማይ አሞራዎችና ለምድር አራዊት እሰጣለሁ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

44 ፍልስጥኤማዊውም ዳዊትን፦ ወደ እኔ ና፥ ሥጋህንም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት እሰጣለሁ አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 17:44
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከመውደቅ በፊት የሰው ልቡ ከፍ ከፍ ይላል፥ ሳይከብርም ይዋረዳል።


“አንተ የሰው ልጅ ሆይ! የጢ​ሮ​ስን አለቃ እን​ዲህ በለው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ልብህ ኰር​ት​ዋል፥ አንተ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በባ​ሕር መካ​ከል እን​ዲ​ቀ​መጥ እኔም ተቀ​ም​ጫ​ለሁ ብለ​ሃ​ልና፤ አንተ ሰው ስት​ሆን ልብ​ህን እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልብ ብታ​ደ​ር​ግም አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ደ​ለ​ህም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ጠቢብ በጥ​በቡ አይ​መካ፤ ኀያ​ልም በኀ​ይሉ አይ​መካ፤ ባለ​ጠ​ጋም በብ​ል​ጥ​ግ​ናው አይ​መካ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዛሬ አን​ተን በእጄ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣል፤ እመ​ታ​ህ​ማ​ለሁ፤ ራስ​ህ​ንም ከአ​ንተ እቈ​ር​ጠ​ዋ​ለሁ፤ ሬሳ​ህ​ንና የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ን​ንም ሠራ​ዊት ሬሶች ለሰ​ማይ ወፎ​ችና ለም​ድር አራ​ዊት ዛሬ እሰ​ጣ​ለሁ። ምድር ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር እን​ዳለ ያው​ቃሉ፤


አንድም መልአክ በፀሐይ ውስጥ ቆሞ አየሁ፤ በሰማይም መካከል ለሚበሩ ወፎች ሁሉ “መጥታችሁ የነገሥታትን ሥጋና የሻለቃዎችን ሥጋ የብርቱዎችንም ሥጋ የፈረሶችንም በእነርሱም የተቀመጡትን ሥጋ የጌታዎችንና የባሪያዎችንም የታናናሾችንና የታላላቆችንም ሁሉ ሥጋ እንድትበሉ ወደ ታላቁ ወደ እግዚአብሔር እራት ተከማቹ፤” ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።


የሰ​ፈ​ሩም ሰዎች፦ ዮና​ታ​ን​ንና ጋሻ ጃግ​ሬ​ውን “ወደ እኛ ውጡ፤ አንድ ነገ​ር​ንም እን​ነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለን” አሉ። ዮና​ታ​ንም ጋሻ ጃግ​ሬ​ውን “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል እጅ አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና ተከ​ተ​ለኝ” አለው።


የኢ​ዮ​ሔል ልጅ ሩጻ​ፋም ማቅ ወስዳ ከመ​ከር ወራት ጀምሮ ዝናብ ከሰ​ማይ እስ​ኪ​ዘ​ንብ ድረስ በድ​ን​ጋይ ላይ ዘረ​ጋ​ችው፤ በቀ​ንም የሰ​ማይ ወፎች፥ በሌ​ሊ​ትም የዱር አራ​ዊት ያር​ፉ​ባ​ቸው ዘንድ አል​ተ​ወ​ችም።


ለጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው እጅ፥ ነፍ​ሳ​ቸ​ው​ንም ለሚ​ሹ​አት እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለሁ፤ ሬሳ​ቸ​ውም ለሰ​ማይ ወፎ​ችና ለም​ድር አራ​ዊት መብል ይሆ​ናል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች