Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 17:39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

39 ዳዊ​ት​ንም ሰይ​ፉን በል​ብሱ ላይ አስ​ታ​ጠ​ቀው፤ ዳዊ​ትም አን​ድና ሁለት ጊዜ ሲራ​መድ ደከመ። ዳዊ​ትም ሳኦ​ልን፥ “አለ​መ​ድ​ሁ​ምና በዚህ መሄድ አል​ች​ልም” አለው። ከላ​ዩም አወ​ለ​ቁ​ለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

39 ዳዊትም ይህን ዐይነት ልብስ ለብሶ ስለማያውቅ፣ ሰይፉን በጦር ልብሱ ላይ ታጥቆ ለመራመድ ሞከረ። እርሱም ሳኦልን፣ “ያልተለማመድሁት ስለ ሆነ እንደዚህ ሆኜ መራመድ አልችልም” አለው። ስለዚህ ሁሉንም አወለቀው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

39 ዳዊትም ይህን ዓይነት ልብስ ለብሶ ስለማያውቅ፥ ሰይፉን በጦር ልብሱ ላይ ታጥቆ ለመራመድ ሞከረ፤ እርሱም ሳኦልን፥ “ያልተለማመድሁት ስለሆነ እንደዚህ ሆኜ መራመድ አልችልም” አለው። ስለዚህ ያንን አወለቀው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

39 ዳዊትም ይህን ዐይነት ልብስ ለብሶ ስለማያውቅ ሰይፉን በጦር ልብሱ ላይ ታጥቆ ለመሄድ ሲነሣ መራመድ አልቻለም፤ ስለዚህ ዳዊት ሳኦልን፦ “ያልተለማመድኩት ነገር ስለ ሆነ ይህን ሁሉ ልብስ ለብሼ መዋጋት አልችልም፤” አለ፤ ስለዚህም ያንን ሁሉ አወለቀ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

39 ዳዊትም ሰይፉን በልብሱ ላይ ታጠቀ፥ ገናም አልፈተነውምና መሄድ ሞከረ። ዳዊትም ሳኦልን፦ አልፈተንሁትምና እንዲህ ብዬ መሄድ አልችልም አለው። ዳዊትም አወለቀ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 17:39
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነገር ግን የይ​ሁ​ዳን ልጆች ይቅር እላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እኔ አም​ላ​ካ​ቸ​ውም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አድ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ እንጂ በቀ​ስት ወይም በሰ​ይፍ፥ ወይም በጦር፥ ወይም በሠ​ረ​ገላ፥ ወይም በፈ​ረ​ሶች፥ ወይም በፈ​ረ​ሰ​ኞች የማ​ድ​ና​ቸው አይ​ደ​ለም” አለው።


መልሶም፦ ለዘሩባቤል የተባለው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፦ በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ሳኦ​ልም ለዳ​ዊት ጥሩር አለ​በ​ሰው፤ በራ​ሱም ላይ የናስ ቍር ደፋ​ለት።


ዳዊ​ትም በት​ሩን በእጁ ያዘ፤ ከወ​ን​ዝም አም​ስት ድብ​ል​ብል ድን​ጋ​ዮ​ችን መረጠ፤ በእ​ረኛ ኮሮ​ጆ​ውም በኪሱ ከተ​ታ​ቸው፤ ወን​ጭ​ፍም በእጁ ነበረ፤ ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውም ቀረበ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች