Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 17:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ይህ​ንም ዐሥ​ሩን አይብ ወደ ሻለ​ቃው ውሰ​ደው፤ የወ​ን​ድ​ሞ​ች​ህ​ንም ደኅ​ን​ነት ጠይቅ፤ ወሬ​አ​ቸ​ው​ንም አም​ጣ​ልኝ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ይህንም ዐሥር የአይብ ጥፍጥፍ ለክፍል አዛዣቸው ዐብረህ ውሰድ፤ ወንድሞችህም እንዴት እንደ ሆኑ አይተህ፣ ደኅንነታቸውን የሚያረጋግጥ ምልክት ከእነርሱ ዘንድ አምጣልኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ይህንም ዐሥር የአይብ ጥፍጥፍ ለሻለቃው የጦር አዛዥ አብረህ ውሰድ፤ ወንድሞችህም እንዴት እንደ ሆኑ አይተህ፥ ደኅንነታቸውን የሚያረጋግጥ ምልክት ከእነርሱ ዘንድ አምጣልኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 እነዚህንም ዐሥር የአይብ ጥፍጥፎች ለሻለቃው የጦር አዛዥ ስጠው፤ ወንድሞችህም እንዴት እንዳሉ በዐይንህ አይተህ የደኅንነታቸውን መረጃ አምጣልኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ይህንም አሥሩን አይብ ወደ ሻለቃው ውሰደው፥ የወንድሞችህንም ደኅንነት ጠይቅ፥ ወሬአቸውንም አምጣልኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 17:18
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እር​ሱም፥ “ሄደህ ወን​ድ​ሞ​ች​ህና በጎቹ ደኅና እንደ ሆኑ እይ፤ ወሬ​አ​ቸ​ው​ንም አም​ጣ​ልኝ” አለው። ወደ ኬብ​ሮ​ንም ቆላ ላከው፤ ወደ ሴኬ​ምም መጣ።


እሴ​ይም እን​ጀ​ራና የወ​ይን ጠጅ አቁ​ማዳ የተ​ጫነ አህያ፥ አን​ድም የፍ​የል ጠቦት ወስዶ በልጁ በዳ​ዊት እጅ ወደ ሳኦል ላከ።


ከጥ​ቂት ቀን በኋ​ላም ጳው​ሎስ በር​ና​ባ​ስን፦“እን​ግ​ዲ​ህስ እን​መ​ለ​ስና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ባስ​ተ​ማ​ር​ን​ባ​ቸው ሀገ​ሮች ያሉ​ትን ወን​ድ​ሞች እን​ጐ​ብ​ኛ​ቸው፤ እን​ዴት እን​ዳ​ሉም እን​ወቅ” አለው።


በውኑ እንደ ወተት አላ​ፈ​ሰ​ስ​ኸ​ኝ​ምን? እንደ እር​ጎስ አላ​ረ​ጋ​ኸ​ኝ​ምን?


ማርና ቅቤ፥ በግና ላም ይበሉ ዘንድ ለዳ​ዊ​ትና ከእ​ርሱ ጋር ላሉ ሰዎች አመጡ። ሕዝቡ በም​ድረ በዳ ተር​በ​ውና ተጠ​ም​ተው ደክ​መው ነበ​ርና።


እስ​ራ​ኤ​ልም ዮሴ​ፍን፥ “ወን​ድ​ሞ​ችህ በሴ​ኬም በጎ​ችን የሚ​ጠ​ብቁ አይ​ደ​ሉ​ምን? ወደ እነ​ርሱ እል​ክህ ዘንድ ና” አለው። እር​ሱም፥ “እሺ” አለው።


ሳኦ​ልና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ሁሉ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጋር እየ​ተ​ዋጉ በኤላ ሸለቆ ነበሩ።


ሙሴም አማ​ቱን ሊገ​ናኝ ወጣ፤ እጅ ነሣው፤ ሳመ​ውም፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ሰላ​ምታ ተሰ​ጣጡ፤ ወደ ድን​ኳ​ኑም ገቡ።


ከመ​ን​ገ​ዱም ፈቀቅ ብለው ወደ ጐል​ማ​ሳው ሌዋዊ ቤት ወደ ሚካ ቤት መጡ፤ ሰላ​ም​ታም ሰጡት።


ዳዊ​ትም ዐሥር ብላ​ቴ​ኖ​ችን ላከ፤ ለብ​ላ​ቴ​ኖ​ቹም አለ፥ “ወደ ቀር​ሜ​ሎስ ወጥ​ታ​ችሁ ወደ ናባል ሂዱ፤ በስ​ሜም ሰላም በሉት፤


ዳዊ​ትም ደክ​መው ዳዊ​ትን ይከ​ተ​ሉት ዘንድ ወዳ​ል​ቻሉ፥ በቦ​ሦር ወንዝ ወዳ​ስ​ቀ​ራ​ቸው ወደ ሁለቱ መቶ ሰዎች መጣ፤ እነ​ር​ሱም ዳዊ​ትን ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩ​ትን ሕዝብ ሊቀ​በሉ ወጡ፤ ዳዊ​ትም ወደ ሕዝቡ በቀ​ረበ ጊዜ ደኅ​ን​ነ​ቱን ጠየ​ቁት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች