Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 15:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 ሳሙ​ኤ​ልም እስከ ሞተ​በት ቀን ድረስ ሳኦ​ልን ለማ​የት ዳግ​መኛ አል​ሄ​ደም፤ ሳሙ​ኤ​ልም ለሳ​ኦል አለ​ቀሰ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ሳኦ​ልን ስላ​ነ​ገሠ ተጸ​ጸተ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 ሳሙኤል ለሳኦል ቢያለቅስለትም እንኳ እስከ ሞተበት ዕለት ድረስ ዳግመኛ ሊያየው አልሄደም፤ እግዚአብሔርም ሳኦልን በእስራኤል ላይ በማንገሡ ተጸጸተ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 ሳሙኤል ለሳኦል ቢያለቅስለትም እንኳ እስከሞተበት ዕለት ድረስ ዳግመኛ ሊያየው አልሄደም፤ ጌታም ሳኦልን በእስራኤል ላይ በማንገሡ ተጸጸተ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 ከዚያን ሰዓት ጀምሮ ሳሙኤል በነበረበት ጊዜ ሁሉ ንጉሥ ሳኦልን በዐይኑ አላየውም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ሳኦልን በእስራኤል ላይ በማንገሡ ተጸጽቶ ስለ ነበር፥ ለእርሱ በማዘን ያለቅስለት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 ሳኦልም ወደ ቤቱ ወደ ጊብዓ ወጣ። ሳሙኤልም እስከ ሞተበት ቀን ድረስ ሳኦልን ለማየት ዳግመኛ አልሄደም፥ ሳሙኤልም ለሳኦል አለቀሰ፥ እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ሳኦልን ስላነገሠ ተጸጸተ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 15:35
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ልብ​ሱ​ንም አወ​ለቀ፤ በፊ​ታ​ቸ​ውም ትን​ቢት ተና​ገረ፤ ራቁ​ቱ​ንም ወድቆ በዚያ ቀን ሁሉ በዚ​ያም ሌሊት ሁሉ ተጋ​ደመ። ስለ​ዚህ፥ “ሳኦል ደግሞ ከነ​ቢ​ያት መካ​ከል ነውን?” ይባ​ባሉ ነበር።


“ሳኦል እኔን ከመ​ከ​ተል ተመ​ል​ሶ​አ​ልና፥ ትእ​ዛ​ዜ​ንም አል​ፈ​ጸ​መ​ምና ስላ​ነ​ገ​ሥ​ሁት ተጸ​ጸ​ትሁ።” ሳሙ​ኤ​ልም አዘነ። ሌሊ​ቱ​ንም ሁሉ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሳሙ​ኤ​ልን፥ “በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ እን​ዳ​ይ​ነ​ግሥ ለና​ቅ​ሁት ለሳ​ኦል የም​ታ​ለ​ቅ​ስ​ለት እስከ መቼ ነው? የዘ​ይ​ቱን ቀንድ ሞል​ተህ ና፤ በል​ጆቹ መካ​ከል ለእኔ ንጉሥ አዘ​ጋ​ጅ​ቼ​አ​ለ​ሁና ወደ እሴይ ወደ ቤተ ልሔም እል​ክ​ሃ​ለሁ” አለው።


ዘወ​ትር እን​ደ​ም​ነ​ግ​ራ​ችሁ፥ ልዩ አካ​ሄድ የሚ​ሄዱ ብዙ​ዎች አሉና፤ አሁ​ንም እነ​ርሱ የክ​ር​ስ​ቶስ የመ​ስ​ቀሉ ጠላ​ቶች እንደ ሆኑ በግ​ልጥ እያ​ለ​ቀ​ስሁ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰውን በም​ድር ላይ በመ​ፍ​ጠሩ ተጸ​ጸተ፤ በል​ቡም አዘነ።


የሳ​ኦ​ልም ልጅ ሜል​ኮል እስከ ሞተ​ች​በት ቀን ድረስ ልጅ አል​ወ​ለ​ደ​ችም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች