Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 15:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ሳሙ​ኤ​ልም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ስ​ራ​ኤል መን​ግ​ሥ​ት​ህን ዛሬ ከእ​ጅህ ቀደ​ዳት፤ ከአ​ን​ተም ለሚ​ሻል ለባ​ል​ን​ጀ​ራህ አሳ​ልፎ ሰጣት፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ሳሙኤልም እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔር የእስራኤልን መንግሥት ዛሬ ከአንተ ቀዶታል፤ ከአንተም ለሚሻል ለጎረቤትህ አሳልፎ ሰጥቶታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ሳሙኤልም እንዲህ አለው፤ “ጌታ የእስራኤልን መንግሥት ዛሬ ከአንተ ቀዶታል፤ ከአንተም ለሚሻል ለጎረቤትህ አሳልፎ ሰጥቶታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ሳሙኤልም ሳኦልን እንዲህ አለው፤ “ዛሬ እግዚአብሔር የእስራኤልን መንግሥት ቀዶ ከእጅህ በመውሰድ ለተሻለ ለሌላ ሰው ሰጥቶታል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ሳሙኤልም፦ እግዚአብሔር የእስራኤልን መንግሥት ዛሬ ከአንተ ቀደዳት፥ ከአንተም ለሚሻል ለጎረቤትህ አሳልፎ ሰጣት፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 15:28
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እር​ሱ​ንም ሻረው፤ ከእ​ር​ሱም በኋላ ዳዊ​ትን አነ​ገ​ሠ​ላ​ቸው፤ ‘የእ​ሴ​ይን ልጅ ዳዊ​ትን ፈቃ​ዴን ሁሉ የሚ​ፈ​ጽም እንደ ልቤም የታ​መነ ሰው ሆኖ አገ​ኘ​ሁት’ ብሎ መሰ​ከ​ረ​ለት።


ሰው ሁሉ በበ​ላይ ላሉ ባለ​ሥ​ል​ጣ​ኖች ይገዛ፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ል​ተ​ገኘ በቀር ሥል​ጣን የለ​ምና፤ ያሉ​ትም ባለ​ሥ​ል​ጣ​ኖች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ሾሙ ናቸው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ከሰ​ማይ ካል​ተ​ሰ​ጠህ በቀር በእኔ ላይ አን​ዳች ሥል​ጣን የለ​ህም፤ ስለ​ዚህ ለአ​ንተ አሳ​ልፎ የሰ​ጠኝ ሰው ታላቅ ኀጢ​ኣት አለ​በት” አለው።


ልኮም አስ​መ​ጣው፤ እር​ሱም ቀይ፥ ዐይ​ኑም የተ​ዋበ፥ መል​ኩም ያማረ ነበረ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሳሙ​ኤ​ልን፥ “ይህ መል​ካም ነውና ተነ​ሥ​ተህ ዳዊ​ትን ቅባው” አለው።


ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲያ ግን መን​ግ​ሥ​ትህ አይ​ጸ​ናም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ልቡ የሆነ ሰው መር​ጦ​አል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያዘ​ዘ​ህን አል​ጠ​በ​ቅ​ህ​ምና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ዝቡ ላይ ንጉ​ሥን ያነ​ግ​ሣል” አለው።


ሳኦ​ልም እጅግ ተቈጣ፤ ይህም ነገር ሳኦ​ልን አስ​ከ​ፋው፤ እር​ሱም፥ “ለዳ​ዊት ዐሥር ሺህ ሰጡት፤ ለእኔ ግን ሺህ ብቻ ሰጡኝ፤ ከመ​ን​ግ​ሥት በቀር ምን ቀረ​በት?” አለ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዳ​ዊት እንደ ማለ​ለት እን​ዲሁ ከእ​ርሱ ጋር ዛሬ ባላ​ደ​ርግ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​በ​ኔር ይህን ያድ​ር​ግ​በት፤ ይህ​ንም ይጨ​ም​ር​በት።


የዳ​ዊ​ት​ንም ዙፋን በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በይ​ሁዳ ከዳን ጀምሮ እስከ ቤር​ሳ​ቤህ ድረስ ከፍ ያደ​ርግ ዘንድ መን​ግ​ሥ​ትን ከሳ​ኦል ቤት ወሰ​ዳት።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ ዳዊት፦ በባ​ሪ​ያዬ በዳ​ዊት እጅ ሕዝ​ቤን እስ​ራ​ኤ​ልን ክፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅና ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው ሁሉ እጅ አድ​ና​ለሁ ብሎ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና እን​ግ​ዲህ አሁን አድ​ርጉ´ ብሎ ነገ​ራ​ቸው።


ዳዊ​ትም ሜል​ኮ​ልን፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ዘም​ሬ​አ​ለሁ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አለቃ እሆን ዘንድ ከአ​ባ​ት​ሽና ከቤቱ ሁሉ ይልቅ የመ​ረ​ጠኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​መ​ሰ​ገነ ይሁን፤ ስለ​ዚ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እጫ​ወ​ታ​ለሁ፤ እዘ​ም​ራ​ለ​ሁም፤


ነቢዩ ሳሙ​ኤ​ልም መለ​ሰ​ለት፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይመ​ለስ ዘንድ አል​ሰ​ማ​ውም፥ ስለ​ዚህ ገደ​ለው፤ መን​ግ​ሥ​ቱ​ንም ወደ እሴይ ልጅ ወደ ዳዊት አሳ​ለ​ፈው።


እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለጌ​ታዬ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቸር​ነት ሁሉ ያደ​ር​ግ​ል​ሃል፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ አለቃ አድ​ርጎ ይሾ​ም​ሃል፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰሎ​ሞ​ንን አለው፥ “ይህን ሠር​ተ​ሃ​ልና፥ ያዘ​ዝ​ሁ​ህ​ንም ትእ​ዛ​ዜ​ንና ሕጌን አል​ጠ​ብ​ቅ​ህ​ምና መን​ግ​ሥ​ት​ህን ከአ​ንተ ከፍዬ ለባ​ሪ​ያህ እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ታች ወደ ሰዎች ይመ​ለ​ከ​ታል፥ ሊመ​ረ​መሩ የማ​ይ​ችሉ ነገ​ሮ​ችን ሁሉ፥ ቍጥር የሌ​ላ​ቸ​ውን የተ​ከ​በ​ሩ​ት​ንና ድን​ቆ​ች​ንም ያስ​ተ​ው​ላል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች